እንደ ምታቁት እኔ አቢይ አህመድን በብዙ ነገር እደግፈዋለሁ፣ ማለትም የኢትዮጵያ አጀንዳ፣ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ሲያራምድ ። በሌላው ነገር ሁሉ በአይነ ቁራኛ እጠብቀዋለሁ ማለትም እንደ መሪ ሃላፊነት ከመውሰድ ሲሸሽ፣ ለመሸወድ ሲጥር፣ ሌሎችን ሲንቅና ለመናቅ ሲሞክር፣ ወዘተ ።
ኤርሚያን በብዙ ብዙ ነገር እወደዋለሁ ። መዘርዘር አያስፈልግም ። እኔ ደግሜ ደግሜ ኤርሚያስን በሚመለከት ያቢይ ስህተት ምን እንደ ነበር ተናግሬያለሁ። አቢይ ኤርሚያስን በአጠገቡ ስራ ሰጥቶ የለውጡ አካል ማድረግ ሲችል አቢይ በፍርሃት ያሸሸው ይመስለኛል። ማለትም በአመለካከት አንድ ናቸው ። አቢይ የከፋ፣ የጂማ የዳሞት መንፈስ ነው ። ኢትዮጵያዊ ነው። ኤርሚያስ የሸዋ መንፈስ ነው ። በግንዱ ኦሮሞ በለው፣ ጂዳ በለው፣ አማራ በለው፣ ጉራጌ በለው ኤርሚያስ ኢትዮጵያዊ ነው። ያቢይ ስህተት ያ ነበር ።
ዛሬ አቢይ ከደቡብ ጋር፣ ካዲሳባ ጋር ግዙፍ ችግር ውስጥ የገባው እንደ ኤርሚያ ያሉ ሰዎችን በመፍራቱና አዲሳባና ደቡብን በአባ ዱላ በኩል አስገብራለሁ ማለቱ ነው።
ለዚህ ነው ምንም እንኳ ኤርሚያ በፍጹም ቁጣ ንዴትና ተቃውሞ ተሸፍኖ ማየት የሚገባውን ፕራግማቲክ ያቢይ ስራዎችና አገልግሎት ላለማየት ቢሸፈንም ኤርሚያ አቢይን በጸሃይ የሚያሳየን መስተዋት ነው። ላንድ ተገዢ ታክስና ቀረጥ ለሚከፍል ሕዝብ እንዲህ ያለ የገዥዎችን ገመና ጸሃይ ላይ ሚያሰጣ ሌላ ረድፍ ፍጹም፣ ፍጹም አስፈላጊ ነው።
ፖልቲካ ሁሉ የሃይል፣ ገንዘብ፣ ዝና እና ክብር ጉዳይ ነው። እናም አንድ ጥያቄ ላንሳ? ኦሮሞ ያገሩ ጠ/ሚ ነው ። በምን ሎጂክ ነው ባዲሳባ ሕዝብ የተመረጠውን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከንቲባ እንዲሆን አቢይ ያላደረገው? ይህ ነው ያምባገነንነት ጅማሮ እና ሌሎችን መናቅ የሚባለው ። ለዚህም ነው እንደ ኤርሚያ ያሉ በመንግስት ጉሮሮ ሚቀረቀሩ አጥንቶች በግድ የሚያስፈልጉት !!
ሰው ላይመስለው ይችላል ። ግን ሁሉም የራሱ ትዝብት አለው ። አቢይ የኤርሚያስን ተሳሳችነት ገሃድ ማድረግ የሚችለው እሱ የሚከሰስበትን ነገር ሲያርም ብቻ ነው፣ እንጂ የሳበር ተሳዳቢዮች በማሰለፍ አይደለም ። ኤርሚያ ያቢይ ድክመት ምን እንደ ሆነ ሊያሳምን የሚችለው ሚዛናዊ ያልተጋነነ ሰው ሁሉ የሚጠረጥራቸውን ያቢይድክመትና ውሸቶች ላይ ብቻ ሲተች ነው።
ማለትም ኤርሚያ በኢትዮጵያ አጀንዳ ላይ ሙሉ አመለካከቱን ይፋ አድርጎ ያንን መርህ አድርጎ አቢይን ሲተች ነው ሚዛናዊና ምክንያታዊ መሆኑን ሕዝብ ሚቀበለው !!!