Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40410
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የመስቀል ስጦታ ከጉራጌ፤ አቢይ አህመድ ስልጣን ላይ የሚቆየው ምን ቢያደርግ ነው?

Post by Horus » 26 Sep 2020, 04:10


እኔ ሆረስ ነኝ ጣጣ አላበዛም፣ ቃላት አልፈልጥም ! የኬር መስቀል ለኢትዮጵያ !

አቢይ አህመድ በፍልስፍና ደረጃ በዛፍና በጫካ መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ ያቃል ። ግን ለሱ አስተዳደር ያለውን አግባብ ምን እንደ ሆነ አያቅም ። ባገራችን ሁኒታ ዛፎቹ ጎሳዎች ናቸው፣ ዛፉ ኦሮሞ ነው፣ ዛፉ አማራ ነው፣ ዛፉ ትግሬ ነው !!

ባገራችን ሁኔታ ጫካው ኢትዮጵያ ነች ! ጫካው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ፣ አንድ ሕዝብ !!!

አቢይ አህመድ ከፈለገ የራሱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልሂቆቹን ያማክር ። ዛፍ ሺ ግዜ ይበልጥ ውስብስብ ጽንሰ ነገር፣ ቅርጸ ነገር ነው ። ጫካ ሺ ግዜ ይበልጥ ቀላል ኮንሴፕት ነው።

ይህም ማለት አቢይ አህመድ በጎሳ ፖለቲካ፣ በጎሳ ሕገ መንግስት፣ በጎሳ ፌዴሬሽን እና በጎሳ ክልል ላይ ቆሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ወይም ፕሬዚዳንት ለመሆን ሚመኝ ከሆነ አቢይ ከፍተኛ የዊዝደም ችግር አለው ማለት ነው። አቢይ በጎሳ ማባበል፣ በጎሳ መወደድ ምናምን ላይ ከቆመ ብልጽግና አይደለም ባገሪቱ ሰላም ና መረጋጋት አያመጣም ፤ ብሎም ከስልጣን ይወርዳል ።

ይህም ማለት አቢይ ከዛፉ ጋር የወርዳል ። ነገር ግን አቢይ አህመድ የጫካው ምስጢር ከገባው ኦሮማራ፣ ኦሮትግሬ፣ ማራትግሬ ምናምን የሚሉ የፖለቲካ ደንቆሮችን ቅዠት በመተው ወደ ስይንስ አለም መግባት ግድ ይለዋል ። በጎሳ ሚዛንና፣ በዛፎቹ ውድድር ጫካ ሊያቆም አይችልም ።

የጫካው አካል መሆን የማይፈልግ እሾካም ግራር ወይም አረም ተቆርጦ ሲወገድ ነው ጫካው ሚለማው ሚለመልመው !!

አቢይ አህመድ በግድ ለራሱ ሃይልና ክብር ሲል በዘር መደራጀት ሕገወጥ ማድረግ አለበት ። ክልሎች የሚፈርሱበትን ፍኖተ ካርታ መልቀቅ አለበት ።

የጎሳ ሕገ መንግስት እንደ ገና እንደሚጻፍ ማወጅ አለበት ።

የዘር ፌዴሬሽን ዞሮ ዞሮ እሱ ራሱን ከስልጣን እንደ ሚያነሳው ማወቅ አለበት ። አሁን ያለው የዎያኔ ሰርዐት ያቢይ አይደለም ፣ የትግሬ ዎያነ ለራሱ ያቆመው ሲስተም ነው። አቢይ በዚያ ሲስተም ውስት ሆኖ ስልጣን ላይ አይቆይም ።

ሬፓፕሊካን ጋርድ ወይም ሌላ የዘብ ሃይል አቢይን በአካል ያጠብቁት ይሆናል ግን የሱን የፖለቲካ ሕይወት ሊያራዝሙ ከቶም አይችሉም። ያ የሚሆነው አቢይ የዘር ነጋዴዎችን እያነሳ ፣ በዕውነት የኢትዮጵያ ልሂቃን ፣ ምሁራል፣ ነጋዴዎች ፣ ገበሬዎች ሲተካና ያን መሰል ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ለሕዝቡ ሲያሳውቅ ብቻ ነው !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 40410
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የመስቀል ስጦታ ከጉራጌ፤ አቢይ አህመድ ስልጣን ላይ የሚቆየው ምን ቢያደርግ ነው?

Post by Horus » 26 Sep 2020, 04:32

ማለትም ይህን የሰማይ ስባሪ ሚያክል ዉሸት ላጋልጥላችሁ !!

ትግሬና አማራ ተፎካካሪ እንጂ እንደ ጎሳ ተደማሪ አይደሉም !! ትግሬ ካማራ አይደመርም፤ አማራ ከትግሬ አይደመርም ። ዉሸት! ዉሸት !

አምራና ኦሮሞ ተፎካካሪ ፣ ተወዳዳሪ ከባሰ ተጠጣሪ ከባሰ ተጎሻሻሚ እንጂ ተማማሪ አይደሉም ፣ አይሆኑም ። ኦሮሞ ኢትዮጵያን ኦሮሙማ ማድረግ ነው ሕልሙ ። አማራም ኢትዮጵያ አማራን እንድትመስል ነው ህልሙ !! ይህን ሚዋሹ ራሳቸው ላይ ነው ሚዋሹት !!

ስለዚህ የኦሮማራ ሰባኪዎች የቅዠት አማኞች ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን እነዚህ የጎሳ ቅዠቶች ካገራችህ እንዲጠፉ ሲያደርጉ ነው እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሚሆኑት !! አለያ ሌላውን ብሉ እንላለን ።

አማራ መቼ ነው ተነስቶ የጎሳ ሲስተም እንዲፈርስ የሚታገለው? ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሸዋ ኦሮሞ መቼ ነው ተነስቶ የጎሳ ሲስተም ይደምሰስ የሚለው?

ይህን ማያደርጉት ሁለቱም የኢትዮጵያ አጀንዳ ሳይሆን የራሳቸው ጎሳ አጀንዳ የዘው ፉክክር ነው ሚያደርጉት !! ይህ ደሞ የተበላ እቁብ ነው?

በዚህ የተበላ እቁብ ያቢይ እጣ ምንድን ነው?

የኬር መስቀል !!!!

Post Reply