ኢትዮ ቴሌ ሀፍረት የሚባል ነገር የለውም እንዴ? ኢንተርኔት ያልተጠቀምንበትን ብር መልሱልን!
Posted: 22 Jul 2020, 12:13
ኢንተርኔት በመቋረጡ አገሪቱ ክፉኛ እንደምትጎዳ ጥርጥር የለውም:: ተሌም በጣም ይከስራል:: ማነው ኪሳራውን የሚሸፍነው? አብይ ከኪሱ አውጥቶ ወይስ ከህዝብ ላይ በመጋጥ? ሁለት ወር ያልተጠቀምንበትን ቴሌ ክፈሉ ሊለን አይችልም:: ይህ በየት አገር ያለ ሕግ ነው?
እንደሚሰማው ቴሌ ግምሹ ለግል መሸጡ ነው: እና መንግስት እንዴት ነው እንደፈለገ “ኢንተርኔት ዝጉ ክፈቱ” ብሎ የሚያዛቸው? የሚደርስባቸውን ኪሳራ ማን ይሞላላቸዋል? ይህ ወደ ፊት እናየዋዋለን :: ይህ የተዛነፈ አካሄድ ምናልባት የግል ባለሀብቶች ሲይዙት ይስተካከል ይሆናል::
እዚህ አገር አንድ ያለ ችግር : የመንግስት መስርያ ቤቶች ፈረንጅ የሚያወጣው ሕግ ይዘው ሙጥጥ ማለት ይወዳሉ:: ፈረንጅ በተግባር ሁሉን ያሳያል ; የኛ አገር ደሞ ዜሮ ናቸው:: ለምሳሌ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ በማውጣትና ሕጉን በመተግበር የሚወዳደረው የለም: ግን ለአገሪቱ ያደረገው ነገር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም:; የሌላው አገር ዩኒቨርስቲ ስንት አስተማሪዎቹ ጉድ የሚባል ነገር ላገራቸው ሲሰሩ የኛዎቹ ግን አንድ ተራ ሞባይል ስልክ መስራት አቅቷቸዋል:: ምናልባትም እንዴት እንደሚሰራም የሚያቁም አይመስለኝም::
ዩኒቨርሲቲው እንደገና ፈርሶ መዋቀር አለበት:: ዩኒቨርሲቲው በግዴታ በግለሰብም ደረጃ ሆነ በግሩፕ : የሆነ ሥራ ሰርተው እንዲ
ያቀርቡ ማድረግ አለበት:: አለበለዚያ እነዚህን ሸክሞች ማባረር ነው ::
በባዶ መኮፈስ እና የፈረንጅን ሱፍ መልበስ የትም አያደርስም:: ሕግ እያወጡ ከመለፋደድ ወደ ተግባር ራስን መቀየር ነው::
ከቴሌ መልስ እንፈልጋለን::