Page 1 of 1

አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 18 Aug 2020, 10:07
by Horus
አቢይ አህመድ ቀስ በቀስ መቆሚያ መሰረቱን ከጎሳ ካድሬዎች ወደ ክህሎታዊ ቴክኖክራቶች እያዞረ ነው !ኤቦ ያሰኛል የሚገርመው ነገር ግን አቢይ ይህን ነገር ለምን በ12 12 12 አውጀው የሚለው ነው!!

Re: አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 18 Aug 2020, 10:24
by Horus

Re: አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 18 Aug 2020, 10:48
by kolfe
Horus,
What is the difference between Takele and a corrrupted Adanech Abebee? abo atasiqen….

Re: አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 18 Aug 2020, 12:11
by Za-Ilmaknun
Adanech Abebe....the presumptive Mayor of Addis Ababa! The demographic change will be on a steroids! :mrgreen: A City that has never been allowed to be administered by one of its own. Talk about self administration :lol: :mrgreen:

Re: አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 18 Aug 2020, 14:25
by Horus
ኮልፌ፤
ምን ግዜም ቢሆን አንድን የስልጣን ቦታ አንተ አስካልያዝከው ድረስ በነገሩ ላይ ወስኝነት የለህም። ስለዚህ ባልያዝነው ስልጣን ላይ የኛን ፍላጎት የሚያስፈጽም የለም። ይህን አለማወቅ ትልቅ የዋህነት ነው። ታከለን የሾመው የኦሮሞ ፓርቲ ነው ።ታከለን ያነሳው የኦሮሞ ፓርቲ ነው። አዳነችንም እንዲሁ!

ትልቁ ጥያቄ ለምን ብለህ ጠይቅ? ለምንድን ነው በዚህ ሰዓት ታከለ የተነሳው? አዳነች ለምንድን ነው ካቃቤ ህጉ የተነሳቸው? እነዚህ ጥያቄዎች አስፈላጊ የሚሆኑት በሚከተለው ሎጂክ ምክኛት ነው።

አንደኛ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ፖለቲከኞች የሚያጣላቸው ወይም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር (1) ስልጣን፣ (2) ገንዘብ፣ (3) አማለካከት፣ ወይም (4) ማንነት/ዝና ነው ። ስለዚህ ታከለ ካቢይ ጋር ያለውን ችግር ከነዚህ 4 ነገሮች ታገኝዋለህ ። ያ ደሞ አቢይ ምን ላይ እንደ ቆመ፣ ምን ማድረግ እንዳለመ ይነግርሃል ። የታከለ መባረር ትልቅ ኢፎርሚውሽን ነው ለህዝቡ።

ሌላው ትልቁ ነገር የፖለቲካ ከረምቦላው ነው ። የፖለቲካ ዳይናሚክስ ልክ እንደ ክሮምቦላ ጠጠር ነው ። አንዱን ስትመታው ሁሉም ይነቃነቃል ። ይህ ሁሉ የምናየው ሹም ሽር በፒፒ ውስጥ ያለ መታመስ፣ የኦሮምው እልቂት፣ የነጃዋር መሸነፍ፣ አቢይ እያደረገ ያለው ጽዳት አካልና ሂደት ነው።

ልብ በል አዲስ አበባ የታከለ ከተማ አይደለችም፣ ያቢይ ከተማ ነች ፣ አዲሳባ የኢትዮጵያ እምብርት ነች ። ታከለ የተነሳው አዲስ አበባን አቢይ በፈልገው መንገድ ማስተዳደር ስላልቻለ ነው ። ነገ አዳነች ትምጣ፣ ከበደ ይምጣ የሚሆነው ያ ነው።

ስለዚህ ጥያቄው አዳነች አቤቤ ምን ትፈልጋለች አይደለም ። አቢይ አህመድ አዲስ አበባን እንዴት ነው ማስተዳደር የሚፈልገው የሚለው ነው ። ዛሬ አዲስ አበባ በፒፒ ስር ነው ያለው ። ፒፒ ደም ኦሮሞ ነው ሚነዳው። ስለዚህ አዲሳባ ራሱን እንዲገዛ መታገል ነው የህዝቡን ፍላጎት የሚያነግሰው ። በፒፒ ውስጥ ያለው ፍትጊያ ግን ለህዝቡ ትግል ግብዓትነት አለው፣ ፖለቲከኛ ከሆንክ ማለት ነው።

እስቲ ለማንኛውም ኢዜማ ይፋ የሚያደርገውን የመሬት ወረራ ከዚህ ጋር እንዴት እንደ ሚያያዝ ለማየት ያብቃን ። በእኔ ግምት በትክክል የተያያዘ ይምሰለኛል። ያዳነች መነሳት ግን ከነጃዋር ጋር ባላት የድሮ ቅርበት ይመስለኛል ። ሙሉ ቀን የምንሠማው የዚያ ገዳይ ጃዋር ድራማ ነው። አቢይ ቋቅ ያለው ይምስለኛል ። ስለዚህ በዚህ አንገብጋቢ 10 ሺ ሰዎች ክስ ወቅት የሷ መነሳት ሹም ሽር እንጂ ሹም ሹመት አይደለም ።

ለጊዜው ማባበያ እንጅ አዳነቸው ዘላቂ ከንቲባ አትሆንም ። አንድ አመት ብትቆይ ነው፣ እስከ ምርጫው ።

Re: አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 18 Aug 2020, 15:14
by Horus
ኢትዮ360ች ግን ሺመልስ አብዲሳ ባሸናፊነት ወጥቷል የሚል ነው እይታቸው ። በኦሮሞ ፒፒ ውስጥ ያለው የስልጣን ትግል የሚወሰነው ይሆናል ። በዚህ ሁሉ ላይ አንድ አመለከከት የነኢትዮ360 ስለሆነ እነሆ


Re: አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 18 Aug 2020, 15:31
by Horus
ታከለ የተነሳው የመሬት ውረራውን ለመሽፈን እና እሱን ለማዳን ይሆን?


Re: አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 18 Aug 2020, 16:12
by Horus
ታከለ ተሾመ ወይስ ተሻረ?


Re: አስታ ላቪስታ ታከለ ኡማ !! የሚቀጥለው ሺመልስ አብዲሳ ነው

Posted: 24 Aug 2020, 13:31
by Horus
ፒፒ ፓርቲ ግምገማ ተቀምጧል። በዚህ ግምገማ ሺመልስ አብዲሳን አለማውረድ ማለት የኦሮማራ መፍረስ ማለት ነው ። ያ ደሞ ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነው ። ኢትዮጵያ ከማንኝውም የጎሳ ጥርቃሞ አምባገነንነት መላቀቅ አለባት ።