Page 1 of 1

ይድረስ ሊኢትዮጵያውያን! ኢሳያስ ያን መርዘኛ መለስ ዜናዊን ባገኘበት ግዜ ዶ/ር አብይን አግኝቶ ቢሆን ንሮ ዛሬ የት በደረስን!!!!

Posted: 20 Jul 2020, 15:17
by pushkin
እውነቱን ልንገራችሁ እውነተኛውን ኢሳያስ አታውቁትም። የኢትዮጵያ ህዝብ ምናልባት 98%ቱ የወያኔን ኢሳያስ(ህወሓት የተረከችለት) እንጅ የኤርትራውን ኢሳያስ አታውቁትም። ኢሳያስ ለሆዱ የማይገዛ ስልጣንን ፈጽሞ ለቅንጦት ያልተጠቀመ መሪ ነው። ለራሱ እና ለቤተሰቡ ያልኖረ፤ ለኤርትራ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው መጻኢ እድል የሚጨነቅ ለትውልድ ብቻ የሚያስብ ሰው ነው።

ወያኔ ስም በማጥፋት እና በውሸት ተወዳዳሪ የላቸውም። ይህን ለመገንዘብ ያለፋትን 2 ዓመታት ብቻ ኢትዮጵያ ላይ የፈጸሙትን እና ያለችበትን ሁኔታ ዞር ብላችሁ ማየት በቂ ነው፤ ያውም ይህን ሁሉ ችግር እየፈጠሩ የሚገኙት መቀሌ መሽገው ነው። ኢሳያስ እና ኤርትራ ግን ላለፋት 20 ዓመታት ስፍር ቁጥር የለላቸውን ልክ አሁን እንደሚያደርጉ አይነት ተንኮሎችን እና ደባዎችን ተቋቁመው አልፈዋል። ዛሬ መቀሌ የመሸገው ህወሓት ያኔ መንግስት በነበረበት እና ኢጋድን፣ AU፣ UN፣ EU በሙሉ በአሜሪካ አማካንነት በእጁ በያዘበት ወቅት መሆኑ የሚዛኑ ክብደት ይገባቹሃል። እኛ ኤርትራውያን ሀገራችን ከነ ሙሉ ሀብቷ ወደ ኋላ ቀርታ ህዝቦ ተበታትኖ እና ህገ መንግስት የለላት፣ ፓርላማ የለላት፣ ምርጫ የማታዳርግ ወዘተ ሲባል የማይሰማን ወይም የማይመለከተን ይመስላቹሃል ?

እስኪ አስቡት መቀሌ ቁጭ ብለው የሚፈጥሩትን ማእት? የሚሰበስቡት ቅራቅቦ መብዛቱ፡ ፌዴራሊስት የሚሏቸው፣ የአገው፣ የቅማንት፣ 27 ዓመታት ሙሉ ደፍጥጠዋቸው ለነበሩት ደቡቦች ዛሬ መንግስትን ለማዳከም ሲባል ብቻ የደቡብ ቼጎቬራ መስለው የኣዞ እንባ ሲያነቡ፣ ሆዳም አክቲቪስቶችን ለቃቅመው የሚነዙት መርዝ እና በሚድያዎቻቸው ግጭቶችን እንዴት እንደሚያባብሱ አስባቹታል? ዛሬ ይህን መፍጠር የቻሉ ሰዎች ያኔ እንደ መንግስት በቆሙበትበ ግዜ ኤርትራ ላይ የፈጸሙትን ግፍ ክበደቱን ገምቱ።

ከኢጋድ ሀገራት በተጨማሪ ሰንዓ ድረስ ሂዳው የመን፣ ሱዳን ጅቡቲ እና ሶማሊያ ያቀፈ ወታደራዊ እና ፓለቲካዊ የትብብር ቃል ኪዳን ድርጅት መስረተው እኮ ኤርትራን በከበባ አጥቅተዋል። ኤርትራ ላይ ለ10 ዓመታት የተጣለው ማእቀብ ሶማሊያን እና ጅቡቲን ሰበብ ተደርጎ ነው። ዛሬ ገና በጥዋቱ አንደበታቸው በዶ/ር አብይ ላይ እንደሚከፈተው ሁሉ ላለፍት 20 ዓመታት መጀመሪያ ሻቢያ ሻቢያ በኃላ ግን ኢሳያስ ላይ በማነጣጠር ምስኪኑን ኤርትራዊ ጭምር brain washed አድርገው እስከ መቀየር ደርሰዋል። "በጎችን ለመበተን እረኛውን መምታት" የሚለው ቃል የእነሱ ዋነኛ ታክቲክ ነው።

አሁን አብይን ኦሮሞ አይደለም የሚባለው ፕሮፓጋንዳ ለረጅም ዓመታት ኢሳያስ ኤርትራዊ አይደለም ተብሎ ብዙ ተሰርቶበታል። በዚህ ብቻ ብዙ ደካሞችን እስከ ማሳመን በቅተዋል። ሌላው ትልቁ ታክቲካቸው አሁን ዶ/ር አብይ ላይ እንደሚያደርጉት አይነት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት ቀውስ እና ረብሻ ከፈጠሩ በኃላ መንግስቱ ደካማ ነው በማለት ተጠቂው ማህበረሰብ በመንግስት(በአብይ) አመኔታ እንዲያጣ እና መንግስት ላይ ጥላቻን እንዲፈጠር ማድረግ ነው። በኤርትራ ላይ ይህን ሳይታክቱ ለ20 ዓመታት ሰርተውበታል። ህዝባችን እንዲቸገር እና በመንግስቱ ላይ እንዲነሳ በሰፊው ደክመውበታል። አብዛኞቻችን ተንኮላቸውን ብንረዳም የበዙት በጥቅም ተገዝተው ቀላል የማይባሉ ደግሞ ተሸርሽረው brain washed ሁነው የአገራቸው ጠላት እንዲሆኑ ተደርገዋል።

በብዛት የኤርትራን ስም ለማጠልሸት ከሚነሱ ነጥቦች አንዱ የእስረኞች ጉዳይ ነው። ያላወቀ አፉን ቢከፍት አይደንቀኝም ምክንያቱም ውሸት ሲደጋገም እውነት ስለሚመስል። እውነቱ ግን ምንድን ነው? ወያኔ በባድሜ ሰበብ ኤርትራ ላይ ጦርነት ሲያውጁ የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል። የአሰብ ህዝብ የሚጠቀምበትን የውሃ ገንዳ፣ ምጽዋ የሚገኘው ብቸኛው የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ፣ የአስመራ ኤርፓርት በጦር አውሮፕላን በቦንብ ተደብድቧል። እነዚህ ሁሉም የሲቪል ተቋም ናቸው። የከፋው ግን በዛ የሁለቱ ጦር በተፋጠጠበት ድንበር 110 ሽህ ዜጎች ህጻናት እና አረጋውያን ጨምረው ከኢትዮጵያ በግፍ ተባረዋል። የኤርትራ ህዝብ በጣም ጥቂት ስለሆነ በጦርነቱ የበዛው ዜጋ በሁሉም መስክ ሀገሩን በመከላከል ተሳታፊ ነበር። ይህ ብቻ ሳይሆን አብዛኛው የኤርትራ ህዝብ የሚኖረው በደቡብ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ላይ በመሆኑ በጦርነቱ ወቅት ከከባድ መሳሪያ እና ከአውሮፕላን ድብደባ የሸሹ 1.2 ሚልዮን ህዝብ ተፈናቅሎ ነበር። የተፈናቀለው 33% የኤርትራን ህዝብ ቁጥር ይሸፍናል። ይህ ጦርነት ይህን የመሰሉ ብዙ ጎዳቶችን አድርሶ በ2000 ቆመ፤ ጉዳዩም ወደ ፍርድ ቤት ሄደ።

ወያኔ ግን አላማቸው የባድሜ ጉዳይ ስላልነበረ ስራቸውን ውስጥ ለውስጥ ዳግም ጀመሩ። የጀመሩትም በሎቢዎቻቸው አንዳንድ የኤርትራን ባለስልጣናትን አሳምኖ ክፍፍል መፍጠር ነበር። እነዚህ ሰዎች በገንዘብ ይገዙ ወይም ኢሳያስ ሲወርድ የተሻለ ስልጣን የመያዝ ፍልጎት ይሁን ወይም "ወያኔ ጥላቻቸው ኢሳያስ ላይ ስለሆነ እሱ ካልወረደ ሰላም አታገኙም" የሚል በነጮች(ሎቢዎች) ስለተነገራቸው። "የኤርትራ ህዝብ ዳግም ጦርነት ውስጥ ከሚገባ ኢሳያስ ይውረድ በሚል ለኤርትራ ህዝብ በማሰብ ነው" ብለው የሚሞግቱላቸው አሉ። እኔ ግን እርግጠኛ ሁኜ የማወራው ራሳቸው ከተናገሩት ቃል በመነሳት ነው። የቡድኑ አንዱ አባል የሆነው በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበረው ሀይለ ወልደ ትንሳኤ(ድሩእ) የተናገረው ለእኔ በቂ እና በቂ ነው።

ይህ ሚንስትር ልክ ጦርነቱ ባቆመ በወራቶች ውስጥ አውሮፓ ለስራ በሄደበት ወቅት ኤርትራውያን ሰብስቦ "የኤርትራ ሰራዊት ተሸንፏል ብቻ ሳይሆን (ተጠላቅዮ) ተገርፋል ወይም ተበሳብሶ ነው የተሸነፈው" የሚል አስጸያፊ የሰራዊቱን እና የህዝቡን ሞራል እና ቀስም የሚሰብር ንግግር ተናገረ። የዚህ ንግግር ዋና ዓላማ ዳግም ጦርነት ቢጀመር ወይም ወያኔ ብትወረን አቅም የለንም ለማለት ሲሆን። ሌላው ተጨማሪ ንግግሩ ደግሞ "በቃ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሂዷል እኛ ሂሳባችን(ጉዳያችን) እንድርግ" በማለት። ህገ መንግስት አጽድቀን ምርጫ እናድርግ የሚል ቅስቀሳ ጀመረ። የዚህ Group አባላት 15 ሲሆኑ የበዙት አስመራ አንዳንዶቹ ደግሞ ውጭ የሚገኙ(አምባሳደሮች) ሲሆኑ በነዚህ ሰዎች የተፈረመ ደብዳቤ ለፕረዜዳንቱ ገባ።

የደብዳቤው ይዘት የመንግስት ደጋፊዎቹ(እኔን ጨምሮ) እንደሚያምኑት "ወያኔ ችግራቸው ካንተ ጋር ስለሆነ ለኤርትራ ሰላም ሲባል ውረድ" የሚል ነው። ተቃዋሚዎች የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ ከጀመረ ጀምሮ ባይቶው(የህዝብ ተወካዮች) ስብሰባ ተጠርቶ ስለማያውቅ በG15 ፊርማ የገባው ደብዳቤ አስቸኳይ ስብሰባ ይጠራ የሚል ብቻ ነው ብለው ይከራከራሉ። አስቸኳይ ስብሰባው ምንድን ነው ዓላማው ብትሏቸው መልስ የላቸውም። ሁሉም ሚያውቀው ግን ታጋዩች ሆነ ህዝቡ አገር ቋፍ ላይ ባባለችበት ስዓት የውስጥ ፓለቲካ ጥያቄ ማንሳት ጥሩ አይደለም ተብለው ተለምነዋል። እነሱ ግን ያኔ በነበሩ የግል ነጻ ጋዜጦች አማካኝነት ህዝቡን የመከፋፈል ስራ ውስጥ ገቡ። መንግስት ለወር የሚሆን ከታገሳቸው በኃላ አባላቱን እና ከእነሱ ጋር ሲተባበሩ የነበሩ ጋዜጠኞች ጨምሮ ቀፈደዳቸው። የግል ጋዜጦችም ፍቃድ ከዛ እለት ጀምሮ ታገደ። ይህ እርምጃ ትክክል ነው ወይ?

በጣም ሲበዛ ትክክል ነው! በተላይ ከዓመታት በኋላ የወያኔን ፍላጎት እና አቋም ዞር ብለህ ስትመለከቱ መንግስት የወሰደው እርምጃ ከትክክል በላይ ነው። አስቡት እነዚህ ሰዎች ጥያቄውን ያቀረቡ በ2001 ድንበር ላይ የሰፈረው ሰራዊቱ ቤቱ ሳይገባ፣ የድንበሩ ፍርዱ እልባት ሳያገኝ፣ የተሰው ጀግኖቻችን ለቤተስብ ሳይነገር(መርዶ)፡ ከኢትዮጵያ ከተባረርነው 110 ሽህ ህዝብ በተጨማሪ 1.2 ሚልዮን ድንበር አካባቢ ሲኖር የነበረው ህዝባችን ተፈናቅለው በመጠለያና በየከተሞች ተበታትኖ በሚገኙበት ስዓት "ወደ ጉዳያችን እንግባ" ማለት ምን ማለት ነው ?

ለአንዲት ሀገር ከዚህ የበለጠ ምን አይነት ጉዳይ ሊኖራት ይችላል ? ምርጫ ሕገ-መንግስት ምናምን እኮ ሀገር ስትኖርህ ነው። ብቻ ወያኔዎች ሀሳባቸው ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ኤርትራ ላይ የተከሰተው ክፍፍል ጠቀማቸው። እኔ በግሌ የታሰሩት ለወያኔ ትልቅ እድል የከፈቱ የኤርትራን ህዝብ ስቃይ ደግሞ ያራዘሙ ሆዳሞች ወይም ደካሞች አድርጌ እወስዳቸዋለው። ለፓለቲካ ፍጆታ ሲባል ለፍርድ አልቀረቡም ምናምን የሚባለው ውሸት ነው። በወታደራዊው ፍርድ ቤት ተፈርዶባቸዋል። ይህ ፍርድ ቤት እነሱ በሃላፊነት ቦታ ሁነው ለ10 ዓመታት ያገለገለ እና ሌሎች ላይ ሲፈርዱበት የነበረ ነው።

ሌላው የስደተኞች ጉዳይ ነው። ባጭር ቋንቋ ኤርትራ ላይ ህዝቡን የማስኮብለል የተቀናበረ ስራ ኢትዮጵያ ላይ ወይም ሌላ ሀገር ላይ ቢፈጸም አንድ ሰው አይቀርም። አንድ ሰው አረብ ሀገር ወይም ደ.አፍሪካ እንዴት ብሎ እንደ ሚገባ አይጠፋችሁም። የአሜሪካ ቪዛ ስንት ይሸጣል ? Average 25 ሽህ ዶላር። እንግዲያው ትግራይ ውስጥ የኤርትራ ድንበር ላይ ካንፓችን በመክፈት ከኤርትራ ለአንዳንዶቹ ከ15-30 ደቂቃ ብቻ ተጉዘው የአሜሪካ፣ የአውሮፓና የአውስትራሊያ ቪዛዎች እንዲያገኙ በማድረግ ነው ህዝባችንን የመበታተን ስራ የተጀመረው። ዛሬ የበዙ ተጋሩ ሳኡዲ አረብ እና የመን ውስጥ ለምን ተሰደዱ ? የኤርትራዊያን ስደት ግን ለፓለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ዋለ። በእኛ ስም ተጋሩ ብቻ ሳይሆኑ የናይጀሪያ የካሜሮን የመሳሰሉ አፍሪካዊያን የኤርትራ ኩናማዎች ነን ብለው የአውሮፓ ወረቀት አግኝተውበታል። ኤርትራ ገና አዲስ ሀገር ነች፤ በዘመኗ 7 ዓመታት ብቻ ነው የሰላም ግዜ ኑሯት የሚያውቀው። ግን ኤርትራ የሽህ ዓመት እድሜ እንዳላት አውሮፓዊት ሀገር ችግሯን ለከፍተኛ የፓለቲካ ፍጆታ በወያኔ ጥረት ሰማይ እንዲደርስ ተደርጓል።

አሁንም ሀገራችን ላይ ብዙ ጉድለቶች እና ችግሮች ቢኖርም ቅድሚያ የምንሰጠው የሀገራችን ሉኣላዊነት ጉዳይ ብቻ እና ብቻ ነው። 100 ሽህዎች የተሰውለት ሙሉ ህዝባችን ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት የኤርትራ ሉኣላዊነት ሳይረጋገጥ ዲሞክራሲ ምርጫ ምናምን የሚባል ቁማር ኤርትራ ውስጥ አይታሰብም። ሲጀመር ሻዕቢያ የፓለቲካ ፓርቲ አይደለም፤ ሀገር ነጻ ያወጣ ግንባር እንጅ። ደግሞስ ቢፈልጉ እንደ ወያኔ ዓይነት የምርጫ ምናምን ድራማ በህዝቡ ላይ መስራት ከብዷቸው ነው? ለዘመናት የደከሙባትን ሀገር ድንበሯን ሕጋዊ ሳያላብሶ ለማንም ሆድ አደር ጥለው ይሄዳሉ ብሎ የሚያስብ ሞኝ ነው። ወያኔ ከወረረችው መሬት ለቃ በፍርድ እልባት የተሰጠውን የድንበሩን ውሳኔ ካልተቀበለች በስተቀር ትግራይ ካለው የወያኔ ቡድን ጋር ሰላም፣ እርቅ እና ግንኙነት የማይታሰብ ህልም ነው።

(ሰሚራ አምቼ)