“የኤርትራ ሹመቴ በዲፕሎማሲ ህይወት ውስጥ በድጋሚ ሊገኝ የማይችል ትልቅ ዕድል ነው” / አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
Posted: 10 Sep 2020, 21:27
Ethiopian News & Opinion
https://mereja.forum/content/


የኤርትራ ሹመቴ በዲፕሎማሲ ህይወት ውስጥ በድጋሚ ሊገኝ የማይችል ትልቅ ዕድል ነው
ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡ከኤርትራ መንግሥት ጋር ለዓመታት ሰፍኖ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃም ከልብ እንፈልጋለን፡፡ የበኩላችንንም እንወጣለን፡፡ በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ አገር ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችንን በውይይት ለመፍታት ያለንን ዝግጁነት እየገለጽኩ፣ የኤርትራ መንግሥትም ተመሳሳይ አቋም እንዲወስድ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ

አሁን ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እያገለገሉ ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ኢትጵያና ኤርትራ ወደ ጦርነት ሲያመሩ ሰራተኛ እንጂ ባለሥልጣን የገዢው ፓርቲ (ኢህአዴግ) አባልም አልነበሩም፡፡ ፓርቲውን በአባልና አመራርነት የተቀላቀሉትም በ1994 ዓ.ም ነበር፡፡ ኢትዮጵያን በኤርትራ እንዲወክሉ ሲሾሙም በአየር ላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡አንድ በዲፕሎማሲ ውስጥ ያለሰው መልሶ ሊያገኘው የማይችል ዕድል ነው
ሲሉ መልሰዋል፡፡የዚህን ታሪካዊ ግንኙነት ሄደህ ማሳለጥ የምትመራበት ዕድል ማግኘት ከሁሉም አይነት ኃላፊነቶች የበለጠ ነው፤ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል እና በከፍተኛ አመራሮቼ ወደ አስመራ ሄደህ አግዝ ስባል ሳላቅማማ ነው የሄድኩት፡፡ አርብ ተደውሎልኝ ሰኞ አዲስ አበባ መጥቻለሁ
በወቅቱ ጀምረውት የነበረውን የሦስተኛ ድግሪ (Phd) ትምህርት አቋርጠው መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ጥሪው ታሪካዊ በመሆኑ
ሲሉም ነው ዲፕሎማቱ በወቅቱ የነበረውን የሹመቱን ሁኔታ የሚያስታውሱት፡፡አንድ በዲፕሎማሲ ውስጥ ያለሰው ሊያገኘው የማይችል በብዙ ዓመታት አንድ ጊዜ ሊከሰት የሚችል በሀገርህ ሳይሆን ምናልባት በሌላ ሀገር ሊከሰት የሚችል ነገር ነው እኔ ጋር የመጣው እና በዚህ ረገድ ደስተኛ ነበርኩ ማለት ነው በደስታ ተቀብየ ነው የሄድኩት
አምባሳደሩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች እና የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው በሰሩባቸው ጊዜያት ሁለቱ ሀገራት በበጎ አይተያዩም ነበር፡፡ በዐይነ ቁራኛም ነበር የሚተያዩት፡፡ ይህን ጉዳይ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዴት ሊያጣጥሙት እንደቻሉ ለቀረበላቸው ጥያቄሹመቱ ትልቅ ስሜትና ደስታ የመስጠቱን ያህል ስጋት ነበረበት
የሚል ምላሽን ሰጥተዋል፡፡የካቢኔ አባል የፓርቲ ኃላፊም ሆኜ እንደ ፖለቲካ የሚወሰደውን አቋምም የግሌን አቋምም፣ የግሌ ያልሆነ አቋምም መግለጽ ስለነበረብኝ ስገልጽ ቆይቻለሁ በዚህ ረገድ ሁሉንም ጠባሳ አውቀዋለሁ፡፡ እንደ ጓደኞቼ ሳስብ የሄዱት ጓደኞቼ ይናፍቁኛል፤ እንደ መንግስት ሳስብ የኢትዮጵያን አቋም ሳራምድ ቆይቻለሁ
ሲሉም ምክንያታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡20 ዓመት ሙሉ የተቋሰለን ነገር በመሪያችን የተለየ ስብዕና፣ የተለየ ድፍረት ምክንያት የመጣ ሰላም ነው እንጂ ያ ሁሉ መቋሰል እየተሟሸ እየተሟሸ የረገበ አልነበረም በዛኛው በኩል ግንኙነቱን በበጎ መቀበል ቢኖርም መሬት ላይ ሲወርዱ ምን ምን ነገሮች ሊከተሉ ይችላሉ በምን ያህል ፍጥነትስ ወደተሻለ መንገድ ያመጣል የሚለው ያሰጋ ነበር
ነው የሚሉት አምባሳደሩ፡፡ተገፍቼ ነበር የወጣሁት
በሚልም ስለሁኔታው ይናገራሉ፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ የመስራት ፍላጎት አልነበረኝም፣ መማርም ቤተሰቦቼንም ማራቅ ስለነበረብኝ በወቅቱ ከነበሩት ኃላፊዎቼ ተደራድሬ፤ ሌላ የተሻለ ትልቅ ሀገር ተመድቤ አልፈልግም ብዬም ነበር የሄድኩት፡፡ ስለዚህ ቀለል ያለ ቦታ የፈለኩበት ከማንም ላለመነጋገርና ትምህርቴን ለመማር ነው
እንደ ትልቅ ነገር መታየት እንዳለበት አብራርተዋል፡፡የተበጣጠሰ ቤተሰብ ማገናኘት፤ ተለያይቶ የቆየን ዝምድና መቀጠል ብሎም ለመተጋገዝ የሚያስችል መንፈስን መፍጠር

የሚሉም ሲሆን ግንኙነቱን ተቋማዊ ለማድረግም እየተሰራ እንደሚገኝ ይገልጻሉ፡፡ከሁሉም በላይ የተፈጠረውን ጠባሳ ማከም ይቀድማል
In my opinion, brother Aurorae does not trust Ethiopian regimes and elites. I think brother Aurorae is trying to over read and over think something it is not there. I understand him very well as an Eritrean brother who has been struggling to accept the new peace between the people of Eritrea and Ethiopia as well as the relationship between PIA and Dr. Abby......



