ግና እኔ ሲመስለኝ ህወሀት ወደመጣበት የተመለሰው ያኔ ያነሣትን ዓላማ እንደገና በማስታወስ ጉዞውን ወደ ነጻነት ያደርጋል የሚል ነበር፡፡ ትግራዋይና አማራ ነኝ የሚለው አማርኛ በጋራ የመኖራቸው ተስፋ ዝግ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ አማራ ስልጣኑን ከአደላደለ ይሉኝታ ይዞት አሁን የአማራን መንግስት እየረዳች ካለችው ኤርትራ አሰብን ከመንጠቅ ይመለሳል ብዬ አላምንም፡፡ ስለዚህ የአማራን መንግስት ከተደላደለ እንኳን ትግራዋይ ኤርትራ ያሰጋታል፡፡ አማራ ስልጣን ላይ ሆኖ ኦሮሞ አንዲዋጋ ስለሚያደርግ፡፡
ነገር ግን ስለ አባይ ጉዳይ ተጨንቀውና ተጠበው ሳያቸው ደግሞ እነዚህ ህወሀቶች (ትግራዋይ) ምን ዓላማ ኑሮአቸው ነው ይህን ያህል ስለግድቡ የተጨናነቁት እላለሁ፡፡ ምክንያቱም የዓባይ ውሀ የኦሮሚያ ሲሆን ግድቡ የቤኒሻንጉል ነው፡፡ መለስ ያስጀመረበት ሌላ ምክንያት አለው፡፡ መለስ ስለአስጀመረ ነው ህወሀት የሚጨናነቀው ልል አልችልም፡፡
በመሆኑም ህወሀት እገነጠላለሁ በማለት አስፈራርቶ ስኳር ለማግኘትና ቅቤ ሲጨመርበት መዝለሉን እንደሚያቆመው ሽሮ ህወሀትም ሌላው የአሀዳዊነት አቀንቃን ሁኖ ብቅ ሊል ነው እንዴ የሚል ጥያቄ ያጭራል፡፡ ለነገሩ አማርኞች ትግራይ መገንጠል ትችላለች ያሉት ልባቸውን ሳያዩ አይደለም፡፡
የምሁር ትንተና ያለው ብቅ ይበል፡፡
Has TPLF no goal as a party? Confused as Tigraway nation? Or deliberate distortion to buy time until oldies of the TPLF say bye?