"ህወሓት/ ትህነግ/ ማለት አማራን በመፍራት የዝቅተኛነት ስሜት (inferiority complex) የሚያሰቃየው ድርጀት ነው" አማራ ብልጽግና - እኛስ ምን አለን!! WEEY GUUD!!
Posted: 27 Jul 2020, 10:23
"ህወሓት/ ትህነግ/ ማለት አማራን በመፍራት የዝቅተኛነት ስሜት (inferiority complex) የሚያሰቃየው ድርጀት ነው" አማራ ብልጽግና - እኛስ ምን አለን!! WEEY GUUD!!
Amhara Prosperity Party /APP/
የህወሓትን/ የትህነግን/ ጠላትነትና እኩይ ተልዕኮ በውል መረዳት ያስፈልጋል!!
/ክፍል 1/
የህወሓት/ትህነግ/ የወትሮ ጠላት አማራ ነው፡፡ አማራን በመጥላት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ፍልስፍና በመዳፉ ጨብጦ ለተወለደውና የጥላቻን ጡጦ እየጠባ ጥርስ ላበቀለው ህወሓት ስለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃነሚት አንስቶ በመሞገት በጎ ምላሽ መጠበቅ ምንጭ በሌለበት ወራጅ ውሀ ለማግኘት እንደመፈለግ ያለ ሞኝነት ነው፡፡
አማራን በመፍራት የዝቅተኛነት ስሜት (inferiority complex) የሚያሰቃየው ህወሓት/ ትህነግ/ ትላንትም የአማራን ህዝብ እንደስጋት ሲቆጥረው ኑሯል፤ ዛሬም ሆነ ነገ ከዚህ በሽታ ሊላቀቅ የማይችል ጽንፈኛ ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም ከእውቀትና ከነባራዊ ሁኔታ ውጭ የሆነ ትንታኔና አረዳድ ሳያታልለን የህወሓትን መሰሪ አካሄድ በአግባቡ መረዳትና ለመላው ህዝባችን በግልጽ ማስረዳት ያስፈልጋል፤ ይገባልም፡፡
የትግራይ ህዝብ መቸም ቢሆን የአማራ ህዝብ ጠላት ሊሆን አይችልም፤ የአማራ ህዝብም ለትግራይ ህዝብ ጠላት የሆነበት የታሪክ አጋጣሚ አልነበረም፡፡ ወደፊትም የህዝቡ የእርስ በእርስ ግንኙነት ከጋራ ተጠቃሚነትና ከአብሮነት ውጭ ሊሆን ከቶ አይችልም፡፡
ህወሓት/ ትህነግ/ በሚከተለው የበሬ ወለደ አስተምህሮ ከማህበራዊ ሳይንስ ፍልስፍና ባፈነገጠ አስተሳሰብና እምነት ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ሀውልት በሁለቱ ወንድማማችና እህትማማች ህዝቦች መካከል ማስቀመጡ ከድርጅቱ የአእምሮ መዛነፍ (psycho disorder) አንጻር ባያስገርምም በህዝብ ለህዝብ የትውልድ ጅረትና ማህበራዊ ትስስር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡የትግራይ ህዝብ እንደአማራ ህዝብ ሁሉ በዘመናት የጭቆናና የድህነት ቀንበር ውስጥ የኖረ ህዝብ ነው፡፡
ሁለቱም እህትማማች ህዝቦች ለዘመናት የተጫነባቸውን የጭቆና ቀንበር ከላያቸው ላይ አውርደው ለመጣል በየመድረኩ መስዋዕትነት ከፍለዋል፣ በአንድ ጉድጓድ እስከመቀበርም ደርሰዋል፡፡ ስለሆነም የአማራ ህዝብም ሆነ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ህወሓት የሚረግጠውን የጥላቻ ድንጋይ እየረገጡ በመራመድ ህዝብን የህዝብ ጠላት የማድረግ እቡይ ሀሳብም ትልምም የላቸውም፡፡
ህወሓትን የምንታገለው ደጋግሞ ስለሚሳሳትና ዛሬም ድረስ ከስህተቱ መውጣት የማይችል ጸረ ህዝብ ድርጅት ስለሆነ ነው፡፡ ህወሓት ጸረ ህዝብ ድርጅት ነው ስንል ከራሱ የቡድን ፍላጎት በላይ ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቅንጣት ያህል ውግንና የሌለው በትግሉ ሰማዕታት መቃብር ላይ ቆሞ ጮማ ይቆረጥልኝ ሻምፓኝ ይረጭልኝ የሚል እብሪተኛ ድርጅት ስለሆነ ነው፡፡
ይህ እብሪተኛ ድርጅት በሚከተለው ጸረ ህዝብ የትግል ስልት ምክንያት ብዙ ሽዎች ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል፡፡በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ዜጎች ቤት ንብረታቸው ወድሞ ተፈናቅለዋል፤ የኢትዮጵያን አንድነት ለማፈራረስና ዱካ ወደሌለው የእርስ በእርስ መጠፋፋት እንድንመጣ ዲጂታል ሚዲያን በመጠቀም የሞት ሽረት ትግል አድርጓል፡፡ ለጥፋት ኃይሎች ስልጠናና፣ የሎጀስቲክ ድጋፍ በማድረግ ለግጭትና ለትርምስ ፍጆታ እዲውሉ አሰማርቷል፡፡ በተለይም ለውጡንና የለውጥ ኃይችሎን ለማጥፋት በስውርና በግልጽ ጦርነት አውጇል፡፡ መሰረታቸውን በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ባደረጉ ጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር ወሰንየለሽ ስምምነት ከማድረግ ፈጽሞ የማይቆጠብ ድርጅት ነው፡፡
ህወሓት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችንና ህገ-መንግስትን ደጋግሞ የሚያነሳው የተለየ ህዝባዊና ህገ-መንግስታዊ ውግንና ስላለው አይደለም፡፡እንደህወሓት አይነት አብሪተኛና ጽንፈኛ ድርጅቶች የህብረተሰቡን ስስ ፍላጎት የትግል ማእከላቸው አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡ በተለይም በህወሓት ቤት ከውስኪ መጠጫ ብርጭቆ ያነሰ ዋጋ የማይሰጠውን ህገ-መንግስት በአደባባይ ላይ ለማንገስ መሞከር ህወሓት ያደገበት የሸፍጥ ፖለቲካ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት የኢትዮጵያ ህዝቦች የሉአላዊነት መገለጫ ነው፡፡ ህወሓት ህገ መንግስቱን የሚያከብረውም ሆነ እንዲከበር የሚፈልገው ትልቅ አጥንት ብቻውን ይዞ ሲታገል የቆየ ውሻ የሚበላውን አጥንት ሊጋራው የሚመጣን ሌላ ተገዳዳሪ ውሻ ለማባረር የቁጣ ጩኸት ለማስተጋባት እንደሚጣጣር ሁሉ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማፈንና ብቸኛ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ስለሚፈልግ ብቻ ነው፡፡
ከዚህ ውጭ የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ለህወሓት ከተራ ማስፈራርያነት የዘለለ ትርጉም የለውም፡፡
ሌላውና የህወሓት ማጭበርበርያ ስልት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና የፌዴራሊዝም ስርአት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀርቶ የትግራይ ህዝብ በህወሓት ቤት ከህወሓት ቡድኑ ፍላጎት ብዙ እርከን ዝቅ ብሎ የሚታይ ነገር ግን ለህወሓት ስልጣን መራዘም እንደ አንድ መታገያ ስልት የሚጠቅም አጀንዳ ነው፡፡ ህወሓት ጸረ ህዝብ ድርጅት ነው ስንል ለትግራይም ሆነ ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቅንጣት ያህል ቁብ የሌለው ድርጅት ስለሆነ ነው፡፡ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች፣ አብሮት እየወደቀ፣ የደምና የነፍስ ዋጋ እየከፈለ፣ ውሀ ሲጠማው የሚጠጣውን እያቀረበ፣ መንገድ ሲጠፋው መንገድ እያሳየ፣ ለስልጣን ያበቃውን የአማራ ህዝብ ትምክህተኛና ነፍጠኛ፣ የኦሮሞን ህዝብ ጠባብና ኦነግ በሚል አሸማቃቂ ቅጥያ እግር ከወርች አስሮ ሲያሰቃየው መኖሩ ፈጽሞ ሊዘነጋ አይችልም፡፡ የትግራይ ህዝብስ ቢሆን ልጆቹን ለነጻነት ገብሮ የተቀዳጀውን ድል እፎይ ብሎ በፍትሀዊነት ማጣጣም ሲገባው አማራ ያጠፋሀል፤ ኦሮሞ ይውጥሀል፤ ከእነዚህ ህዝቦች ጋር ህብረት ከፈጠርህ ባንዳ ነህ እያለ ባልተገባ መንገድ ሲመራው የቆየ ድርጅት መሆኑ እየታወቀ ህወሓት በየትኛውም ሞራሉ ለብሄር ብሄረሰቦች ተቆርቋሪና የፌዴራል ስርአቱ ጠበቃ ሊሆን አይችልም፡፡
ህወሓት ጸረ ህዝብ ድርጅት ነው የምንለው ያለምክንያት አይደለም፡፡ ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ለመከፋፈል የሚያሴር ድርጅት ስለሆነ ነው፡፡ ራሱ በተኮሰው ጥይት የሚሞተውን ነፍስ እገሌ ገደለው ብሎ በአደባባይ ላይ ሲያውጅ ቅሽሽ አይለውም፡፡ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ንጹሀንን ቀብሮ ሲያበቃ በቦታው ያልነበረን ኃይል ጠቅሶ የጉድጓዱ ባለእዳ ያደርገዋል፡፡ ራሱ በወረወረው ቦንብ የራሱን ህዝብ ጨፍጭፎ ሲያበቃ ለተፈጸመው ጭፍጨፋ ልብወለድ እየጻፈና እያስጻፈ የኃይል ማሰባሰቢያ አንድ አቅም አድርጎ ይጠቀምበታል፡፡
ትላንት ጥያቄው ሲነሳ የጸረ ህዝብ፣ የትምክህተኞችና የጠባቦች ጥያቄ ነው ብሎ የደፈቀውን የህዝብ ጥያቄ ዛሬ ላይ ለጥያቄው ዋነኛ ጠበቃና ተሟጋች ሆኖ ስለፌዴራሊዝምና ስለብሄር ብሄረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ሲወተውት ከመመልከት በላይ ጸረ ህዝብነት የለም፡፡
ህወሓት በተተኳሽ መሳርያዎች፣ በተወርዋሪ ቀስቶች፣ በሚቀጣጠሉ ኬሚካሎች፣ በሚሰሙ ጩኸቶችና ሞገዶች ሁሉ ራሱን ካልወከለ በህይወት የኖረ የማይመስለው ጸረ ህዝብና ጸረ ህገ-መንግስት ድርጅት ነው፡፡ ወይ ራሱ ባለቤት ሆኖ አቧራ ያስነሳል፣ ወይም ጠላቴ የሚላቸውን አካላት ስም በማብጠልጠል ከሞገዱ ጋር አብሮ ይማግዳቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ መነሻው የህወሓት መሰሪ የትግል ስልት ሲሆን ከራሱ ቡድን ፍላጎት ጋር የሚጋጭ ሆኖ እስካገኘው ድረስ አገርና ህዝብ፣ ህገመንግስትና የፌዴራል ስርአት የሚባሉ ጉዳዮች ለህወሓት ከፕሮፓጋንዳ የዘለለ ተጨባጭ ዋጋ አልወጣላቸውም ወይም የታወቀ ተመን የላቸውም፡፡
ይቀጥላል!!

Please wait, video is loading...