Page 1 of 1
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ከበርቴ መደብ ማቆጥቆጥና የአቢይ አህመድ መንግስት
Posted: 19 Sep 2020, 02:01
by Horus
ከጥቂት ቀናት በፊት የአቢይን ስልጣን እንደ ምሰሶ የሚደግፉት ሶስት ረድፎችን አሳይቼ ነበር። እነሱም ቁልፍ ደጋፊ ረድፍ፣ ተጽኖ ፈጣሪ እና መራጭ ረድፍ ናቸው።
በእኔ አስተያየት እዚህ ቪዲዮ ውስጥ ያሉት 200 ብሄራዊ ከበርቴዎች በትክክል ቁልፍ ደጋፊ ረድፍ የሚመደቡ ናቸው።
ይህ ብቻ አይደለም የምዕራቡ አለም ከአረብ ዲፖልምሲና ከነትራምፕ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ለማምረከክ ሲሞክሩ አቢይ ከአገር በቀል ባለሃብት ባንድ ቃል ኢትዮጵያ ወዳድ ከሆነው ብሄራዊ ከበርቴ ጋር ሰምና ወርቅ መሆኑ እጅግ የሚደገፍና ትክክለኛ ፖሊሲ ነው።
የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪ የሚያሳድጉት፣ የላቀ ሚያደርጉት እነዚህ አገር በቀል፣ አገር ወለድ፣ አገር ወዳድ የቢዝነስ መደብ ናቸው ።
ዎያኔ የፈለፈላቸው ቆሻሻ፣ ከሃዲ ባንዳ ኪራይ ሰብሳቢዎች ከህዝቡ አፍ እየቀሙ ገንዘብ ካገር በማሸሽ ኢትዮጵያን የሚያደሀዩ ከጣሊያን ማያንሱ የባንዳ መደብ ናቸው።
Re: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ከበርቴ መደብ ማቆጥቆጥና የአቢይ አህመድ መንግስት
Posted: 19 Sep 2020, 02:50
by Horus
ያቤሎ
አንተኮ አንድ በትራማ ውስጥ የምትኖር የፖለቲካ ደንቆሮ ነህ ። ይህን ስማኝና ተማር ።
አንድ ፣ ኢትዮጵያ የምትባል በጣም የምወዳት በጣም የምቆረቆርላት አገር አለች ። የሷ መኖር ለሆረስ ከፈጣሪ መኖር እኩል ዋጋ ያለው ነገር ነው ።
አቢይ እስካሁን ድረስ ለኢትዮጵያ ታማኝ መሪ ነው። እንደ ዎያኔ ቆሻሻ ባንዳዎች ኢትዮጵያን ሲከዳ ያኔ ምን እንደ ምል ጠብቀኝ ።
ሁለተኛ በአንድ አገር ውስጥ ሕግ ና ሰርዐት ምን ግዜም መኖር ስላለበት መንግስት መኖር አለበት ። የመንግስት መኖር የሚቃወሙ ህጽናትና ደንቆሮ አናርኪስቶች ናቸው።
ሶስተኛ እንዳንተ ላለ መሃይም ድብቅ ነው እንጂ ፖለቲካ ምን እንደ ሆነ ለምናውቀው አቢይ አህመድ አንድ ፖለቲከኛ ነው፣ እናም እንደ አንድ አልቃሻ ህጻን ሳይሆን እንደ አንድ ፖለቲካ እንሰሳ ሆነን ነው ምናስተውለው ።
አቢይ ሲያፈነግጥ ይነገረዋል ይተቻል ፣ በቃላት ይደበደባል ። አቢይ የኢትዮጵያን ስራ ሲሠራ ይደገፋል ። እንደ እናንተ ካለ የቆሻሻው ዎይኔ ሌባ ቡድን ደጋፊ ይጠበቃል ።
ይህ ይበቃሃል ለዛሬ ። የሌባ ዘመን ሙሉ በሙሉ ያበቃል !!!
Re: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ከበርቴ መደብ ማቆጥቆጥና የአቢይ አህመድ መንግስት
Posted: 19 Sep 2020, 04:13
by Horus
ያቤሎ ።
አንተ ሳይክቴራፒ ትፈልጋለህ፣ በቃ ! አለማየሁ እሸቲኮ ግንቦት 7 ነው !! አንተ ቆርፋዳ ዎያኔ አሁን ወድቀሃልና ግዚዬን አታባክን ። ለኔ ዎያኔ ማለት አንድ ተራ ሌባ ወንጀለኛ ቡዲን ነው !!!
Re: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ከበርቴ መደብ ማቆጥቆጥና የአቢይ አህመድ መንግስት
Posted: 19 Sep 2020, 04:31
by Horus
አንተ ደደብ ዎያኔ ...
ያማርኛ ችግር እንዳለህ አቃለሁ ። ነገርኩህኮ አለማየሁ ያን የዘፈውነው ደብተራው በመተከል በረሃ በመልስ ከመገደሉ ከዘመናት በፊት ነው ። አንተ ዛሬ ነው የቆሻሻው ሌባ ቡድን ካድረ ሆነ እዚህ ዛሬ ህይወትክን ምታባክን ። አለማየሁ እሸቴ እያሸሸትሽ ኑሪ ብሎ ወጣት ያሰነሳው አንተ ዱላ ተሸክመህ ኩበት ስትለቅም ነው። ፈስ !! አሁን ምን ለመሆን ነው ምትሻው .. የወደቀ እበት ቆርቆሮ ለቃሚ !!!
Re: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ከበርቴ መደብ ማቆጥቆጥና የአቢይ አህመድ መንግስት
Posted: 19 Sep 2020, 04:46
by Horus
yaballo wrote: ↑19 Sep 2020, 04:39
Horicho,
The key word of my description regarding that song was? ... DEDICATED TO. That means that it does not matter when the song was first sang. CAPITO?? .. HARREE! .. Just try to enjoy the song as a reminder to your effort as a "wannabe EPRP urban guerrilla fighter" - dinqichom - or whatever you were upto then .. maybe selling something in merkato??
አንተ ዪልማ አጠራው ይህን ሰምተህ ዘናበል
Re: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ከበርቴ መደብ ማቆጥቆጥና የአቢይ አህመድ መንግስት
Posted: 19 Sep 2020, 16:15
by Horus
እኔ ለብዙ ዘመን እንዳልኩት ኤትኖክራሲ የሚባል ቀውስ እንጂ ዘመናዊ ፖለቲካ የለም ። የዘር፣ የዘውግ ቀመር የሶሺያል አንትሮፖሎጂ መስክ እንጂ የፖለቲካ መስክ ጽንሰ ነገር አይደለም። ስለሆነም ደንቆሮ የጎሳ ምሁር ነን ባዮች 50 አመት በጭለማ ውስጥ ከዳከሩ በኋላ ሁሉም (ስልጣን ላይ ያሉትም የሌሉትም) ተሸንፈው ብትንትናቸው ወጥቷል። አሁን አለምንም የፖለቲካ አላማ ያለውን መንግስት ሌት ተቀን ይቃወማሉ ።
ለምሳሌ የአቢይ አህመድን አካሄድ አስተውሉ ። የብልጽግና ፓርቲ ከጎሳ መሰረት ተነስቶ ቀስ በቀስ መሰረቱን ወደ ከተማ፣ ወደ ነጋዴው፣ ወደ ኢትዮጵያዊው ረድፍ እያዘመመ ነው። ስለሆነም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሚቆሙ ሰዎች ማድረግ ያለበት አቢይ አህመድ ሕዝባዊ መሰረቱን ከጎሳ ተኮር ሃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ተኮር ሃይሎች እንዲያዞር መገፋፋት ነው።
ለዚህም ነው አገር ወዳዱ ብሄራዊ ከበርቴ መደብ አቢይን በመደገፍ ያቢይ ቁልፍ ደጋፊ ረድፍ እና ባቢይ ላይ ተጽኖ ፈጣሪ ረድፍ መሆኑ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ እድገት እጅግ ወሳኝ ነገር ነው ። የጎሳ ረድፍና የጎሳ ድርጅቶችም ከኢኮኖሚ እድገት ሚፈይዱት አንዳች ነገር የለም ። እንዲያውም በተቃራኒው የጎሳ ንትርክ እስከ ገነነ ድረስ ብልጽግና ሚባል ነገር አይመጣም ።
አቢይ እንዳደረገው ፣ መንግስት ገንዘብ (ሬቬኑ) ይፈልጋል ፣ ባለሃብቱ መከበርና መደገፍ ይፈልጋል፣ ይህ ነው እየተደረገ ያለው መስተጋብር ። በተቃራኔው በሌብነት፣ ክራይ ሰብሳቢነት ላይ ያለው የቢሮክራሲ ከበርቴ (የሌባው ከበርቴ መደብ) ሙሉ በሙሉ ማክሰም ባይቻል እንኳ በጣም እንዲዳከም መሆን አለበት ።
ይህም የሚሆነው አቢይ አህመድ እነዚህን ሌባ የቢሮ ከበርቴን አንድ ባንድ ከስልጣን እያነሳ በሙያ ቴክኖክራሲ መደብ መተካት አለበት ።