Picture of the Day. The Mechanized Sawa Birgades versus Mechanized Adwa Brigades
Posted: 01 Oct 2020, 07:28


ጦርነቱ ተካሄደ።
በባድመ ግንባር ነበር የተጀመረው። ማጥቃቱን የጀመሩት ሶስት ክፍለ ጦሮች ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው፣ 20ኛው ሜካናይዝድ ክፍለ ጦርና አንድ ኰማንዶ ብርጌድ ተጨምሮ፣ ሌሎች ሁለት ክፍለ ጦሮች ታክለው በድጋሚ ተሞከረ። ከፍተኛ ሰብአዊና ማቴሪያላዊ ጉዳት ደርሶብን እቅዱ ሳይፈጸም ቀረ።
በባድመ ውጊያ በእቅዱ መሰረት መሄድ እንዳልተቻለ እየታወቀ፣ በፆረና በኩል ዉጊያው እንዲቀጥል ፃድቃን አዘዘ።
የዉጊያው እቅድ መግለጫ የተሰጠው እንፋራ በተባለ ቦታ ላይ ነበር። ፆረና ላይ ልዩ ዝግጅት ተደርጎ ነበር። 12,000 ያህል የትግራይ ሚሊሺያ፤ ከ5,000 በላይ አግላይ እንዲሁም ስንቅና ጥይት አቀባይ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ አህያና ፈረስም ለዚሁ ጦርነት ተሰልፈው ነበር። ለአንድ ሳምንት ያህል ከፍተኛ የጭንቀት ሙከራ ቢደረግም በዚያች ጠባብና ሙት መሬት የተሰለፈው ያ ሁሉ ንብረት፣ መሳሪያ፣ ሚሊሻና አግላይ፣ አህያና ፈረሶች ሳይቀር አንድ ላይ ረገፉ።