Page 1 of 1

በመቀሌዉ እሳት አደጋ ከ 520 በላይ ሱቆች ወደሙ

Posted: 07 Aug 2020, 11:30
by Abaymado
I think I haven't seen this news in this website, what happened? If I missed it and if it was posted, I will remove it. By the way, facebook is back today.


https://www.dw.com/am/%E1%89%A0%E1%88%9 ... JOl5z-DVps

Re: በመቀሌዉ እሳት አደጋ ከ 520 በላይ ሱቆች ወደሙ

Posted: 07 Aug 2020, 11:47
by tarik
Abaymado wrote:
07 Aug 2020, 11:30
I think I haven't seen this news in this website, what happened? If I missed it and if it was posted, I will remove it. By the way, facebook is back today.


https://www.dw.com/am/%E1%89%A0%E1%88%9 ... JOl5z-DVps
FACT: Terrorist-Tigray-Tplf did it 2 blame it on Eritrea and Abiy. Old tplf drama like they did it in Hawzen. !!! WEEY GUUD !!!:lol: :mrgreen:
በመቀሌዉ እሳት አደጋ ከ 520 በላይ ሱቆች ወደሙ
በመቀሌ ዓዲ-ሓቂ ተብሎ በሚታወቀዉ ትልቁ የገበያ ማእከል በደረሰ የእሳት አደጋ የወደሙት ሱቆች ቁጥር ከ520 እንደሚበልጡ የከተማዋ ፖሊስ ገለፀ፡፡ የእሳት አደጋው የደረሰው ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥብያ ሲሆን የአደጋው መነሻ በትክክል አለመታወቁ ተጠቅሷል፡፡


Feuer in Mekelle, Tigray (DW/M. Hailesilassie)
በመቀሌ ዓዲ-ሓቂ ተብሎ በሚታወቀዉ ትልቁ የገበያ ማእከል በደረሰ የእሳት አደጋ የወደሙት ሱቆች ቁጥር ከ520 እንደሚበልጡ የከተማዋ ፖሊስ ገለፀ፡፡ የእሳት አደጋው የደረሰው ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥብያ ሲሆን የአደጋው መነሻ በትክክል አለመታወቁ ተጠቅሷል፡፡ የእሳት አደጋ በተከሰተበት በመቀሌዉ ትልቅ የገበያ አዳራሽ ልብስና ጫማ መሸጫ፣ የጥቅል ጨርቆች ማከፋፈያ፣ የቤትና ቢሮ እቃዎች መሸጫ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉን ፖሊስ አረጋግጦአል። ንብረታቸው ከወደመባቸው ነጋዴዎች መካከል አቶ ሃይላይ ገብረስላሴ በቃጠሎው እስከ 800 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ማጣታቸው ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ውጭ የመቀለ ከተማ እሳት አደጋ መከላከል ኃይል ለግብር ከፋዩ የማይመጥንና ኃላፊነቱን ያልተወጣ ብለዉታል።
ቃጠሎ የደረሰበትን የገበያ ማእከል ከጎበኙ በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር አርአያ ግርማይ በበኩላቸዉ የከተማ አስተዳደሩና ህዝብ የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸን አመስግነዋል። በቃጠሎዉ ንብረታቸዉ የወደመባቸዉን በማቋቋም ተግባር ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራም የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ተናግረዋል።
በአደጋው በንብረትና ገንዘብ ላይ ከደረሰ ቃጠሎ ውጭ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ማረጋገጡን ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ ከስፍራዉ ዘግቦአል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ


አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ