ከዋናዋናዎቹ "ፖስቶ አዳሪ" ተካፋይ የአብይ አህመድ እና የታከለ ካድሬዎች!!
"0ኛ" ኢሳት ቲቪ እና ጋዜጠኞቹ
1ኛ. ናትናኤል መኮነን
2ኛ. ስዮም ተሾመ
3ኛ. የኦናታን ተስፋዬ
4ኛ. ኮር ዳዊት
Minalachew Simachew Yeshiwas
ትዝታ ዘ ኢሳት!!
"እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል " እንዲሉ! ኢሳት በነበርንበት ወቅት ለእውነት በጋራ የቆምንበት ጊዜ ተረስቶ የራሳችን ባልደረቦች እንዴት ይፈታተኑን እንደነበር ለማስታወስ ነው::
በዛን ጊዜ የቆምንላት እውነት እንዲህ እንደዛሬው በአስመሳዮች ሳትሸረሸር "ከ40 ለሚበልጡ የኦሮሚያ ብርድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ጋዜጠኞች እና የአስተዳደር አካላት የጊዜው የአዲስ አበባ ከንቲባ ኮንደሚኒየም በነፃ ሰጡ " የሚለውን የተረኝነት ጉዳይ ዜና የውስጥ ምንጮቼን ጠቅሼ የሰራሁት እኔ እንደነበርኩ አስታውሳለሁ::
በወቅቱ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና ታከለ ዑማ አወዳሽ የነበሩት ሁለቱ የኢሳት ባልደረቦቼ ለለውጡ የጫጉላ ሽርሽር አዲስ አበባ በሄዱበት ወደ እኔ ደውለው "ከንቲባውን እንዴት በሀሰት ትወነጅላለህ ?" ብለው በመውቀስ ዜናው ከገፃችን ላይ እንዲነሳ ሊያስገድዱኝ ሞክረው እንደነበርም አልዘነጋውም::
በወቅቱ አስተባባሪያችን የነበረውና ሁላችንም የምንወደው ታማኝ በየነ ኮንደሚኒየም ያለእጣ የታደላቸውን የኦሮሚያ ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር እና ማስረጃ አይቶ ከጎኔ ባይቆም ኖሮ በኔ ላይ የጀመሩትን ከስራ የማሰናበት ሴራ ያኔ ቀድመው ይፈፅሙት እንደነበር አሁን ላይ ሆኜ አስባለሁ::
ያኔ ታዲያ በዜናው የተደናገጠው የወቅቱ የአዲስ አበባ ከንቲባ ታከለ ዑማ ለታማኝ ደውሎ ዜናውን ለማስተባበል የባጥ የቆጡን ቢያወራም : -
" በእኔ የአስተዳደር ዘመን ሳይሆን በቀደሞው ከንቲባ ኩማ ድሪብሳ ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው " ብሎ ለማስተባበል ቢሞክርም:-
ማስረጃ እንዲያቀርብ ሲጠየቅ "እሺ " ካለ በኃላ በዚያው በመጥፋቱ ዜናው ከገፃችን ላይ ሳይነሳ ቀረ::
ያኔ በከንቲባ ታከለ ቢሮ ተጥርተው ቡና እየተጋበዙ በኔ ላይ የኩነኔ ማዕት ሲያወርዱ የነበሩት የቀድሞ የኢሳት ባልደረቦቼ አሁን ላይ የፓለቲካ ክርስትና የተነሱበት ፓርቲያቸው ኢዜማ ይህን መግለጫ ሲያወጣ ምን ይሉ ይሆን?
ለማንኛውም ነገ "እለታዊ "ላይ ምን እንደሚሉ ለመስማት መፈለጌን ለመግለፅ ነው::
ይህ በመሆኑም ማየት ያቆምኩትን የኢሳት እለታዊ ፕሮግራም ለዚህ ብየ ለመስማት የግዴንም ቢሆን ከራሴ ጋር ቀጠሮ መያዜን ለቀድሞ የኢሳት ባልደረቦቼ አሳውቃለሁ::
ምናልባት ወኔ አግኝተው "እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል!! " ይሉ ይሆን?
ወይንስ አሁንም ሁሌም ባልደራስን እንደሚሉት ኢዜማን ደግሞ በስም አጥፊነት ይወነጅሉት ይሆን?
