Why?
Posted: 30 Aug 2020, 15:53
Do agames at last accept Welqayt is gone? Why weyane destroyed 300 hectare crops with poison? That sound like something.
Amhara Mass Media Agency
ህወሃት እያደረሰ ያለውን ግድያ፣ ማሳደድና ዘር ማጥፋት የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ እንዲያስቆም ኮሚቴው ጥሪ አቀረበ፡፡
ከ300 ሄክታር በላይ በሰሊጥ የተሸፈነ የአርሶ አደሮች ማሳ በህወሃት ትዕዛዝ በመርዝ መውደሙን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
ህወሃት በወልቃይት፣ ጠገዴ እና አካቢው እያራመደው ባለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትና ማን አለብኝነት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅርባችኋል በሚል ሰበብ ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ሁሉ አርሶ አደሮችን በኢኮኖሚ የማሽመድመድ እና ለስደት የመዳረግ እስትራቴጂውን ገፍቶበታል ብሏል የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴው።
በወልቃይት ጠገዴ መሬት አፅሚ ሃርማዝ ቀበሌ ልዩ ስሙ ስየ በተባለ ቦታ ላይ ነሐሴ 19/ 2012 ዓ.ም የ30 አርሶ አደሮች የሰሊጥ ማሳ በማላታይን መርዝ እንዲወድም መደረጉንም አንድ ማሳያ አድርጎ ጠቅሷል፡፡
አርሶ አደሮቹ በተማጽኖ ቢጠይቁም 'ከመንግስት ተልከናል' ባሉ ግለሰቦች አማካኝነት በትግራይ የልዩ ሃይል አባላት ጥበቃ እየተደረገላቸው ማሳዎቹን ማላታይን መርዝ በመርጨት አውድመዋል።
ምን አጠፋን ? ለሚለው የገበሬዎቹ ጥያቄ "አማራዎች እዚህ ምን አላችሁ? ይህ የትግራይ መሬት ነው" የሚል ምላሽ ብቻ እንደተሰጣቸው ኮሚቴው ገልጿል።
ሰሊጥ በማላታይን ከተረጨ ሙሉ ለሙሉ እድገቱም ሆነ ምርታማነቱ እንደሚገታም አርሶ አደሮቹ አረጋግጠዋል፡፡ የወደመው ሰሊጥ የአበባ ዕድሜውን አገባድዶ ፍሬ በማፍራት ላይ የነበረ ነው።
በ300 ሄክታር ላይ የወደመው ሰሊጥ የ30 ቤተሰብ አመታዊ የገቢ ምንጭ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ መውደሙ ከዘር ማጥፋት የማይተናነስ በደል እና ጭካኔ መሆኑን የወልቃይት ጠገዴ የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አስታውቋል፡፡
ህወሃት የምርጫ ድራማውን እውነት ለማስመሰል ከአካባቢው ውጭ ያሉ ወጣቶችን በማሰማራት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ምርጫውን እንደሚደግፍ የሚያሳይ የሀሰት ሰልፍ እያደረገ መሆኑም ለነዋሪዎቹ "በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ" ሆኗል ያለው ኮሚቴው ድርጊቱ የሕዝብን መብት ከመጣስ ባለፈ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽ እድል የሚሰጥ በመሆኑ መንግስት የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብሏል፡፡
ህወሃት በአካባቢው እያደረሰ ያለውን ግድያ፣ ማሳደድና ዘር ማጥፋት የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ እንዲያስቆምም ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል፡፡
የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅትም በትህነግ ህወሃት በተለይ ምርጫን ሰበብ በማድረግ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምትና በራያ እያደረሰ ያለውን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰትና አፈና በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
ዘጋቢ፦ ደሳለኝ ክንዱ