Page 1 of 1

ማን ይሆኑ እሳቸው?!?

Posted: 04 Sep 2020, 11:31
by Meleket
የሎሚ ተረት

ክቡር ሰው እሳቸው
ፍፁም ቀና ነበር - አጀማመራቸው
በደስታ ሚስቁ - ተሳክቶ ኑሮአቸው
ሰዎችን በማየት - በደስታ ማንባት - ነበር ምኞታቸው

ግልባጩ ሆነ - ነገሩ ተሳክሮ
ስደት በረከተ - ሰቆቃ እና ሮሮ
ክቡር ሰው እሳቸው - የተስፋው ጀማሪ
በሚያለቅሱ ሰዎች - ዋይታና እሪ!
መደሰት ጀመሩ - አቁመው አዝማሪ
(ግጥም - ተ.ገ.)

የስደተኛው ማስታወሻ ገጥ 289፣ 2006 ዓ.ም. 2013 G.C