Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Digital Weyane
Member+
Posts: 9843
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

ህጋዊው የትግራይ ክልል ም/ፕሬዚደንት ህወሃት በሰላም ስልጣን እንዲያስረክብ ጠየቁ

Post by Digital Weyane » 28 Jul 2020, 14:38

ህጋዊው የትግራይ ክልል ም/ፕሬዚደንት ህወሃት በሰላም ስልጣን እንዲያስረክብ ጠየቁ



Admin Ethiopia, Nebiyou Sihul, Tigray


በሰሎሞን አረጋዊ

አዲስ አበባ (ቲኤ) – ህጋዊው የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት ነብዩ ስሁል ጥያቄውን ያቀረቡት አራት የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት በህዝቡ ከባድ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ነው።

ምክትል ፕሬዚደንት ነብዩ ስሁል ህዝባችን በህወሓት ተስፋ በመቁረጡ ወደ ኃይል እርምጃ እየገባ መሆኑ እንዳሳሰባቸው ገልጸው ከዚህም የከፋ ነገር እና ቀውስ በክልሉ ሳይፈጠር ህወሃት በሰላም ስልጣን እንዲያስረክብ ጠይቀዋል።

አቶ ነብዩ ስሁል ህጋዊው የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው የተመረጡት ገዥው ፓርቲ ከመረጣቸው በኋላ ነው።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ አሰራር የክልል ገዥዎች ስልጣን የሚይዙት ገዥው ፓርቲ ከመረጣቸው በኋላ ነው በቀጥታ የክልልም ሆነ የአገር መሪ ምርጫ ኢትዮጵያ ውስጥ አይካሄድም።

ይህን አሰራር በመቀየር በቀጥታ ህዝብ ምርጫ አድርጎ መሪውን የሚመርጥበት ፕሬዝደንታዊ አሰራር እንዲኖር ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

https://timesofaxum.com/%e1%88%85%e1%8c ... %e1%8b%88/