Page 1 of 1
መስቀል 1 ወር ቀረው! የጉራጌ መስቀል የክርስትናም የስልምናም ሳይሆን የመላ ጉራጌ ጥንታዊ በዓል ነው !!!
Posted: 23 Aug 2020, 03:04
by Horus
ዛሬ ኦርቶዶክስ ፍልሰታ ነው ።
ነሃሴ (ናሴ) 15 በጉራጌ የምጅር (የደመራ) መትከያ ቀን ነው።
አሁን ሰዉ ሁሉ ራስ ወዳድ ሆነ እንጂ እኛ ልጆች ሆነን በምጅር መትከያ ቀን ማንም ሰው ዛፉ ለደመራ (ለምጅር) ቢቆረጥ አይከለክልም። ልጆችም የማንም ዛፍ ለምጅር ቢቆርጡ ፈቃድ አይጠይቁም።
ዛፉን (ቀጥ ያሉ ወጣት ዛፎችን) ቆርጠን ቆዳውን ከላጥን (እንዲደርቅ) በኋላ የደመራው የምጅሩ አጥንት ተሸካሚ የሆኑትን የምጅሩ እስኬሌተን በትልቅ ሆያ ሆዬ ጭፈራ የምንተክለው ዛሬ ነው፣ ናሴ 15!
ከዛሬ እስከ መስቀል 1 ወር አለ ። በመሃሉ ያው የዛሬ 2 ሳምንት 'አክራሚ' እንቁጣጣሽ አለ ። ከዚያም ካክራሚ ማግስት እስከ ደንጌሳት የሴቶች ፤ 'ኢምር ኢምር' የብርሃን ዘፈን በምጅሩ ዙሪያ ማታ ማታ አለ ... እያለ ለሴቶቹ መስቀል፣ ለልጆቹ መስቀል፣ ለታላቁ መስቀል፣ ላዳብና፣ ላዳምና እንደርሳለን።
ማለትም ለቅድመ ኦርቶዶክስ ጉራጌ የዘመን መለወጫው አዲስ አመት በዓል የ15 ቀን ፌስታ ነበር ፤ ከአክራሚ (እንቁጣጣሽ) እስከ መስቀል !!!
በጉራጌ ቋንቋ አክራሚ (ወይም የኬርማይ) ማለት ቅዱስ ቀን ማለት ነው። የቅዱስ ዮሃንስ ወይም የእንቁጣጣሽ እለት ቅዱስ ቀን እንለዋለን ።
Re: መስቀል 1 ወር ቀረው!
Posted: 23 Aug 2020, 03:25
by Horus
ሰዎች ልብ የማይሉት ነገር መስቀል ለጉራጌ ሕዝብ የክርስትናም የእስልምናም ሃይምኖታዊ በዓል አይደለም። መስቀል የሁሉም ጉራጌ ኦርቶዶክስ፣ ሙስሊም፣ ኦሪታዊ ሁሉ ያዲስ አመት እጅግ ግዙፍ በዓል፣ ባህል፣ ካልቸርና ሕዝባዊ ማንነት መገለቻ ደስታ ሁሉ ደስታ፣ የበዕላት ሁሉ በዓል ነው !!! ወደ ፊት በመስቀልና በገና መሃል ያለውን የእምነትና ባህላዊ ትስስር የምለውን እላለሁ !!
Re: መስቀል 1 ወር ቀረው! የጉራጌ መስቀል የክርስትናም የስልምናም ሳይሆን የመላ ጉራጌ ጥንታዊ በዓል ነው !!!
Posted: 23 Aug 2020, 03:55
by Horus
እዚህ ውስጥ ሴቶች በቡድን የሚሰሩት የሴቶች ዉሳቻ ይባላል፣ የሴቶች ደቦ ማለት ነው። ለምሳሌ የልጆች ከብት ማገድ ደቦ ዎጀ ይባላል። ሌላው ቀርቶ የበዕል እንጨት ፈለጣ ፣ ጌሾ ወቀታ ሁሉ በደቦ ነው የሚሰራው ።
Re: መስቀል 1 ወር ቀረው! የጉራጌ መስቀል የክርስትናም የስልምናም ሳይሆን የመላ ጉራጌ ጥንታዊ በዓል ነው !!!
Posted: 23 Aug 2020, 04:41
by Degnet
Horus wrote: ↑23 Aug 2020, 03:04
ዛሬ ኦርቶዶክስ ፍልሰታ ነው ።
ነሃሴ (ናሴ) 15 በጉራጌ የምጅር (የደመራ) መትከያ ቀን ነው።
አሁን ሰዉ ሁሉ ራስ ወዳድ ሆነ እንጂ እኛ ልጆች ሆነን በምጅር መትከያ ቀን ማንም ሰው ዛፉ ለደመራ (ለምጅር) ቢቆረጥ አይከለክልም። ልጆችም የማንም ዛፍ ለምጅር ቢቆርጡ ፈቃድ አይጠይቁም።
ዛፉን (ቀጥ ያሉ ወጣት ዛፎችን) ቆርጠን ቆዳውን ከላጥን (እንዲደርቅ) በኋላ የደመራው የምጅሩ አጥንት ተሸካሚ የሆኑትን የምጅሩ እስኬሌተን በትልቅ ሆያ ሆዬ ጭፈራ የምንተክለው ዛሬ ነው፣ ናሴ 15!
ከዛሬ እስከ መስቀል 1 ወር አለ ። በመሃሉ ያው የዛሬ 2 ሳምንት 'አክራሚ' እንቁጣጣሽ አለ ። ከዚያም ካክራሚ ማግስት እስከ ደንጌሳት የሴቶች ፤ 'ኢምር ኢምር' የብርሃን ዘፈን በምጅሩ ዙሪያ ማታ ማታ አለ ... እያለ ለሴቶቹ መስቀል፣ ለልጆቹ መስቀል፣ ለታላቁ መስቀል፣ ላዳብና፣ ላዳምና እንደርሳለን።
ማለትም ለቅድመ ኦርቶዶክስ ጉራጌ የዘመን መለወጫው አዲስ አመት በዓል የ15 ቀን ፌስታ ነበር ፤ ከአክራሚ (እንቁጣጣሽ) እስከ መስቀል !!!
በጉራጌ ቋንቋ አክራሚ (ወይም የኬርማይ) ማለት ቅዱስ ቀን ማለት ነው። የቅዱስ ዮሃንስ ወይም የእንቁጣጣሽ እለት ቅዱስ ቀን እንለዋለን ።
Yetem yekebral,Mekelle lemsale gen Merkato slemawkew des yelu neber(ye lijnet gize)
Re: መስቀል 1 ወር ቀረው! የጉራጌ መስቀል የክርስትናም የስልምናም ሳይሆን የመላ ጉራጌ ጥንታዊ በዓል ነው !!!
Posted: 25 Aug 2020, 01:32
by Horus
7 ጎጎት ዶቢ እነ መሃል አምባ፣ እነኬላ እነሱተን እነኑረና እነ ኧሽከዲየ
Re: መስቀል 1 ወር ቀረው! የጉራጌ መስቀል የክርስትናም የስልምናም ሳይሆን የመላ ጉራጌ ጥንታዊ በዓል ነው !!!
Posted: 25 Aug 2020, 04:09
by Horus
እጅግ ወብ ከሆኑት አዲስ ነጠላዎች አንዱ !!! ጉራጌ የካልቸር ባህር !! የጥበብ ፋፍሪካ !!!