የዛሬው የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ‼️
Posted: 05 Sep 2020, 14:21
ተገምቶ የነበረውን ወታደራዊ እርምጃ ይበልጥ legitimate የሚያደርግ ሲሆን፣ በምርጫው ከህወሓት ውጭ (በጣምራም ቢሆን) የክልል መንግስት መመስረት ለቀጥተኛ እርምጃ ለም መሬት መፍጠር ማለት ነው። ስለዚህም ውጤቱ ለታወቀ ጉዳይ አላስፈላጊ ምክንያትነትን ህወሓት ያስቀር ዘንድ አንድ የመጨረሻ እድል ተሰጠው ማለት ነው። ያኔም ወታደራዊ እርምጃውን (ልክ ዛሬ በተገለጠው መልኩ ህዝቡ እንዳይጎዳ በሚል) ለማስቀረት/ለማቆየት ቢፈለግ ራሱ፦
፩) ክልሉን ለማስተዳደር ፌዴራል መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር ሊመሰርት ይችላል
፪) ይህን የሚገዳደር የኃይል ተግባር በህወሓት ቀድሞ ከተደረገ ደግሞ ለቀሪው ውጤት ሁሉ ኃላፊነቱን ህወሓት ይወስዳል ማለት ነው።
፫) ይህ ሁሉ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ክልሉን ከበጀት ውጭ ያደርጋል ማለትም ነው።
፬) ህጋዊነት የለውም ተብሎ በፌዴሬሽን ምክርቤት የተወሰነበትን አካል እንደ መንግስት ቆጥሮ ሊታዘዘው የሚገባ የክልል ኃይል አይኖርም ማለት ነው (ይህ እንግዲህ ህገወጡን የፀጥታ መዋቅርና የትህነግን ትስስር ትተን ማለት ነው) ስለዚህም አልታዘዝም የሚል የክልሉን ፀጥታ መዋቅር የመጠበቅና ከለላ የመስጠት ተግባርን ፌዴራል መንግስቱ ያገኛል። የክልሉ ፀጥታ መዋቅር ደግሞ ለህገወጥ ፓርቲ ሳይሆን ለክልሉ ህዝብ አገልጋይነቱንና ለህገመንግስቱ ተገዢ እንዲሁም ጠባቂ የመሆን ግዴታውን ማረጋገጥ ይኖርበታል ማለት ነው።
፭) በፌዴሬሽን ምክርቤቱም ይሁን የክልል ም/ቤቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ክልሉ ምንም ቦታ አይኖረውም ማለት ነው።
፮) ትህነግ አንቀፅ 39 እያሉ የሚያናፉበትንም ይሁን የትኛውንም ለመተግበር የሚያስችል ቅቡልነት አይኖረውም ማለትም ነው፣
፯) የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት፣ ህወሓትን እንዲህ የሚሉ ምርጫዎች ላይ ይጥሉታል:-
፯.፩) የተሰጠውን እድል ተጠቅሞ የቁም ተዝካሩን ይሰርዛል፣
፯.፪) ይህ ውርደት ከመሰለው ደግሞ ፣የፌዴራል መንግስቱ ወደፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚያደላ ተስፋ በማድረግ የ"ምርጫ" ድግሱን ለይስሙላ በማካሄድ ራሱን አሸናፊ ያደርግና የፌዴራል መንግስት "በዚህ የጨረባ ድግስህ የተነሳ ሳይሆን ፣ በፊት በነበረህ ቅቡልነት ስራህን ቀጥል" እንዲለው ራሱን ያመቻቻል (ለታይታ ግን ዋጋ ያልተሰጠውን ድግሱን እያሳየ መደስኮሩን ይቀጥላል)
፯.፫) በትዕቢቱ ይፀናና እያንዳንዷን ነገር በነካ ቁጥር "ፋወል! " እየተባለ ፣ መከራው ሲጠናበት ለይቶለት ያብዳል፣ የፌዴራል መንግስቱም ሰራዊቱን ልኮ ቀብሩን ይፈፅምለታል።
ለኔ የዛሬው ውሳኔ ከባድ ሚዛን አሸናፊነትን ለመንግስት ሰጥቶታል ።
Fassil Shiferaw