Page 1 of 1

የጉራጌ አረንጓዴ ምድር ካልቸር (ልክ እንደ መስቀል! ኤቦ)

Posted: 22 Jul 2020, 23:25
by Horus

እኔ ብዙ ግዜ ስለ ኢትዮጵጵያ ወይም የጉራጌ አጀንዳ ምን መሆን እንዳለበት ስጽፍ ካሉት አራት አይነት አላማዎች አራተኛ ካልቸር ነው። ይህም ባህል የፈጠራ፣ ኤኮሎጂክል እና መንፈሳዊ ካልቸር መገንባት የሚል ነው ። የፈጠራ ወይም ክሪኤቲቭ ባህል ይታወቃል ። ኤኮሎጂካል ካልቸር ግን ላዲሱ ትውልድ አዲስ ነገር ነው። ኤኮሎጂካል ካልቸር ማለት ከታች በቪዲዮ እንደ ምታዩት አንድ ሕዝብ ያካባቢውን እጸዋት፣ እንሣት፣ ዉሃ፣ አየርና አፈር የመንከባከብ ልምድና ካልቸር ማለት ነው ። እንደ ምትሰሙት አረንጓዴ ልማት ልክ እንደ መስቀል አመታዊ ሕዝባዊ ባህል እየሆነ ነው ። ዬቦ !!!




Re: የጉራጌ አረንጓዴ ምድር ካልቸር (ልክ እንደ መስቀል! ኤቦ)

Posted: 23 Jul 2020, 01:20
by Horus
የዘመናችን ወጣት ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች አሁን ብዙ ተስፋ የሚሰጡ የምርምርና ፍስፈፋ መስኮች እየተከፈተላቸው ነው።

ምሳሌ፤

በጉራጌ የኬር እምነትትና ስነምግባር መልካም ነገር ሁሉ፣ የተባረከ፣ የተመረቀ በረከት ወይም መልካም ሴራ ሁሉ ከሰማይ ይወርዳል፣ ከምድር ይወጣል ። ምርቃት ማለትም ብራኮት፣ በረከት ሲጀመር 'በሰማይ ዬውርድ፣ በምድር ዬውጣ' ብሎ ነው የሚጀምር! ከሰማይ ብርሃን፣ ዝናብ፣ አየር ይወርዳል ። ከምድር ህይወት ማለትም አፈር፣ እጸዋት፣ እንስሳት፣ ሰው፣ ፍጥረት ይወጣል ። የዚህ ሁሉ ወላጅ አፈር ወይም ምደር ነው (ነች) ። ምደር እናታችህን ነች ። ፍጡር ሁሉ የምድር ልጅ ነው ። ምድር ወይም መሬት የሁሉም ነገር እናት ናት ። ሰዎች መሬት ልክ እንደ ሰው፣ እንደ እንሰሳ፣ እንዳ ዛፍ ህያው ማለትም ህይወት ያላት ህዋስ እንደ ሆነች አያቁም ። መድር ህያው ህዋስ ስለሆነች ነው እጸዋት የምታበቅለው፣ ህይወት ያለው ነገር የምትወልደው።

ስለዚህ አንድ በእውነት መንፈሳዊ ነኝ የሚል ማንናውም ካልቸር ምድርን እንደ ህያው ፍጡር ማየትና መንከባከብ ግድ ይለዋል ። በሆኑም ወላጆቼ ጉራጌዎች የኬር ነገር ሁሉ፣ ኬርነት፣ መልካምነት፣ በረከት ሁሉ ከምድር ይወጣል፣ ከሰማይ ይወርዳል ብለው መባረክ መመረቅ ሲጀምሩ ምን ያህል ያዩ፣ ያስተዋሉ እንደ ነበሩ ያሳያል ።

ደሞ ይህ ነው የልማት፣ የእድገት፣ የእላም ፣ ሚዛናዊ ፣ ኤኮሎኪካዊ ና መንፈሳዊ ካልቸር ማለት !!!

Re: የጉራጌ አረንጓዴ ምድር ካልቸር (ልክ እንደ መስቀል! ኤቦ)

Posted: 23 Jul 2020, 05:39
by Guest1
ከላይ የገለጽከው በሙሉ በሁሉም ማህበረሰቦች ይገኛል። በሁሉም!
የጉራጌን ህዝብ ልዩ የሚያደርገው የሰራ ባህሉና የፈጠራ ችሎታው ነው።