የአብይ መንግስ ት የሚታነቅበት ገመድ ውስጥ አንገቱ አስገብቷል
Posted: 07 Oct 2020, 14:54
አሁን ያለው ብቸኛው አማራጭ ይህ ህገወጥ መንግስት ከስልጣን ወርዶ ለባለአደራ መንግስት ስልጣኑን ማስረከብ እና ባለአደራ መንግስትም በአጭር ጊዜ ውስጥ ነፃ ገለልተኛ ሆኖ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ምርጫ ማካሄድ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ፤ አሁንም ህገመንግስቱን የመጠበቅ ሓላፊነት የተሰጣቸው የፀጥታ ኣካላት ህገወጡን አካል ከስልጣን በማውረድ የባለአደራ መንግስት እንዲያቋቁሙ እድል ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሁሉም በየፊናው የየራሱ እርምጃ ይወስዳል፤ የትግራይ ክልልም ራሱን በራሱ የመከላከል እና መብቱን የማስከበር እርምጃ የመውሰድ ጉዳይ እጁ ላይ ነው፡፡ ይህ ህገወጥ ጥገኛ ሀይል በስልጣን ላይ ካለ አሁን በአገራችን ያለው የሰላም እና የመረጋጋት ችግር ተባብሶ ኢትዮጵያችን ምናልባት የሶማሊያ ዕጣ ሊደርሳት ይችላል፡፡ ይህ ከመድረሱ በፊት ግን በህገመንግስቱ መሰረት አገሪቱና ህገመንግስቱ የመጠበቅ ሀላፊነት የተሰጠው የመከላከያ ሰራዊታችን ባፋጣኝ ይህን ህገወጥ ሀይል ከስልጣን በማስወገድ ኢትዮጵያን እንዲታደጋት ይጠየቃል፡፡ ስለዚህ ደም መፋሰሱ ከመቀስቀሱ በፊት፣ ገመድ አንገቱ ላይ ያስገባውን ብልፅግና፣ ገመዱን ከአንገቱ አውጥቶ ከወንበሩ ይልቀቅ ካልሆነ ደግሞ ወንበሩን ከብልፅግና በማላቀቅ እዛው ራሱን እንዲሰቅል ማድረግ ነው፡
http://aigaforum.com/amharic-article-20 ... nging-rope
http://aigaforum.com/amharic-article-20 ... nging-rope