የኦነግ ዎያኔ ጎሬላ ጦርነት ቲኦሪ፣ እስትራተጂ ና ታክቲክ ምንድን ነው?
Posted: 08 Aug 2020, 01:58
ሆረስ እባላለሁ፣ የማኦን ቀይ መጽሃፍ ያነበብኩት 10ኛ ክፍል ሆኜ ነበር። ከዚያም ለብዙ አመታት የሩሲያን ሞዴል አጥንቻለሁ ፣ ቀጥሎም ልዩ ልዩ ያውሮፓ የከተማ ጎሬላ ውጊያ አጥንተናል። የቻይና ህዝባዊ ጦር አንዱ ከከተማ ወደ ገጠር ጦርነት አለ ። በዚህ ሞዴል የጎሬላው ጦር ገጠርን ነጻ አውጥቶ ከተማን ይከባል።
ሌላው የላቲን አሜሪካኑ የነ ሬጂስ ዲብሬ የከተማ ፎኮ ጎሬላ ጦርነት ነው ።
ሌሎችም ልዩ ልዩ የከተማ አመጽ ሞዴሎች አሉ ።
በመጨረሻም የግለሰብ ግድያ ታክቲክና ስልት አለ ።
የእኔ ጥያቄ የሸኔ ዎይኔ ጎሬላ አርሚ የሚከተለው ቲኦሪ እስትራተጂ እና ታክቲክ ምንድን ነው? ይህ ነው የዘመኑ ያልተማረ ሚዲያ የማያነሳው ጥያቄ !!!!