የኤርትራ መንግስትና ህዝባዊ ግንባርን ግልጽ አቋም የሚያመለክት ከ11 ዓመት በፊት ከተሰጠ መግለጫ የተተረጎመ፣
ኢሄ መልእክት በ 2018 የተከሰተውን ሰላም ተጠቅመው፡ ጫፉን ይዘው ትንተና ለመስጠት ለሚሯሯጡ ወገኖች፡ የኤርትራን መንግስት ማይቅየር ግልጽ አቋም እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡"የድንበር ግጭት ከተነሳ በኋላ ወያነ እውነቱን ሸፍኖ ስለ ወደብ ይናገር እንደነበረ ይታወሳል። ' ኢትዮጵያ ያለ ወደብ (ባህር በር) ቀረች እያለ የሌሎች ኣጫፋሪዎች ወሬም ገኖ ነበር፡ መታወቅ ያለበት ግን 'ወደብ' በር ከመሆን ኣልፎ ሌላ ትርጉም የለውም። ኣስፈላጊነቱ ኣጋኖ ማቅረብ ትርጉም የለውም፡፡ በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝብ የነበረው ግንኙነት ከተሻሻለ ወደባችን ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም የማይውልበት ምክንያት የለም፡፡ ኢትዮጵያ 'በኤርትራ ወደብ መጠቀም እፈልጋለሁ' ካለች፡ የማትጠቀምበት ምክንያት የለም። ውግያ በነበረበት ግዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ ተከስቶ ነበር፡ የበጎአድራጎት ማህበሮች በአሰብ በኩል እርዳታ ለማግባት ይፈቀድልን ብለው በጠየቁን ግዜ እምቢ አላልንም። ምክንያቱ በረሃብ የተጎዱ ኢትዮጵያውያኖች በወያነ ሰበብ ችግር ላይ እንዲወድቁ ፍላጎታችን ስላልነበረ። በተቃራኒው 'ለኢትዮጵያ ህዝብ እቆረቆራለሁ' የሚል ወያነ የኤርትራን ወደብ ኣልጠቀምም ማለቱ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያለው ንቀት የሚያሳይ ነው።"