Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42247
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የሌብነት ካልቸርና የብልጽግና ፓርቲ ቀውስ

Post by Horus » 17 Sep 2020, 02:49

እኔ ብዙ ሃተታ አላበዛም ።

ኢትዮጵያ የሌብነት ካልቸር አሸንፋ፣ አምክና ወደ ስራ ካልቸር ካልተሸጋገረች በምንም፣ በማንኛውም ተአምር ወደ ብልጽኛ አትሸጋገርም። በመሆኑም አሁን አቢይ አህመድ እና የብልጽግና ፓርቲ የሚሰብኩት የኢትዮጵያ የ10 እና የ20 አመት የብልጽግና ራዕይና ፕላን ከንቱ ሆኖ ይቀራል ።

አቢይ አህመድ 4 ቁልፍ ምሰሶዎች ጠቅሷል ፤ እነሱም አልትራ፣ ሱፐር፣ ኢንትራ፣ ኢንፍራ እስትራክቸር ይባላሉ። ከነዚህ ሶስቱ የካልችር አካላልት ናቸው ። እነሱም አልትራ፣ ሱፐር፣ እና ኢንትራ እስትራክቸር ናቸው። ይህም ማለት የአንድ አገር አልትራ እስትራክቸር ሌብነትና ሙስና ከሆነ ፤ ያንድ አገር ሱፐር እስትራክቸር ሌባና ሙሰኛ ከሆነ ፤ ያንድ መንግስት ኢንትራ እስትራክቸር የሌባና ሙስና ካልቸር ከሆነ ያ አገር ሊበለጽግ አይችልም፣ ብሎም ይወድቃል ።

በመሆኑም አሁን የገንዘብ ለውጥ መደረጉ አንድ ጥሩ መጀመሪያ ነው ። ግን አሁንም ብዙ ብዙ የሌብነት ደኖች በሰፊው ተለቀው እየተስፋፉ ነው። አዲስ አበባ በራሷ ሰው እስካልተገዛች ድረስ የሌብነት ካልቸር ማዕከል ሆና ትቀራለች ። የቤትና የመሬት ዘረፋና ሌብነት ይቀጥላል።

በአንድ ቃል ከሌብነት እና ሙስና ነጻ የሆነ ካልቸር ስትፈጥር ኢትዮጵያ በፍጹም ወደ እድገት፣ ብልጽኛ፣ ዴሞክራሲ ወይም ስልጣኔ መሸጋገር አትችልም። ሌብነትን ማጥፋት ከኣባይ ግድብ፣ ከሕገ መንግስት፣ ከዴሞክራሲ እኩል ዋጋ ያለው ነገር ነው።

ታዲያ ለምድን ነው የብልጽግና ፓርቲ ቀውስ ያልኩት? ከአቢይ አህመድ ባህሪ መገመት የሚቻለው የብልጽግና ፓርቲ ብቸኛ አውራ አምባ ገነን ፓርቲ ሆኖ መቀጠል ይፈልጋል። ይፈልጋሉ ። ይህም ማለት ትልቁ፣ ግዙፉ የሌብነት፣ የሙስና ዋሻ የሚሆነው ይህ ፓርቲ ነው ። ምክንያቱም ...

ስልጣን ያባልጋል፣ ፍጹም ስልጣን ፈጽሞ ያባልጋል የሚለው የፖለቲካ ሳይንስ ሕግ ስለሆነ ነው ። ይህን ሳይንስ የማያውቁ የፖለቲካ ሃሁ አያቁም ። ይህን ሃቅ የሚክዱ፣ የሚደብቁ ብልጥ የፖለቲካ ነጋዴች እንጂ ያገር መሪዎች አይደሉም። የአንድ ፓርቲ አምባገነነት ዋናው የሌብነት፣ የሙስና የብልግና ዋሻ ነው ።







Post Reply