ሰላም ኢትዮጵያውያን ወገኖች እንዲሁም ኤርትራውያን ፤
መቼም ሰሞኑን የማይነገርና የማንሰማው የሴራ ቲዎሪ የለም ፤፤ ብዙ የሴራ ቲዎሪዎችን እየሰማን ነው ፤፤
አንዳንዶች ደግሞ ምንም ሊታመኑ የማይችሉ የሴራ ቲዎሪዎች ናቸው ፤፤ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የሃያሎም አርአያ አገዳደል ጉዳይ ነው ፤፤ ይቅርታ ወያኔዎች የወያኔን ማይም ታጋይ < ጀኔራል > ብሎ ለመጥራት ስለሚቀፈኝ እንጂ ሃያሎምን የጀኔራልነት ማዕረግ እንደሰጣ ች ሁት አውቃለሁ ፤፤ ወያኔ ወይም እነ መለስ ዜናዊ ብዙ የሴራ ግድያዎችን ፈጽመዋል ፤፤ ለምሳሌ ያህል የድሮ የድኅንነት ኃላፊው ክንፈ ገብረመድህን አገዳደል ደንበኛ የሴራ ግድያ ነበር ፤፤ የሃያሎም ግድያ ግን በወቅቱ ከተሰጠው የምስክርነት ቃል አንጻር በፍጹም ሴራ አይመስልም ፤፤ ልብ በሉ እኔ ዕድሜ ልኬን የወያኔ ዋና ተቃዋሚ ነኝ ፤፤ ይህ ማለት ወያኔን የመከላከልበት ምንም አይነት ፓለቲካዊ ምክንያት የለኝ ም ፤፤ ነገር ግ ን በዚህ ግድያ ዙሪያ በወቅቱ ሃያሎም ከተገደለበት ቡና ቤት አብሮ ይጠጣ የነበረው ፕሮፌሰር እንደሪያስ እሽቴ በቲቪ ቀርቦ ከሰጠው የምስክርነት ቃል አንጻር ይህ ግድያ ሃያሎም ባጠፋው ጥፋት የተገደለ መሆኑን ነው ፤፤ በወቅቱ አብሮት ይሁን ቡና ቤቱ ውስጥ ይጠጣ የነበረ ጀማል የሚባል ኤርትራዊ ነበር ፤፤ እንደ ፕሮፌሰር እንደሪያስ እሽቴ ቃል ሃያሎም ይህን ሰው በጥፊ ይመታዋል ፤፤ ሰውየው ማለትም ጀማል ደሙ ይፈላና መኪናው ውስጥ የነበረውን ማካሮ ሽጉጥ አው ጥ ቶ በሃያሎም አር አ ያ ላይ ያራግፍበታል ፤፤ አሞሞቱ በዚህ አይነት ሁኔጽ ሲሆን ገዳዩ ጀማል ግ ን እንዴት ብሎ ቅጣቱን እንዳገኘ የወያኔ ካንጋሮ ኮርት ስለሆነ < ውስጡን ለቄስ > እንደሚባለው ነው ፤፤ ታዲያ ከሰሞኑ ፈንቅሎች ወያኔን መታገላቸው ጥሩ ሆኖ እያለ እንደዚህ አይነት የማይመስል ሴራዎች መፈብረኩ አስፈላጊ አይመስለኝ ም ፤፤ ወያነና እነ መለስ ዜናዊ ብዙ የሴራ ግድያዎች ቢፈጽሙም ይኸኛው ግድያ ግን በሃያሎም ንቀትና ጥፋት የተፈጸመና ፤ ሃያሎም የተጎነጨው ጽዋ ሰው ሰውን ሲንቅ የሚያጋጥመው ግድያ ይመስለኛል ፤፤ እስኪ በዚህ ጉዳይ በተለይ ፕሮፌሰር እንደሪያስ እሽቴ በኢቲቪ ቀርቦ የሰጠው ምስክርነት ቪዲዮ ያላችሁ እውነትን ለማጥራት ተባበሩን ለማለት ነው ፤፤
-
- Member
- Posts: 494
- Joined: 27 Oct 2014, 15:59