Page 1 of 1
የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡ ተሰማ
Posted: 26 Jul 2020, 08:04
by MINILIK SALSAWI
የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡ ተሰማ
ከሦስት ቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ከአንድ ቀን በኋላ መፈታታቸውን .... የአቶ ዳውድ ስልክ ስለማይሰራ ከራሳቸው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አልቻልንም ....
READ MORE :
https://mereja.com/amharic/v2/307168
Re: የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡ ተሰማ
Posted: 26 Jul 2020, 11:05
by MINILIK SALSAWI
የዛሬ በጉለሌ ታስቦ የነበረው ዳውድ ኢብሳን ከሥልጣን በማንሳትና በሳቸው ቦታ አራርሶ ቢቂላን በመተካት ጋዜጠኞችን በመጥራት መግለጫ መስጠት ነበረ
የኦነግ አባል የሆኑት
1.አራርሶ ቢቂላ
2.ኢብሳ ነጋዋ
3.አቶምሳ ኩምሳ
4.ጀቤሳ ጋቢሳ
5.ቶሌራ አዳባ
6.ዋቆ ኬኔ
የሚባሉት ለዛሬ እሁድ ስብሰባ ጠርተው ነበር ይሁን እንጂ የተቀረው የኦነግ አመራር በዳዉድ ኢብሳ የሚመራው ከላይ የተጠቀሱት የኦነግ አመራሮች ወደ ስብሰባ አዳራሽ ማለትም ጉለሌ የሚገኘው እንዳይገቡ በቄሮዎችን አስደርገዋል።
አሁን እንደአጣራነው ጊቢውን ለቀው እንደሄዱና ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልቻሉ አውቀናል ስለዚህ ጊቢው አሁን ቀደም ብለው የነበሩት ቄሮዎችና ጥበቃዎች ናቸው ያሉት:: ጉለሌ የሚገኘው የኦነግ ጽህፈት ቤት በአሁኑ ሰዓት በፌዴራል ፖሊሶች እየተጠበቀ ይገኛል።

Re: የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡ ተሰማ
Posted: 26 Jul 2020, 13:10
by kibramlak
There is no OLF and OLF-Shene; there is one and only one called OLF