የመስቀል ስጦታ ከጉራጌ፤ አቢይ አህመድ ስልጣን ላይ የሚቆየው ምን ቢያደርግ ነው?
Posted: 26 Sep 2020, 04:10
እኔ ሆረስ ነኝ ጣጣ አላበዛም፣ ቃላት አልፈልጥም ! የኬር መስቀል ለኢትዮጵያ !
አቢይ አህመድ በፍልስፍና ደረጃ በዛፍና በጫካ መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ ያቃል ። ግን ለሱ አስተዳደር ያለውን አግባብ ምን እንደ ሆነ አያቅም ። ባገራችን ሁኒታ ዛፎቹ ጎሳዎች ናቸው፣ ዛፉ ኦሮሞ ነው፣ ዛፉ አማራ ነው፣ ዛፉ ትግሬ ነው !!
ባገራችን ሁኔታ ጫካው ኢትዮጵያ ነች ! ጫካው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ፣ አንድ ሕዝብ !!!
አቢይ አህመድ ከፈለገ የራሱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልሂቆቹን ያማክር ። ዛፍ ሺ ግዜ ይበልጥ ውስብስብ ጽንሰ ነገር፣ ቅርጸ ነገር ነው ። ጫካ ሺ ግዜ ይበልጥ ቀላል ኮንሴፕት ነው።
ይህም ማለት አቢይ አህመድ በጎሳ ፖለቲካ፣ በጎሳ ሕገ መንግስት፣ በጎሳ ፌዴሬሽን እና በጎሳ ክልል ላይ ቆሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ወይም ፕሬዚዳንት ለመሆን ሚመኝ ከሆነ አቢይ ከፍተኛ የዊዝደም ችግር አለው ማለት ነው። አቢይ በጎሳ ማባበል፣ በጎሳ መወደድ ምናምን ላይ ከቆመ ብልጽግና አይደለም ባገሪቱ ሰላም ና መረጋጋት አያመጣም ፤ ብሎም ከስልጣን ይወርዳል ።
ይህም ማለት አቢይ ከዛፉ ጋር የወርዳል ። ነገር ግን አቢይ አህመድ የጫካው ምስጢር ከገባው ኦሮማራ፣ ኦሮትግሬ፣ ማራትግሬ ምናምን የሚሉ የፖለቲካ ደንቆሮችን ቅዠት በመተው ወደ ስይንስ አለም መግባት ግድ ይለዋል ። በጎሳ ሚዛንና፣ በዛፎቹ ውድድር ጫካ ሊያቆም አይችልም ።
የጫካው አካል መሆን የማይፈልግ እሾካም ግራር ወይም አረም ተቆርጦ ሲወገድ ነው ጫካው ሚለማው ሚለመልመው !!
አቢይ አህመድ በግድ ለራሱ ሃይልና ክብር ሲል በዘር መደራጀት ሕገወጥ ማድረግ አለበት ። ክልሎች የሚፈርሱበትን ፍኖተ ካርታ መልቀቅ አለበት ።
የጎሳ ሕገ መንግስት እንደ ገና እንደሚጻፍ ማወጅ አለበት ።
የዘር ፌዴሬሽን ዞሮ ዞሮ እሱ ራሱን ከስልጣን እንደ ሚያነሳው ማወቅ አለበት ። አሁን ያለው የዎያኔ ሰርዐት ያቢይ አይደለም ፣ የትግሬ ዎያነ ለራሱ ያቆመው ሲስተም ነው። አቢይ በዚያ ሲስተም ውስት ሆኖ ስልጣን ላይ አይቆይም ።
ሬፓፕሊካን ጋርድ ወይም ሌላ የዘብ ሃይል አቢይን በአካል ያጠብቁት ይሆናል ግን የሱን የፖለቲካ ሕይወት ሊያራዝሙ ከቶም አይችሉም። ያ የሚሆነው አቢይ የዘር ነጋዴዎችን እያነሳ ፣ በዕውነት የኢትዮጵያ ልሂቃን ፣ ምሁራል፣ ነጋዴዎች ፣ ገበሬዎች ሲተካና ያን መሰል ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ለሕዝቡ ሲያሳውቅ ብቻ ነው !!!