ለሙሾ ፖለቲከኞች: ፍተሻው በጎጃም መስመር ብቻ አይደለም!!!!
Posted: 25 Sep 2020, 13:36
የፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ እያደረገ ያለው ከአማራ ክልል በሚመጡ መንገደኞች ብቻ ሳይሆን ወደ መዲናዋ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ተመሳሳይ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአልን ምክኒያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ይህንኑ ተከትሎ ሁከት እና ግጭት እንዲፈጠር በዝግጅት ላይ የሚገኙ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ መረጃውን መሰረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ። ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት አይኖርም በሚል የተለያዩ እንስቃሴዎች የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ ገልጸው የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።


