ባንኩ/መንግስት በሞባይላችን በሚልከው ብራችሁን ቀይሩ ማስጠንቀቂያ መስረት ወደ ባንክ ሄድኩ.. ግን አንድ ነገር ሠራተኞቹን አስደነገጣቸው/አስገረማቸው
Posted: 07 Oct 2020, 14:34
በሞባይል ስልካችን ሰሞኑን አስራ አንድ ቀን እንደቀረ እና ከ 100ሺ ብር በላይ ያላችሁ ቀይሩ የሚለው ነገር ስላልጣመኝ ወደ ባንክ ሄድኩ:: ደሞ ሚልዮን ብሬን ከጥቅም ውጭ ያረጉታል ብዬ ስለሰጋሁ ወደ ባንክ ሄድኩ:: ባንኩ በጣም ሕዝብ ይበዛበታል ብዬ ባስብም : ባዶ ነበር::
ደስ የሚለው ነገር ; የባንኩ ሰራተኞች ቅልጥፍና ነው:: ሳይታክቱ ደንበኛን ያስተናግዳሉ:: ሁሉን ጨርሼ ከመውጣቴ በፊት ግን ሠራተኞቹን አንድ ጥያቄ ጠይኩዋቸው::"ክሬዲት ካርድ እንዴትማግኘት እችላለሁ ? "ነበር ያልኩዋቸው:
ሰራተኛዋ ሙሉ በሙሉ ግራ ተጋብታ ነበር:: ከዛ ከበላዮችዋ ያሉትን ጠየቀች:: እነሱም ግራ ሆኖባቸዋል:: ቃስ ብላ "እኛ ጋር ክሬዲት ካርድ አገልግሎት የለም :: " አለች::
ይህ ነው እንግዲህ ባንካችን!!
ምንድነው እነሱ ያስፈራቸው? ባንኩ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት እንዳይኖረው ምንድነው እጁን የያዘው? ክሬዲት ካርድ ስላቸው የገባቸው ለአገር ውስጥ ብቻ የሚያገለግለውን መስሏቸው ይሆናል::
የእኔ ጥያቄ ግን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለውን ክሬዲት ካርድ ነበር:: master card: visa የመሳሰሉትን ነው::
አሁንም ይህ ነገር መልስ ይሻል::