የሸዒብ ፍዳ እና ጄኔራል መርዳሳ ሌሊሳ - ኤርትራ፣ 1980 (1988)!!!!! ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
Posted: 09 Aug 2020, 17:24
ከላይ በተጠቀሰው ዓመት በኤርትራ ምድር በደርግና በህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ህግሓኤ) መካከል ሲካሄድ የነበረው ጦርነት በባሕሪው ከስረ መሠረቱ ተቀይሮ ነበር። የደርግ መንግሥት "እፍኝ የማይሞሉ ወንበዴዎች" ሲላቸው የነበሩት የኤርትራ ነፃነት ሃይሎች አፍአበት ላይ ታላቁን ወታደራዊ ድል የተቀዳጁት በዚህ ዓመት በመጋቢት ወር ነበር። ይህ የአፍአበት ድል የኤርትራ ህዝብን ያስደሰተውን ያህል በደርጎች ዘንድ ታላቅ ሃፍረትና ቁጣን ቀስቅሷል። በተለይም በዲያስፖራ የሚገኙ ኤርትራዊያን በጦር ሜዳ የሚታገሉት የህግሓኤ ታጋዮች ያገኙትን ድል እያሞገሱ መጠነ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ መስራታቸው መንግሥቱ ሃይለማሪያምን ክፉኛ ነው ያስቆጣው።
ኮሎኔል መንግሥቱ በአፍአበት ላይ ሽንፈት ያቀመሳቸው የህግሓኤ ጦር በሶስት አቅጣጫ ወደ ስፍራው እንደደረሰ ሰምተዋል። ኤርትራዊያኑ የመጡበት አንደኛው አቅጣጫ ከአፍአበት በስተምሥራቅ ያለው ነው። የህግሓኤ ተዋጊዎች ከአፍአበት በስተሰሜንና ምዕራብ ያለውን ወታደራዊ ስፍራ ሁሉ ተቆጣጥረዋል። የምስራቁ ክልል ግን በእጃቸው አልገባም ነበር። በዚህ ክልል ከሚገኙት ከተሞች አንዷ "ሸዒብ" ትባላለች።
ኮሎኔል መንግሥት በኤርትራ ሽንፈት ሲገጥማቸው ብዙ ጊዜ ከወታደራዊ አዛዦቻቸው አንድ ሁለቱን በመረሸን ንዴታቸውን ይወጡ ነበር። በዚህኛው ወቅት ግን እንዲያ አላደረጉም። ከዚያ ይልቅ ሸዒብ በምትባለው ከተማ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ሰው እንዲደገል ነው ያዘዙት።
ትእዛዙን ለመፈጸም የተመረጠው ደግሞ ዛሬ እንደ ጀግና በጋዜጣና በሬድዮ የሚለፈልፈው ብርጋዴር ጄኔራል መርዳሳ ሌሊሳ ነው። ጄኔራል መርዳሳ የመንግሥቱ ሃይለማርያም የረጅም ጊዜ ወዳጅ ነው። በመሆኑም ትእዛዙን ተፈጻሚ ለማድረግ "ለምን?" አላለም።
የሸዒብ ህዝብ በታንክ ተደፍጥጦ እንዲገደል ነበር የተወሰነው። ከታንኮቹ ሮጦ ለማምለጥ የሚሞከረው ደግሞ በጥይት እንዲጨፈጨፍ ተወስኗል። ጄኔራል መርዳሳም በግንቦት ወር 1980 መግቢያ ላይ ዝርዝር እቅዱን ተቀብሎ ከሸዒብ በተወሰነ ርቀት ላይ ባለችው የሰለሙና መንደር ከትቷል።
ግንቦት 4/1980 (May 12/1988)
ጠዋት ነበር። ከሸዒብ ህዝብ ግማሹ ወደ ስራው ሄዷል። ግማሹም ለግብይት ወደ ሌሎች አነስተኛ ከተሞች ነጉዷል። በቤት ውስጥ የቀሩት በአብዛኛው አረጋዊያን፣ ህጻናት እና ሴቶች ነበሩ።
ታዲያ ረፋዱ ላይ ጄኔራል መርዳሳ ሌሊሳ አንድ ታንከኛ ሻለቃ ጦር እየመራ ወደ ሸዒብ መንደር ገባ። ሆኖም የመንደሩ ህዝብ ቁብ አልሰጠውም ነበር። ምክንያቱም አካባቢው ሁልጊዜ የጦር ሰራዊት የሚመላለስበት በመሆኑ አዲስ ነገር የሚፈጠር ስላልመሰለው ነው።
ይሁንና ወደ መንደሪቱ የገባው የደርግ ጦር በድምጽ ማጉያ "ሁላችሁም ከቤት ወጥታችሁ በገበያ ቦታው ተሰብሰቡ" የሚል ትእዛዝ ሰጠ። ታዲያ ህዝቡ በዚህን ጊዜም ጥርጣሬ አልገባውም። ምክንያቱም ወታደሮቹ በዚያ መንደር ሲመላለሱ ለህዝቡ የወባ መድሀኒት እና ውሃ ያድሉ ስለነበረ እና እርሱን ለማግኘት ስለጓጓ ነው። በመሆኑም አብዛኛው ህዝቡ ትእዛዙን ተቀብሎ ከቤቱ ወጣ። አንዳንዶች ግን ጥርጣሬ ገብቶአቸው ኖሮ በቤታቸው መቅረትን መረጡ።
የደርግ ወታደሮች የተሰበሰበውን ህዝብ ሜዳው ላይ አቁመውት በቤታቸው የተደበቁትን ለማምጣት ፍተሻ ጀመሩ። በዚህም የተወሰኑ ሰዎችን አገኙ። ታዲያ ይሄኔም ጥቂት ሰዎች ፈጣሪ ቀጣዩን ትርኢት በዐይን እማኝነት እንዲመሰክሩ መርጦአቸው ኖሮ በተለያዩ መደበቂያዎች ራሳቸውን ለመሰወር ቻሉ። ወታደሮቹ በፍተሻ የተገኙትን ሰዎች በሜዳ ላይ ከቆሙት ጋር ቀላቀሏቸው። በዚህ ሁኔታ የተሰበሰበው ህዝብ ተደምሮ ከአራት መቶ በለጠ። ህዝቡ የቆመበት ስፍራም በወታደሮች ተከበበ።
እነሆ የመጨረሻዋ ደቂቃ ደረሰች። አረመኔው ጄኔራል መርዳሳ ሌሊሳ ታንኮቹ በህዝቡ ላይ እንዲሄዱ ትእዛዝ ሰጠ። ከሃያ በላይ ታንኮች ምንም ዓይነት መሳሪያ ባልያዙት በእነዚያ ንጹሐን ላይ መረማመድ ጀመሩ። ከእርምጃው ለማምለጥ ሽሽት የጀመሩት ደግሞ ወታደሮቹ በሚከፍቱት የክላሽና የመትረየስ እሩምታ ተጨፈጨፉ። ሸዒብ በንጹሐን ዋይታና ጣር ተመላች። የሚስኪኖች ደም በዚያች ስፍራ እንደ ጎርፍ ፈሰሰ። የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ሰርተው የማያውቁት እነዚያ አቅመ ደካሞች ኤርትራዊ መሆናቸው ብቻ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው በጭካኔ ተረፈረፉ።
----
ጄኔራል መርዳሳ እጁን በእነዚያ ንጹሓን ደምና እንባ ከታጠበ በኋላም እብሪቱና ጭካኔው አልበረደለትም ነበር። የሟቾቹን ሬሳ መሬት አስቆፍሮ ከመቅበር ይልቅ በመንደሪቱ ውስጥ ባሉት የውሃ ጉድጓዶች ውስጥ መጨመርን ነው የመረጠው። ጄኔራሉ እንዲያ ሲያደርግ "ይህቺ ከተማ ከዚህ በኋላ ወና ሆናለች፣ ሰው አይኖርባትም" ማለቱ ነው።
ፈጣሪ ግን ሁሉንም ያያል። ይፈርዳልም። በዚያች ከተማ የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ጄኔራል መርዳሳ ከሚጠላቸው "ወንበዴዎች" ጆሮ ወዲያውኑ ነው የደረሰው። ለዚህም ሰበብ የሆኑት ከቤት የመውጣት ትእዛዙን ሳይቀበሉ በሰዋራ ስፍራ የተደበቁት ጥቂት ሰዎች ናቸው። እነዚያ ሰዎች ወታደሮቹ ከመንደሪቱ ሲሄዱ በውድቅት ጭለማ ተነስተው የህግሓኤ ቤዝ አምባ ወደ ነበረው የሳሕል አውራጃ ደረሱ። በዚያ ላገኟቸው የህግሓኤ ታጋዮችን በከተማቸው ላይ የደረሰውን ፍዳ ነገሯቸው።
የህግሓኤ ታጋዮች የወገኖቻቸውን መጨፍጨፍ ሲሰሙ ተላቀሱ። ከፍተኛ እልህና ቁጭትም ያዛቸው። አንዳንዶቹ "ዛሬውኑ ሸዒብን ነፃ ማውጣት አለብን" አሉ። የህግሓኤ አመራር ግን ታጋዮቹንና ከጭፍጨፋ የተረፉትን አረጋጓቸው።
ጥቂት ጊዜ እንዳለፈ ህግሓኤ (ሻዕቢያ) በሸዒብ-ሰለሙና ግንባር ያልተጠበቀ መብረቃዊ ጥቃት ከፈተ። የደርግ ሰራዊትን ከአካባቢው ጠራርጎ አስወጣ። ጭፍጨፋው የተፈጸመባትን የሸዒብ ከተማንም ተቆጣጠረ። በመንደሪቱ የተሰራውንም ወንጀል በቪድዮና በኦድዮ አስደግፎ ለዓለም ህዝብ አጋለጠ። መላው ኤርትራዊ ጭፍጨፋውን ሲሰማ በእጅጉ ተቆጣ። ለህግሓኤ የሚያደርገውንም ድጋፍ አጠናከረ። ኤርትራም የሸዒብ ጭፍጨፋ በተፈጸመ በሶስት ዓመቱ ነፃነቷን አረጋገጠች።
ሸዒብ ጨካኙ መርዳሳ ሌሊሳ እንደተመኘው ወና ሆና አልቀረችም። ከነፃነት በኋላ በድጋሚ ተገንብታለች። በዚያ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለሞቱት አራት መቶ ሰማእታትም በመንደሪቷ ጥግ ላይ ትልቅ የመታሰቢያ ሃውልት ተሰርቶላቸዋል።
ጄኔራል መርዳሳ ሌሊሳ እንዲህ ዓይነት ቆሻሻ ታሪክ የተሸከመ ሰው ነው። የኢትዮጵያ አንድነት ጠበቃ ነን የሚሉት ሃይሎች "ንጹህ የኦሮሞ ልጅ" እያሉ የሚያሞካሹት እንዲህ ዓይነቱን ግፈኛ ነው። ደግሞም ሰውዬው መርዳሳ ከመሆኑ ውጪ የኦሮሞ ስነ ልቦና የለውም። ከካሳዬ ጨመዳ ጋር ሆነው ለኦሮሞ መብት የሚታገሉትን ወጣቶች "ዘረኞች" እያሉ ከሚወርፉት ባለጌዎችም አንዱ እርሱ ነው።
ኦሮሙማ በመርዳሳ ሌሊሳ የተሰጠን ጭምብል ሳይሆን ብዙ የታገልንበትና የደማንበት አርማችን ነው። መርዳሳ ሌሊሳ እና ካሳዬ ጨመዳን ተገን እያደረጉ ኦሮሙማን ማጥፋትም አይቻልም።
በመጨረሻም
"ነፃነት በነፃ የለም" ይባላል። እውነት ነው። ለዚህም ምስክር የሚሆነው ከላይ የቀረበው የሸዒብ ጭፍጨፋ ታሪክ ነው። የሸዒብን ጭፍጨፋ እንደ ምሳሌ ያነሳነው የጄኔራል መርዳሳ ሌሊሳ አትርሱኝ ባይነት ስላስደነቀን ነው። ለምሳሌ በ1969 ጸሎት በምትባለው ትንሽዬ ከተማ አቅራቢያ ሻዕቢያ በደርግ ሰራዊት ላይ ከባድ ጉዳት በማድረሱ ብቻ በወቅቱ የኤርትራ አስተዳዳሪ የነበሩት ጄኔራል ጌታቸው ናደው ተናደው ለአስመራው አየር ሃይል ቤዝ አዛዥ "በጸሎት ላይ ሰው ሳይሆን የቆመ ዛፍ እንዳይታይ አድርገህ ጨፍጭፍልኝ" በማለት የመንደሪቱን ነዋሪ በአውሮፕላን ማስጨፍጨፋቸውን በወቅቱ የደርግ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ገስጥ ተጫኔ ጽፈዋል። በአስመራ፣ በአቆርዳት፣ በሃዝሃዝ፣ በከረን፣ በኤላበረድ፣ በምጽዋ፣ በአሰብ፣ በጊንዳዕ፣ በደቀምሐረ፣ በተሰነይ፣ በባሬንቱ ወዘተ ተመሳሳይ ጭፍጨፋዎች ተፈጽመዋል። ሆኖም ኤርትራዊያን ትግሉን አላቆሙትም።
የኤርትራ ህዝብ ነፃነቱን የተቀዳጀው እጅግ መራራ መስዋእትነት ከፍሎ ነው እንጂ በማንም ችሮታ አይደለም። ዛሬም ማንም እየተነሳ "ኤርትራን ያስገነጠላት ወያኔ ነው" ብሎ የውሸት ታሪክ ቢዘባርቅ አንቀበለውም። ሌሎች ጭቁን ህዝቦችም ነፃነታቸውን ሊቀዳጁ የሚችሉት በትግል እንጂ በችሮታ አይደለም። ነፃነት በነፃ የለም።