Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40388
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኦሮማራ ኤሊቶች ፉክቻና የሺመልስ አብዲሳ መሻር፡ አቢይ ለኢዜማ የሰጠው መልስ፡ የዜጋና ዘውግ ፖለቲካ ሊፋቱ ነው !!!

Post by Horus » 02 Sep 2020, 23:00

የፖለቲካ ሃሁ፡

በስልጣን ላይና በስልጣን ዙሪያ ያሉ ፖለቲከኞች ሁሉ አንድ እና ተመሳሳይ ፍላጎት አላቸው ። ባህሪያችውን ሁሉ የሚያንቀሳቅሰው እና የሚገልጸው ይህ ፍላጎ ነው ። ይህ ገፊ ፍላጎት ምንድን ነው? ምንድን ናቸው?

1ኛ ስልጣን ወይም ሃይል፡ ማን ምን መስራት፣ ማን ምን ማድረግ እንዳለበት ፣ ማን ምን ማግኘት እንዳለበት መወሰን እና የማስፈጸም ሃይል ።

2ኛ ገንዘብ፣ መሬት፣ ሃብት፣ ጥቅማ ጥቅሞች ማካበት፡ ይህ የሃብት ፍላጎት ከሌሎች እስከ መቀማት እና ሌብነት ደርሷል ።

3ኛ ዝና፡ ገጽታ የስም መግነን የመታወቅ ፍላጎትና ጥማት

4ኛ ክብርን መሻት ። ይህ በስልጣን ዙሪያ ለሌለ ሰው ትንሽ ነገር ይመስላል ። ግን ስልጣን ና ክብር አብረው ካልሄዱ ትልቅ የትግል፣ የመሻሻርና እስከ መጋደል የሚያደርስ ጉዳይ ነው።

ሳይንሱ ይህ ነው ። ፖለቲከኛ ሁሉ የሚናውዘው እነዚህ 4 ነገሮች ወይም ካራቱ አንድ ሁለቱን ለማግኘት ነው።

ስለሆነም የኦሮሞና አማራ ፖለቲካ ኤሊቶች በምንም አይነት በጥቅም አንድ ሊሆኑ ወይም ፍጹም ስምምነት ሊያገኙ አይችሉም። በማንኝውም ሰር ኣት ውስጥ ለሁሉም እኩል የሚዳረስ ስልጣን፣ ሃብት፣ ዝና ወይም ክብር የለም ። ለምሳሌ ጠ/ሚ አንድ ቦታ ብቻ ነው ፣ ወዘተ

በሳይንስ ላይ የተመሰረተ ሃሳብ መስጠት ለምትሹ ፖለቲከኞችን ሁሉ በዚህ መለኪያ ለኩ እላለሁ ።


አሁን ኢትዮጵያን የሚያደነቁሩት 100 በላይ ፓርቲ መሪ ነን ባይ ፖለቲከኞችን ሁሉ የሚነዳ ፍላጎት፣ ሞቲቬሽን ይህ ነው።

አቢይ የዜጋ ፖለቲካን ወደ ጎሳ ፖለቲካ ሊደምር ካሰበ ፍጹም ተሳስቷል ማለት ነው



Last edited by Horus on 03 Sep 2020, 00:58, edited 2 times in total.


Post Reply