Page 1 of 1

ኧረ ገዳሙ ገዳሙ!

Posted: 20 Aug 2020, 11:10
by Meleket
“ንዘረባ ዘረባ የምጽኦ” ከምዚበሃል ብዛዕባ ገዳም አቡነ ዮሓንስ ኣብዚ ኣብ ቅርዓት መረጃ ኪዝረብን ኪሕተትን ካብሰማዕና ንአንፍና ነዚ ታሪኽ’ዶ ነዞም ጎረባብትናን አሕዋትናን ጆባእ ክንብለኩም።

ኤርትራ ውስጥ ባህረነጋሲ የተባሉ የባህር ሹሞች በነበሩበት በአክሱም ዘመን ወቅትኣቡነ ፍሬሚናጦስ በሓማሴን ምድር (በኤርትራ) ክርስትናን ሰበኩ። ይህም ከ325-372 ዓ.ም. ተፈጸመ። አቡነ ፍሬሚናጦስ 10 የሚሆኑ ኣብያተ ክርስትያናት በማነጽ ለስድስት የሓበሻ ልጆች በዱባሩባ አካባቢ፡ መዓረገ ክህነት ሰጧቸው። እነዚህም ስድስት የመጀመሪያ ሓበሻ ካህናትም ዘአማኑኤል፡ ማቴዎስ፡ ዑቅበእግዚእ፡ ስብሓትለኣብ፡ ኣሓዱ እግዚእና ተንስአክርስቶስ ይባሉ ነበር። በመቀጠልም አቡነ ፍሬሚናጦስ፡ ለአንድ ባህታዊ አቡነ እንበረም በሚል መጠሪያ የሰምሃር አካባቢ ሓዋርያዊ ወንጌል / ሰበካ ጉባኤ/ ጳጳስ በማድረግ ሾሙ። (እስተዛሬ ድረስም በዚሁ በምጥዋ አካባቢ እምበረሚ የምትባል ቀዬ እንዳለች ይታወቃል)።

መሪጌታ ብርሃነ ተስፋማርያም የኤርትራ ገዳማት ታሪክ በሚለው መጸሃፋቸው በገጽ 7፣ 28 እና 106 ላይ እንዳሰፈሩት፡ አቡነ ፍሬሚናጦስ ፡ በዚያን ወቅት አረማውያን የነበሩትን ዔዛናና ሳይዛና በመባል የሚታወቁትን የአክሱም ነገሥታት፡ ክርስትያን ለማድረግ ማለትም ለማጥመቅ ወደ ኤርትራ አመጧቸው። አብርሃና አጽብሃ በማለት ኤርትራ ውስጥ ድባሩባ አካባቢ “ምስላም” በተባለ ኮረብታ በማጥመቅ የወርቅ አክሊል በራሳቸው ላይ በመድፋት አነገሷቸው። “ምስላም” ማለትም ትርጓሜው መሾም ወይም ማሳመር ማለትን ያመለክታል። ይህ ታሪክ ኤርትራ ውስጥ ቴድረር በተባለ ቦታ በሚገኘው የአቡነ ዮሓንስ ቤተክርስትያን ውስጥ በሚገኝ ብራና ላይ ሰፍሮ ይገኛል።

ከአቡነ ፍሬሚናጦስ ቀጥለው፡ ኤርትራ ውስጥ የክርስትና ሃይማኖት የሰበኩ አቡነ ሊባኖስ መጣዕ የተባሉ ሲሆኑ ከ340 – 475 ዓ.ም. አካባቢ እንደነበሩ ይታወቃል። በብራና ላይ ሰፍሮ የሚገኘው ገድላቸው እንደሚገልጸውም ቀዳማይ ንጉስ ሰልአዶባ የተባለው የሮም ንጉሥ በነገሠበት ወቅት፡ ወደ ኤርትራ መጥተው መጀመርያ በአስገደ ባቕላ ሳሕል፡ ቀጥለው ደግሞ በባርካ በመዘዋወር ፡ ጉሕጨዓ በተባለው ወረዳ መንበራቸውን ተክለው ለ70 ዓመታት በመላው ሰራየና በአከለጉዛይ አብያተ ክርስትያናትንና ገዳማትን እንዳነጹ፡ ታቦት በመቅረጽም ክርስትናን እንደሰበኩ በሰፊው ተሰንዶ እናገኛለን።

አቡነ ሊባኖስ መጣዕ የነዋሪውን ቋንቋ ማለትም ግእዝን አጥንተውም መንፈሳዊ ጽሑፎችን ከግሪክኛ፡ ከዓረብኛ፡ ከአርማይስጥና ከዕብራይስጥ ቋንቋ ወደ ግእዝ የተረጎሙም ናቸው። “መጣዕ” የሚለው ቃልም “ማታይ” (ማቴዎስ) ከሚለው የዕብራይስጥ ቋንቋ የመጣ ይመስላል። የማቴዎስ ወንጌልን ወደ ግእዝ ስለተረጎሙ የተሰጣቸው ስያሜም ነው የሚሉ ሰዎችም አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ መጣዕ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ቋንቋ ችግኝ መትከል ማለትን ያሰማል።

ከአቡነ ሊባኖስ መጣዕ በኋላም ማለትም በ420 ዓ.ም. አካባቢ፡ በሰንሒት በሳህል በሰምሃርና በአከለጉዛይ አካባቢ ኣባ ዮሓኒ (ኣባ ሓኒ) የተባሉ ካህን ነበሩ። አባ ዮሓኒ ከተከሏቸው ገዳማት መካከልም የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡
1. ገዳም ደብረ ሲና ደብረ ምጥማቅ በሰንሒት
2. ገዳም ደብረ ሰማዕታት ሃገረ ናግራን በሳሕል
3. ገዳም ደብረ ሚካኤል በሳህል
4. ገዳም ቅድስት ሥላሴ በሳህል
5. ገዳም ደብረ ሰላም (ሳላ) (አቡነ ሰላማ) በሳህል
6. ገዳም አቡነ ሰላማ በጀንገሬን ሰንሒት
7. ገዳም ደብረ መዓር ቅድስት ማርያም በሳሕል
8. ገዳም ቅዱስ ጊዮርጊስ አባ ሓኒ በጽንዓደግለ አከለጉዛይ
9. ገዳም አቡነ ሰላም(ሰላማ) በዓረት አከለጉዛይ
10 ሌሎች በብዙ ቦታዎችም ኣባ ሓኒ በመባል የሚታወቁ ትንንሽና ትልልቅ ገዳሞችንና መካነ ባህታውያንን እንደሰሩም፡ ዜና ደብረሲና በሚባለው የጥንት መጸሓፍና ትግራይ ውስጥ በተንቤን የሚገኘው ገድላቸው የሰፈረበት ጽሁፍ ምስክር ነው።

ከዚህ በኇላም ማለትም ከአቡነ ሊባኖስ መጣዕ 700 ዓመታት ያህል እንደ ሰንሰለት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በአቡነ አውስጣቴዎስ ልጆች በሚል መጠሪያ የሚታወቁ 13 ገዳማት በኤርትራ ይገኛሉ። እነሱም፡
1. ደብረ ድማሕ፡ በቆላ ሰራየ የሚገኝና አቡነ መርቀሬዎስ የቆረቆሩት
2. ደብረ ከሳሔ ወይ ደግሞ ደብረማርያም፡ በቆሓይን ወረዳ የሚገኝና አቡነ አብሳዲ የቆረቆሩት
3. ደብረ ቢዘን፡ ከአስመራ ወደ ምጽዋ በሚወስደው መንገድ ዳርቻ የሚገኝ፡ አቡነ ፍሊጶስ የቆረቆሩት
4. ደብረ ጽጌ፡ በተኸላ ወረዳ የሚገኝና፡ አቡነ ዮናስ የቆረቆሩት
5. ደብረ ድሑሃን፡ በቆሓይን ወረዳ የአቡነ ዮናስ ሁለተኛ ገዳም
6. ደብረ ሳሕል፡ በዛይደከሎም ወረዳ የአቡነ ዮናስ ሶስተኛ ገዳም
7. ገዳም ደብረ ኮል፡ በመራጉዝ ወረዳ ሮማዊ አቡነ ብሩክ የቆረቆሩት
8. ደብረ ጥሉል፡ ከአስመራ ወደ መንደፈራ በሚወስደው መንገድ ዳርቻ የሚገኝና፡ አቡነ አብራንዮስ የቆረቆሩት
9. ደብረ ምእዋን፡ በእገላ ሓምስ ወረዳ የሚገኝና፡ አቡነ ብጹእ ኣምላክ የቆረቆሩት
10. ደብረ ቅድስት ሥላሴ በኮዳዱ የሚገኝ፡ በጽልማ ወረዳ የአቡነ ብጹእ ኣምላክ ሁለተኛ ገዳም
11. ደብረ ወግረ ስሔን፡ በቆሓይን ወረዳ የሚገኝና አቡነ እንድርያስ ዕፉን የቆረቆሩት
12. ደብረ ጽዮን ጉንደት፡ በዓይላ ጉንደት በተባለ ቦታ የሚገኝና በአቡነ አብሳዲ ተከታዮች የተቆረቆረ
13. ደብረ ማይሕይወት፡ በመረብ ወንዝ አካባቢ የሚገኝና አቡነ ቴድሮስ የቆረቆሩት ይጠቀሳሉ

የኤርትራ ገዳማት ታሪክ ከሚለው መጸሓፍ ቀንጭቤ በከፊል የጠቀስኩት ይህ ታሪክ፡ ከዘመነ አክሱም በፊት በምድረ አግዓዚ (ኤርትራ) ውስጥ፡ ምን ያህል ከፍተኛ የበሰለና በህግ ተገዝቶ የሚተዳደር ፈሪሓ እግዚኣብሔር የተላበሰ ሕዝብ ይኖር እንደነበረ እንረዳለን።

የክርስትና እምነት ኤርትራ ውስጥ ይህን ያህል ስር ሰዶ ነበር ማለት ነው። በዚያን ወቅት በደቡብ ዓረብ ውስጥ አንድ ፊንሃስ የተባለ አይሁድ ንጉሥ በዓረብ ሃገር የነበሩ ክርስትያኖችን ይጨፈጭፍ ነበር። ቅዱስ ኂሩት የተባለ መንፈሳዊ መሪንና 36,000 ተከታዮቹንም በሃገረ ናግራን (ናጅራን) በሰማእትነት እንደተሰውም ይታወቃል። በዚህ የክርስትና እምነትና አማኞች ፈታኝና ወጣሪ ወቅትም፡ የቁስጥንጥንያ የኢየሩሳሌም ጳጳሳት በአክሱም ነግሠው ወደነበሩት ወደ አጤ ካሌብ መልእክት በመላክ፡ የዓረብ ሃገር ክርስትያኖችን አጤዉ እንዲረዱ ተማጠኗቸው።

የዓረብ ታሪክ ውስጥ፡ ዘመነ-ዝሆን በመባል በሚታወቀው ግዜም ዝሆኖችን አሰልጥነው ለጦርነት ይጠቀሙባቸው ነበር። ሕርጊጎ የሚለው ቃል ዝሆን ማለትን ያመለክታል (በሳሆ ቋንቋ ደኾኖ) ይባላል። እነኝህ የዓረብ ሃገር ክርስትያኖች ታላቅ ፈተና ላይ በነበሩበት ወቅትም፡ በ525 ዓ.ም. በአዱሊስ ወደብ በኩል 120 የሚሆኑ ስንቅንና ትጥቅን የያዙ ዝሆኖች የሚገኙባቸ ሠራዊት ለውጊያና ክርስትያኖችን ለመታደግ ወደ ዓረብ ሃገር አመሩ። ካርነሽም በተባለው ወረዳ መስፍንቶ በተባለው ቀዬ ተወላጅ የነበረው ኤርትራዊው ባሕረነጋሲ አብረሃምም ሰራዊቱን በመምራት ፊንሃስ የተባለውን የአይሁድ ንጉሥ ለመዋጋት ወደ ደቡብ ዓረብ አመራ። ባሕረነጋሲ አብረሃምን የዓረብ ጸሓፊዎች ንጉሥ አብረሃም በማለት ይጠቅሱታል ።

የባሕረነጋሲ አብረሃም ሰራዊት ብቻ 70,00 ይደርስ እንደነበረም ይነገራል። ከዚህም የክርስትና እምነት ኤርትራ ውስጥ ምን ያህል ስር የሰደደ እንደነበረ እንረዳለን። በተጨማሪም የሕዝቡ መበቆል ወይ ምንጭ ደቡባዊ ዓረብ መሆኑን በግምት በማስገባት፣ በዚያን ወቅት ምን ያህል ጠንካራ ግንኙነት እንደነበረ ለመረዳትም ይቻላል።

አጤ ካሌብም በበኩላቸው ከቦታቸው 30,000 የሚሆን ሠራዊት ይዘው እንደተነሱና ጦርነቱንም ድም ነስተው እንደተመለሱ የናግራን ሰማእታት ገድል ላይ ተጽፎና ሰፍሮ ይገኛል። ከዚህ ፍጻሜም በኃላም፡ አጤ ካሌብ መንነው ወደ ገዳም እንደገቡ ይነገራል። ሠራዊቱና ንጉሡ እንደተመለሱም በሓባብ ምድር ማለትም በኤርትራ ሰሜናዊ ጫፍ በኩል፣ ሃገር በተባለው ተራራ ላይ፡ ሃገረ ናግራን ላይ በተደረገው ጦርነት በሰማእትነት ለተሰውት 32,000 ሰማኣታት ዝኽር ወይ መታሰቢያ የሚሆን ቤተክርስትያን አሰሩ። ለዚህም ምስክር የሚሆን ቅዱስ ያሬድ “ኦ ሃገረ ናግራን ሃገረ ቅዱሳን” በማለት ተቀኝቶላታል። 44 የሚሆኑ ቤተክርስትያኖችም ታንጸውባት ነበርም ይባላል።

በሚካኤል ሓሳማ በተጻፈው የኤርትራ ታሪክ በሚባልው መጥሃፍ ገጥ 16-17 ላይ እንደሰፈረውና የሓባብ ነዋሪዎች እንደሚተርኩት፡ በምድራቸው እስከ የጣሊያን ግዛት ሰዓት ድረስ ምንም ኣይነት ተተናኳይ አውሬ አልነበሩም። ከተወሰነ ግዜያት ወዲህ ግን፡ ሰውና እንስሳትን የሚተናኮሉ አውሬዎች መታየት ጀመሩ ይላሉ። ድሮ በጣም ጫካ ስለነበረም ግመሎች ወደ ሃገረ ናግራን ሊወጡ አይችሉም ነበር። አሁን ግን ወጥተውስ እዛ በገፍ እናገኛቸዋለን . . . ። ከረጅም ግዜ በፊት አንድ ሸኽ “እንዳ እየሱስ” በመባል ይታወቅ የነበረውን ቦታ “መስጅድ ኢሳ” በማለት ሰየሙት። (ይህ ቅዱስ ቦታ በነጻነት የትጥቅ ትግል ግዜ የኤርትራ ህዝብ የታጋይ ልጆቹን ድምጽና ቃል የሚያደምትበትና “የሰፊው የኤርትራ ሕዝብ ድምጽ” በመባል የሚታወቀው የሬዲዮ ጣቢያ የሚገኝበት ቦታ ነበር። በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ድርጅቶችም ትምህርት የሚቀስሙበትና ድምጻቸውንም የሚያስተጋቡበት ሃገር የተባለው ተራራ ነበር።)

በተመሳሳይ መልኩም፡ ባሕረነጋሲ አብረሃም ንጉሥ ተብሎ ተሰይሞ በደቡብ ዓረብ ማስተዳደር እንደጀመረ፡ የሃገረ ናግራን ታሪክ ይገልጽልናል። ከኒሰት አልሓበሽ (የሓበሻ ቤተክርስትያን)፡ አርድ አልሓበሽ (የሓበሻ ምድር) ጀበል እልሓበሽ (የሓበሻ ተራራ) የሚሉ የመጠሪያ ስሞችም እስከ አሁን ድረስ በደቡብ ዓረብ ይገኛሉ። በዚያን ሰዓት የተሰሩ ሃውልቶችና ግድቦችም ሳይቀሩ እስከ አሁን ድረስ ይገኛሉ። ስለሆነም የመን ውስጥ ነፍጠኛ ሆነው የሄዱና እዚያው የተቀመጡ ከ3-4 ሚሊየን የሚሆኑ ትውልዳቸው ከሓበሻና ከባሕረነጋሲ አብረሃም ዝርያ እንደሆኑ የሚያምኑ ዜጎች ይገኛሉ። (ከዚህ በተጨማሪም ከባሕረነጋሲ አብረሃም በፊትም እንጋንያ የተባለ ሌላ ኤርትራዊ ወደ ዓረብ ሃገር ሄዶ ይገዛ እንደነበረ በአንዳንድ ጡሁፎች ላይ ተጠቅሶ እንደሚገኝ ይነገራል።)

በሌላ በኩልም አፈ ታሪክ/ ትውፊት እንደሚነግረን በንግዱ በኩልም ቢሆን ወደ ትግራይ ይሁን ወደ ሌሎች የአክሱም ግዛቶች ያልፉ የነበሩ ንግዳዊ እቃዎች ኤርትራ ውስጥ ቀረጥ ይከፍሉ እንደነበረ እናውቃለን። ቀረጥ ይከፈልባቸው ከነበሩት ቦታዎች መካከልም የሓዳስ ወንዝ፣ ቀይሕ ኮር፣ ሓቒቕ (ዓጊግ)፣ ሕጻጽና ሌሎችም በብዛት ይጠቀሳሉ። በተለይም በሩባ ሓዳስ በኩል የነበረው የቀረጥ መቅረጫ ኬላ እስከ የአሉላ ጊዜ ድረስ እንደነበረ ይጠቀሳል።

የአብዛኛው የምድረ ሓበሻ የትውልድ ቦታና የስልጣኔው መሰረት፡ እላይ የተገለጸውን ሁሉ ግምት ውስጥ በማስገባት የኤርትራና የየመን ታሪክ ምን ያህል የተያያዘና የተሳሰረ እንደነበረ ለማወቅ ይቻላል። የኤርትራና የየመን ዝምድና ደግሞ የመረዳዳትና የወንድማማችነት እንጂ የዝርፊያና የወረራ ታሪክ አልነበረም። እንደዚህ ጽሁፍ ተራኪ እንደ አባ ፍስሓጽዮን እምነት “የኤርትራን ታሪክ በይበልጥ ለማወቅ መጀመሪያ የየመንን ጥንታዊ ቅርሶች ማጥናት እንደሚያስፈልግ ይገልጻል።” ታሪኩ እጅግ እንዳይረዝምብን እዚህ ላይ ቋጭተነዋል። :mrgreen:

ለማሳረጊያ ግን ይህችን በኤርትራዋ የወደብ ከተማ በምጽዋ የምትገኘውን በአፍሪካ አህጉር የመጀመሪያዋን መስጊድ ስእል እናጋራችሁ። :mrgreen:
ታሪኳን በተመለከተ ደግሞ አዋቂዎቿ እንዲያካፍሉን ስንጠይቅ በታላቅ አክብሮት ነው።
:mrgreen: