° የአማራ ፖለቲከኞች "ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!" ከሚል ጆሮ የሚያደነቁር ባዶ ለቅሶ ተላቀው የሚከበር፣ የሚበላ፣ የሚጠጣ ስትራቴጂ እና ታክቲክ መንደፍ ይጠበቅባቸዋል። * ተስፋዬ ገ/አብ
Posted: 04 Sep 2020, 04:07
×የሓዳስ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ "መቐለ" ይሆናል×
×ወድያው ደግሞ 'የኦሮሚያ'ዋና ከተማ "ፍንፊኔ" ይሆናል' ማለትም... የመቐለ"ኢትዮጵያ"ና የፍንፊኔ" ኦሮሚያ አምባሳደር ይለዋወጣሉ:: ተስፋዬ ገ/አብ
አፍሪቃ ቀንድ ነገ!
የወያኔ ፖለቲከኞች "ሉአላዊነታችንን ካወጅን 'ኢትዮጵያ' የሚለው ስም መነሻው የኛ ስለሆነ ይዘነው እንሄዳለን!" እያሉ ሲያስፈራሩ ሰንበተዋል። በርግጥ ማስፈራራት ላይሆን ይችላል። አብይ እንደ አገር መሪ ትግራይ ክልልን በካሮትም ሆነ በዱላ ማስገበር ካልቻለ ወያኔ ያለመችውን ለመፈጸም እድል ታገኛለች።
እንደሚባለው የሓዳስ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ "መቐለ" ይሆናል። በዚያው ቅጽበት ደግሞ "ኦሮሚያ" እንደ ሉአላዊ አገር እንደምትመሰረት ተስፋ ያደርጋሉ። የኦሮሚያ ዋና ከተማ ደግሞ "ፍንፊኔ" ይሆናል። ማለትም የመቐለ "ኢትዮጵያ" እና የፍንፊኔ "ኦሮሚያ" አምባሳደር ይለዋወጣሉ።
ይህ ከተፈጸመ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ አገር አልባ ሆኖ ይንሳፈፋል! ወይ ደግሞ ወደሚቀርበው፣ ወደሚመቸው ይጠቀለላል። ደቡብ እና ኦሮሚያ የሚያግባባ የጋራ ታሪክ ስላላቸው ችግር አይኖረውም። አሳሳቢው የአማራ ህዝብ ጉዳይ ነው። ምናልባት ባህርዳርን ዋና ከተማ በማድረግ የፈረንጅ ቃሪያ ቅርጽ ያላት አገር ይመሰርታሉ። "ኢትዮጵያ" የሚለው ስም ቀድሞ ከተያዘባቸው የአገራቸውን ስም 'አቢሲንያ" ለማለትም ይገደዱ ይሆናል። ወዳጄ አበበ ገላው "አቢሲንያ ለዘልአለም ትኑር!" የሚል የፌዝ-ቡክ Profile Picture ሲለጥፍ አይተን እንሳቀቅም ይሆናል። ርግጥ ነው፣ በዚህ ዋዘኛ ትረካዬ የሚስቅና የሚያሾፍ፣ ምናልባትም የሚያዝን ሊኖር ይችላል። መሳቅም ሆነ ማዘን አይገባም። መሆን ያለበት "መንቃት" ነው።
ከዚህ አባባሌ የከፋ ነገርም ሊያጋጥም ይችላል። ፕሮፌሰር መረራ በጥናት ጽሁፉ እንደገለጸው በግብጽ እና በሱዳን የሚደገፍ ሃይል ፍንፊኔን ሊቆጣጠርም ይችላል።
በፖለቲካ መንገድ ላይ "ክህደት" የሚባል ነገር የለም። የሚመችህን ታደርጋለህ። ካሸነፍክ ታሪክ ከጎንህ ይቆማል። ጀግና ትባላላህ። ከተሸነፍክ "ከሃዲ" ይለጠፍብሃል። ቀና መንገድ ይዘህ ሳለ መሸነፍ ሊያጋጥም ይችላል። ታሚል ታይገርስ ዛሬ የትም የሉም። በጦርነት ስለተሸነፈ እንጂ ደጃች ውቤ ከአጤ ቴዎድሮስ የተሻለ ራእይ ነበረው። ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የተዳከመ ሁኔታ ስናስብ ፕሮፌሰር መረራ እንዳለው በውጭ ሃይል ትብብር ልትያዝ ትችላለች። ምንም ዋስትና የለም።
ቅዱስ አቡነ አርዮስን የመሰለ ሊቅ ያበቀለችው ሊቢያ ዛሬ የት ናት? የሶማሊያ ምርጥ ዩኒቬርስቲዎች የሜዳ ውሻ ማደሪያ መሆናቸውን ማስታወስ ይገባል። "ቀይ ባህር ደማችን፣ ኤርትራ አንገታችን" የሚለው ዘፈን ተረስቶ "ኦሮሚያ ሆዳችን" በሚል መተካቱም የኛው ዘመን ታሪክ ነው።
እዚህ ላይ ሂትለር ትዝ አለኝ። በርሊን ስትከበብ እንዲህ አለ፣
"ሌላው ደህና! በርሊንን መያዝ ግን የማይታሰብ ነው!"
አንድ ሚሊዮን የናዚ ሰራዊት በርሊንን ከቦ ነበር። በሩስያውያን የተመራ ሃይል አንዱን ግንባር ጥሰው እንደ እግር ኩዋስ እየነጠሩ ሲገሰግሱ ጀብደኛው አዶልፍ ሂትለር ራሱን ከማሰናበት በቀር አማራጭ አልነበረውም።
ማለት የፈለግሁት ምንድነው?
የኔ ወንድም! ከልቤ ልምከርህ?
"ጫማ ስትገዛ ቁጥርህን በትክክል እወቅ!"
በነገራችን ላይ ይህ ሁሉ አባባል የኔ አሳብ፣ የኔ ሙዋርት አይደለም። ሲባል የኖረ ነው። ሲፈጭ - ሲከካ - እና ሲጋገር የሰነበተ ነው። በወቅቱ አላመንኩትም ነበር እንጂ ጋዜጠኛው ዳዊት ከበደ አብርሃም ያየህን ቃለመጠይቅ ባደረገው ጊዜ ይህን ህልም እና እቅድ በጨረፍታ ነግሮን ነበር።
የአማራ ፖለቲከኞች "ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!" ከሚል ጆሮ የሚያደነቁር ባዶ ለቅሶ ተላቀው የሚከበር፣ የሚበላ፣ የሚጠጣ ስትራቴጂ እና ታክቲክ መንደፍ ይጠበቅባቸዋል። ማለትም ትምክህታቸውን ቆፍረው በመቅበር በመከባበር ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ ማዳበር አለባቸው።
እኔ እንደሚመስለኝ . . .
ወያኔ "ኢትዮጵያ" የሚለውን ስም በመውረስ ለመገንጠል ያሰበችው በርግጥ "ኢትዮጵያዊነትን" በማፍቀር አይደለም። የወያኔ ዋና አላማ አፋር፣ ቅማንት፣ ህዳሴ ግድብ፣ ዳቡስ ወንዝ፣ ቤኒሻንጉል እና ወሎን ለመጠቅለል በመመኘት የመስላል። "ሃገረ ትግራይ" ብላ ብትገነጠል "ገንፎ" እንደምትሆን ገብቶአታል። እና ባላት አቅም አርቃ ለማሰብ እየሞከረች ነው።
በርግጥ እያናናቅሁ አይደለም!
ስብሃት ነጋ የሚመራው የወያኔ ቡድን ድምጹን አጥፍቶ ስራውን እየሰራ መሆኑን ማመን ይገባል። በደፈናው መናቅ እና ማናናቅ ጅልነት ነው። ህልማቸው ረጅም መሆኑን ሜድያቸውን መስማት ብቻ ይበቃል።
አንዳንድ ደግ እና የዋህ ኤርትራውያን ወያኔ በኤርትራውያን ላይ ያላትን ድብቅ አጀንዳ ባለመረዳት፣ ወያኔ በኤርትራውያን ላይ የፈጸመችውን መራር ግፍ ችላ ብለው ወይም ረስተው አብረው ሲደነሱ መታየታቸው ገራሚ ክስተት ነው።
ለአብነት በቅርቡ ሰናይ ሰሎሞን ሃምሌ 26 2020 ከስዊድን ዮቶበሪ ይፋ ያደረገውን አስደንጋጭ መረጃ ማየት ይበቃል። ማለትም የደግ ኤርትራውያን የዳንስ መጨረሻ እግርህን ተሰብረህ ቁጭ ወይም እንደ ራስ ወልደሚካኤል ሰሎሞን "ታሪካዊ ሞኝ" መሆን ይሆናል።
የኦሮሞን ህዝብ ትግል ከወያኔ ተንኮለኛ የፖለቲካ ሴራ ጋር ማያያዝ ልክ ሊሆን አይችልም። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የኦሮሞ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ ውስጥ አገሪቱን በዴሞክራሲያዊ ስርአት የማስተዳደር ብቃት እና ፍላጎት ያላቸው ይመስለኛል። ነጻ ኦሮሚያን መመስረት ከፈለጉም የኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ እንጂ ከወያኔ ጋር አይያዝም። ወያኔ ለጥቅምዋ እንደምታውለው ግን አያጠራጥርም።
Tesfaye Gebrab