Re: ዎያኔ በጉርጌ ሕዝብ ላይ የሰራው ለዘላለም የማይፋቀው ታሪካዊ ግፍ
ጉራጌ ነጻ ሕዝብ ነው፤ አቢይ ተቀበል !! በቃ !!!
አቢይ አህመድ እንደ ማንኛውን የፖለቲካ መሪ የመጀመሪያ አላማው ስልጣን መያዝ ፣ ቀጥሎ ስልጣኑን ላለመነጠቅ መታገል፣ ቀጥሎ ስልጣኑን በመጠቀም ባገር ሃብትና እድገት ላይ ሃይሉ፣ ቁጥጥሩን እና ተጸዕኖውን መጫን ነው። ይህ የእያንዳንዱ መሪ ሆነ ፖለቲከኛ ሆነ ዲክታቶር መሻትና ተግባር ነው። አቢይ ከዚህ ውጭ አይደለም።
ግን አቢይ በጎሳ ፖለቲካና በጎሳ ክልሎች ላይ እስከ ቆመና አወዛጋቢው የጎሳ ፌዴሬሽን አለቃ እስከ ሆነ ድረስ ዲክታቶር ሳይሆን ጠንካራ አገራዊ መሪ እንኳ ሊሆን አይችልም። ባ10 ክልል በተከፋፈለች ኢትዮጵያ 10 የክልል ፕሬዚዳንቶች ባሉበት፣ አስሩም ክልሎች 10 የተለያዩ የፖሊስ፣ ሚሊሺያ፣ ልዩ ጦር ባቆሙባት ኢትዮጵያ አንድ የኢትዮጵያ ዲክታቶር ሊነሳና ሊቆም አይችልም። ያ ሞዴል ቅዠት ነው። ያ የመሳፍንቶች ሞዴል ነው !!!
ዲክታቶር ማለት አንዲት በተዋሃደች አገር ውስጥ ባሉትን ጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን ተደግፎ፣ በጥቂት የጦር መሪ መኮንኖንች ተደግፎ ፣ እነዚህን ጥቂጥ ጠባብ የድጋፍ መሰረትን በስልጣናን በሃብት በመደለል የነሱን ድጋፍ አረጋግጦ፣ ያገር ኢኮኖሚ በመቆጣጠር በስልጣን ላይ የሜሰነብት መሪ መንግስት ማለት ነው።
ይህ በኢትዮጵያ አይሆንም። በኢትዮጵያ ያለው ሞዴል የመሳፍንቶች ሞዴል ነው ። 10 ወይም ወደፊት እስከ 60። 80 የሚደርሱን ትናንሽ ግዛቶች አለቃ የክልል እና የዞን ፕሬዚዳንት ወይም መሳፍንት ያሉበትና እርስ በርሳቸው ትብብርና መቀናጆ በመለዋወጥ የሃይል ሚዛናንና አሰላለፍ የሚጫወቱባት አገር ነው።
ዛሬ ያቢይ ወንበር ደጋፊ አማራ ነው። አቢይ ባማራ ካልተደገፈ ስለሚወድቅ ። ግን የኦሮሞ ክልል አላማና ያማራ ክልል አላማ ምንጊዜም ተቃራኒ ናቸው። አቢይ ዲክታቶር እንዳይሆን የሚገታው አማራ ነው። ይህ ለሌላም ክልል ይሰራል። አማራ አቢይን በመደገፍ የኦሮም ሄጂሞኒ እንዲሰፍን አይፈቅድም፤ ደቡብም እንዲሁ !!
ደቡብ አቢይ አህመድ ዲክትቶር እንዳይሆን ከሚገቱት አይሎች አንዱ ነው። አቢይ ወደ ስልጣን እንዲወጣ ቁልፍ ድምጽ ደቡብ ነበር። ወደፊትም አንድ የኢትዮጵያ ዲክታቶ ያለ በቡብ ድጋፍ ዲክታቶር ሊሆን አይችልም። እንዲያውም አቢይ አባዱላን እንደ አገረ ገዥ ደቡብ መላኩ ታላቅ ቁጣን ቀስቅሷል።
ስለዚህ በምንም መደመር ወይ ሌላ የፖለቲካ ጥንቆላ በኢትዮጵያ አሃዳዊ፣ ኢጎሳዊ፣ ክልል አልባ አንድ ኢትዮጵያዊ አወቃቀርና መንግስት ሳይቆም ማንም የኢትዮጵያ ዲክታቶር መሆን አይችልም ። ካሻው አንድ የክልል ፕሬዚዳንት በራሱ ሕዝብ ላይ ዲክታቶር ሊሆን ይችላል ልክ እንደ አብዲ ኢሌ ማለት ነው።
ስለዚህ አቢይ እነ አባዱላን ወዘተ ደቡብ እየላከ ጭቃሹም፣ ምስለኔ፣ አገረ ገዥ ቁስል መቀስቀሱ ለራሱ ገጽታ መልክም ያልሆነ አሳፋሪ ስድብ ነው።
አቢይ ሙሉ ዲክታቶር እንኳ ባይሆን ጠንካራ አንድ የኢትዮጵያ መሪ፣ ፕሬዚዳንት ሊሆን የሚችልበት አንድ ብቻ ሞዴል ነው ያለው። እሱም ....
ክልሎችን ማፍረስ
ኢጎሳዊ ክፍለ አገሮች ማዋቀር
ጠንካራ ፕሬዚዳንታዊ ሕገ መንግስት በሕዝቡ ቅቡል ማድረግ
ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት (ኢትዮጵያዊ ሰራዊት ጭምር) ማቆም
በየከልሉ እንደ አሸን የፈሉት የዘመነ መሳፍንት ጀሌ ልዩ ጦር፣ ሚሊሺያ አፍርሶ ብሂራዊ ሰራዊት ጋር ማዋሃድና
ይህን በብሄር ስም የፈላው ባላባታዊ የክልል ግዛቶችን በማፍረስ ነው።
ይህን ለማድረግ አቢይ የኢትዮጵያ ድጋፍ አለው፣ ግን ለዚያ አይነት ቆራጥና ራዕያዊ እርምጃ ገና ብቁ ያልሆነ ገና ከራሱ የጎሳ አነሳስ ያልተላቀቀ መሪ ነው። ደሞ ግዜ ቆሞ አይጠብቀውም ።
ይህን ታሪካዊ ተልዕኦ እሱ ካልቻለው ሌላ ብልህ መሪ ተነስቶ ያደርገዋል ። ኢትዮጵያ በጎሳ ፖለቲካ አትቀጥልም። ይህ ሁሉም ያውቀዋል ። አማራጩ ...
ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ የሚገዛ ዲክታቶር ወይም ዴሞክራቲክ መሪ ነው ። ሁለቱም የጎሳ ሰርዐትን በማፍረስ ነው ያን የሚያደርጉት !!! የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚደግፈው ከነዚህ አንዱን ነው !!!