Page 1 of 1

የፖለቲካ ባለሙያዎች ምንድን ነው የሚታገሉለት ጥቅም?

Posted: 20 Sep 2020, 03:49
by Horus

ከቀበሌ እስከ ያገር ፕሬዚዳንትነት ያሉትን የስልጣን ቦታዎችን ለመያዝ ይህን ሁሉ ትግልና ድራማ ውስጥ የሚባክኑት ሰዎች ከተራ በር ከፋች ካድሬ እስከ ዘበኛ እስከ ኮኦማንዶ እስከ ክልል ካድሬ ክልል ፕሬዚዳንት ምን ፈልገው ነው ይህን የፖለቲካ ሙያ ስራዬ ብለው የተጠመዱበት?

1 ሁሉም ስልጣን፣ ሃይል፣ አዛዥነት ይፈልጋሉ !!

2 ሁሉም ደሞዝ፣ ጥቅማጥቅም፣ ጉቦ፣ ገንዘብ፣ ሃብት ቤት፣ መሬት ይፈላሉ !!!

3 ሁሉም ዜና ላይ መታየት ይፈልጋሉ ። ለዚህ ነው በሆነው ባልሆነው ሁሉ ቪዲዮ እየቀረጹ የሚያሰራጩት !! አትዩት ሳፍሯቸው !!!
የማንም ክታራ ሁሉ ቭድዮ ላይ የመታየት በሽታ አለው !!!

4 ሁሉም የሆነ የሌላችው ፣ ያጡት ፣ የጎደላቸው የተቀባይነት፣ ያለመታወቅ፣ የመናቅ፣ የመረሳት፣ የመወገድ ትራማና በሽታ አላቸው ። አሁን እነሱ እንደ ሱስ የሚፈልጉት ክብር ፣ ተቀባይነት ፣ ከፍ ከፍ መደረኝ ነው !!!

ብዙ ማለት ይቻላል ! ለዛሬ ይብቃን :idea: :idea:

Re: የፖለቲካ ባለሙያዎች ምንድን ነው የሚታገሉለት ጥቅም?

Posted: 20 Sep 2020, 05:51
by Guest1
ሁሉም የሆነ የሌላችው ፣ ያጡት ፣ የጎደላቸው የተቀባይነት፣ ያለመታወቅ፣ የመናቅ፣ የመረሳት፣ የመወገድ ትራማና በሽታ አላቸው ። አሁን እነሱ እንደ ሱስ የሚፈልጉት ክብር ፣ ተቀባይነት ፣ ከፍ ከፍ መደረኝ ነው !!!
መድረክ ላይ ሳይፈሩ በድፍረት መንግስት ያወግዛሉ። ለመታወቅና ለስልጣን ፓርቲ ይመሰርታሉ። ይታሰራሉ፤ ይገረፋሉ፤ ይሞታሉ። አሪፍ ፕሮፌሺን ነው ክክክክክክክክክክክክክክክ