Page 1 of 1

የወልቃይት እና የጠገዴ ነዋሪዎች አቤቱታ

Posted: 18 Aug 2020, 08:36
by Zmeselo


ዜና
የወልቃይት እና የጠገዴ ነዋሪዎች አቤቱታ

ነሐሴ 17, 2020

አስቴር ምስጋናው

https://amharic.voanews.com/a/wolkait-t ... 47010.html


ፎቶ ፋይል

ባህር ዳር — የትግራይ ክልል መንግሥት ምርጫ አደርጋለሁ በሚል ሰበብ ወከባና እንግልት እየፈፀሙብን ነው ሲሉ የወልቃይት እና የጠገዴ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ክልሉ ዕድሚያቸው ከ15 እስከ 17 ያሉ ህፃናትን በግዳጅ ለጦርነት እየመለመለ ጎልማሶችን ደግሞ ለሰራዊቱ ድጋፍ የሚሆን ገንዘብና እህል አምጡ እያለ እንደሚያስጨንቅም አስታውቀዋል። የፌዴራል መንግሥቱን እንዲደርስላቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ብልፅግና ፓርቲም የፌዴራል መንግሥቱ በወልቃይት ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም ጣልቃ መግባት እንዳለበት አሳስቧል። የትግራይ ክልል መንግሥት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው ምላሽ እየተፈፀመ ነው የተባለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስተባብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

https://amharic.voanews.com/a/wolkait-t ... 47083.html