Page 1 of 1

አማራጭ የሌለው ምርጫ እና ተወዳዳሪ የሌለው ሩጫ አሸናፊ የለውም!!!!

Posted: 11 Sep 2020, 16:11
by pushkin
በትግራይ ክልል በተካሄደው የጨረቃ ምርጫ ለመሳተፍ ተመዝግቧል የተባለው 2.7 ሚሊዮን ህዝብ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 2,633,848 ድምፅ ሰጥቷል ተብሏል። እንደ አዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ድምፅ ሰጡ ከተባሉት ውስጥ 2,590,620 ህወሓትን ሲመርጡ 20,839 ባይ ቶናን፣ 18,479 የትነፓን፣ 3,136 ሳልሳይ ወያኔን፣ እንዲሁም 774 ደግሞ አሲምባን መምረጣቸው ተገልጿል። በዚህ መሠረት በጨረቃው ምርጫ ከጠቅላላው ድምፅ ሰጪ ውስጥ ህወሓት = 98.4%፣ ባይቶና= 0.8%፣ ትነፓ = 0.7%፣ ሳልሳይ ወያነ = 0.1%፣ እንዲሁም አሲምባ= 0.0% (ሲጠጋጋ) ድምፅ አግኝተዋል። በመሠረቱ ምርጫ ሊኖር የሚችለው አማራጭ ሲኖር ብቻ ነው። አማራጭ የሌለው ምርጫ እና ተወዳዳሪ የሌለው ሩጫ አንድ ናቸው።