በጌታቸው ረዳ!!
“ዓድዋ አኽሱም ሽረ ጹሩያት ተጋሩ
ራያ እንደርታ ተምቤን ጎረቤት አምሓሩ”
ማለትም
“ዓድዋ አኽሱም እና ሽሬ የጠሩ ትግሬዎች
ራያ እንደርታ ተምቤን ያማራ ጎረቤቶች “
ይህ ዘረኛ ግጥም ወያኔዎች በረሃ እያሉ በእረኞች በኩል እንዲዘፈን ካሰራጩት ዘፈን አንዱ ነው።
ወያኔ በእንደርታ ታጋዮች ላይ በአውራጃዊነት የተመሰረተ የማግለል ፖሊሲ ይከተል እንደነበር ከድርጅቱ የስለላ እና የሓለዋ ወያኔ (እስር ቤት) ዋና ሓላፊ ከነበረው ከአክሱማዊው ከብስራት አማረ አንደበት የተነገረን መረጃ እነሆ እንዲህ ይላል።
“በ1969-ዓ.ም.በድርጅቱ ተነሳስቶ የነበረው ቀውስ/ትርምስ (ሕንፍሽፍሽ) እያሉ የሚጠሩት የደቡብ ትግራይ ልጆች ገብሩን መሃል አድርገው ከሌሎች የዓድዋ እና የአክሱም ተወላጆች በማነጻጸር የሃላፊነት ቦታ (የደቡብ ሰው) ማለትም የእንደርታ ሰው በመሆኑ አልተሰጠውም። መለስ ዜናዊ(ዓድዋ)፣ አታኽልቲ ቀጸላ፣ ሸዊት ዳኘው (አክሱም) በመሆናቸው የማአከላዊ ኮሚቴ ውክልና ተሰጥቷቸዋል። ገብሩ አስራት ግን በአስተዳደር እና በመሳሰሉት ከእነሱ የተሻለ እንጂ ያነሰ አይደለም ብለው የመከራከርያ ነጥባቸው አድረገው እንደወሰዱት ይታወቃል፣፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ገብሩ በአሉታም በአዎንታም ያለው ነገር እንደሌለ ቢታወቅም ያኔ የተሓህት መሪዎች በገብሩ ላይ ጥርጣሬ እንደነበራቸው ግልፅ ነው፣፣…” ብስራት አማረ ( በትግሉ ወቅት የህወሓት የስለላው ክፍል እና የህወሓት እስር ቤቶች ጉዳይ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረ )። “ከዚያ ያደረሰ መንገድ ሲመረመር” (ካናዳ ውስጥ ከሚታተም በሐዋርያ ጋዜጣ የቀረበ)
“በ1981/82 ዓ.ም አቤራ ላይ በተደረገው የማሌሊት/ህወሓት ጉባኤ ገብሩ አስራት ለማሌሊት/መለስ ለስላሳ ለም መሬት ሆኖለት መለስ ዜናዊ ያለውን ሁሉ በታማኝነት ለማረጋገጥ በፖሊሲያቸው/ባመለካከተቻው ለየት ያለ አቋምና ጥንካሬ ያላቸው ጓዶቹን {አንዳንዱም በእንደርታ ተወላጆች ላይ ሳይቀር ማለቱ ነው ለምሳሌ እንደ እነ መስፍን አማረ ላይ}፣፣(ኮሎኔል) መስፍን አማረ በ1969 /70 ገብሩ አስራት ለአመራር ብቁ ነው ፣ አድልዎ መፈጸም የለባችሁም ብሎ ስለ ገብሩ የቆመ ፣ ከድርጅቱ መሪዎች ጋር የተከራከረ የእንደርታ ተወላጅ፣- የሗላ ሗላ ገብሩ ከመለስ ዜናዊ ጋር ሆኖ ስሙን በማጥፋት በመወንጀል መስፍን አማረን አመራር እንዳይወጣ እንቅፋት በመሆን ቀደም ብሎ በአውራጃዊነት አድልዎ የተጠቃው ገብሩ አስራት በአድርባይነት ለመለስ ካደረ በሗላ (ለዓድዋዎች እና አክሱሞች.. አድሮ) ስልጣኑን ለማቆየት ችሏል” ብስራት አማረ “ከዚያ ያደረሰ መንገድ ሲመረመር” በአህጽሮት የተጨመረ የኔ። (የወያኔ ገበና ማሕደር ገጽ 149-151 ደራሲ ጌታቸው ረዳ። ምንጭ ሃዋርያ ጋዜጣ -አዘጋጅ ሙሉቀን ሙጨ- ካናዳ)። በነገራችን ላይ ኮሎኔል መስፍን አማረ ዛሬ ብርጋዴር ጀኔራል ማዕርግ ያለው የስረርዓቱ የውጭ እና የውስጥ ልዩ የደህንነት ጉዳይ ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ ነው።
በድርጅቱ ዋና ዋና ሰዎች አንደበት የተነገረን በደም ጥራት ቀለም የተቀባው ፋሺስታዊው የወያኔ የጥላቻ ብትር ለራሱ ሕዝብ እንኳ እንዳልማረው ነው። በነገራችን ላይ ብስራት አማረ ወያኔ ዘረኛ ነው ይበለን እንጂ እራሱም ባለፈው ቅዳሜ (ማረቸሀ 15/2014 በፈረንጆች አቆጣጠር) “ገዛ ተጋሩ” በመባል የሚታወቀው በተዋጣላቸው ጸረ አማራ ዘረኞች የሚመራ ፓል ቶክ የጎጃም ሕዝብ “ዝቅተኛ፤ኢድየት፤ እና ሪታርድ ነው!” በማለት የጎጃም ሕዝብን የዘለፈቺው ሕድያት ትግራይ የተባለቺው የራያ እና አዘቦ “ጨርጨር፤መዀኒ” ልጅ /የፓልቶኩ ዋና ባለቤት ልብ ይለዋል።) በእንግዳነት ተጠርቶ “አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ሲደርስ ወደ አገር አንዳይገባ በመከልከሉ” ምክንያት ይመስለኛል፤ በጉዳዩ ማብራርያ እንዲሰጥ በተጠየቀበት ወቅት ያገዱትን የወያኔ ከፍተኛ ሹሞች “ዲቃላዎች” በማለት ሲዘልፋቸው ተደምጧል። አንግዲህ የትግል አጋሮቹ ወደ አገር አንዳይገባ ስላገዱት “ዲቃላዎች” ብሎ ሲዘልፋቸው፤ የወያኔ ዘረኛ በሽታ ሁሉንም አንዳጠቃቸው ማሳያ መረጃ ነው። በጎሳ ፖለቲካ መደራጀት ‘የማሰብ ሚዛንህ የሚያዛባ’ የጥላቻ ፖለቲካ ነው፤ወያኔ በደም ጥራት የሚጓዝ ፋሺስት ነው፤የምላችሁም ለዚህ ነው። አሁን ወደ ዋናው ርዕስ ልውሰዳችሁ።