Page 1 of 1

አቢይ ወደ አስመራ ለምን አቀና ?

Posted: 20 Jul 2020, 10:47
by Hameddibewoyane
የሳይበር አናሊስቶች ' አቢይ ለምን አስመራ ሄደ ? ' እያሉን ነው። አንዳንዶቹ አቢይ ችግኝም ሲተክል ፣ አረጋውያንንም ሲጠይቅ ለምን ብለው አቃቂር የሚያወጡ ውሀ ወቃጮች ስለሆኑ ብዙም ምላሽ አያስፈልጋቸው ይሆናል። ምንም ብትሰራ የሚራገሙ damned you do , damned you don't አይነት ጉንጭ አልፋዎች ናቸው።

ያም ሆኖ ከአጉል ጸጉር ስንጠቃ ባሻገር ውይይት ለሚሻው ወገን አቢይ ወደ አስመራ ያቀናባቸው ምክንያቶች ላይ ከዚያም ባሻገር የአዲስአበባና አስመራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ማድረግ ጠቃሚ ነው። በግሌ አቢይ ወደ አስመራ ሉሁለት ዋንኛ ጉዳዮች ተጉዟል ባይ ነኝ :

፩. ምክንያት አንድ በአባይ ግድብ ዙሪያ የሚደረግ ውይይት ነው። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ አዲስአበባ ፣ ካርቱምና ካይሮ ሄደው የሶስቱንም ሀገር መሪዎች አነጋግረዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራምፎሳም መጪው ማክሰኞ ሶስቱን መሪዎች የማነጋገር ዕቅድ እንደያዙ እየተሰማ ነው። አቢይ አህመድ ከግብጽ በኩል የመጣ የአቋም ለውጥ ካለ ፣ የውሀ ፖለቲካ ጡዘቱን እንዴት ማብረድ እንደሚቻል ከኢሳያስ ጋር እንደሚመክሩ እሙን ነው። ኢሳያስ አፈወርቂ የአባይ ጉዳይ በዲፕሎማሲ እንዲፈታ ለማድረግ ጥረት መጀመራቸውም የሚደገፍ ነው።

፪. አቢይና ኢሳያስ ከሚወያዩባቸው ጉዳዮች ሁለተኛው የህወሃት ነገር ነው። የዋህ ኢትዮጵያውያን አቢይ እንዴት በሀገሩ የውስጥ ጉዳይ ከባዕድ ሀገር አመራር ጋር ይነጋገራል ሊሉ ይችላሉ። ይህ ጥያቄ ህወሃትን ካለመረዳት ይመነጫል። በቅርቡ ጌታቸው ረዳ እንደነገረን ህወሃት ከመስከረም 30 በኃላ ኢትዮጵያን የሶማሌ ጦር አበጋዞች ሀገር እናደርጋታለን ብሏል። ህወሃት የቴሌቭዥን ስርጭቷ ሲቋረጥ ቀድማ ያቀናቸው ወደ ካይሮ እንደሆነም መዘንጋት አያስፈልግም።

ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኬርሰሞ እንደሚሉን ህወሃት terrorist semi state መሆኗን መተማመን ያስፈልጋል። ህወሃት የአቢይ አስተዳደር በቀጠናው ያለው ተደማጭነት እንዲዳከም ፣ ሀገሪቱን የመቆጣጠር አቅሙ እንዲላላ ጠንክራ እየሰራች ነው። ይሄ ጥንቆላና ባዶ ክስ ሳይሆን ህወሃት ራሷ በመግለጫዎቿ በግልጽ የነገረችን የመልሶ ማጥቃት ስትራቴጂ አካል ነው። ከህወሃት እስከ ኦነግ ሻኔ ፣ ከ OMN እስከ ድምጺ ወያኔ የተዘረጋው ጥምረት እንዲሁ ባዶ የመንግስት ፕሮፖጋንዳ አይደለም። መሬት ላይ ያለ ሀቅ እንጂ። በቅርቡ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተነሳው የጡንቻ ፍተሻ አመጽ የህወሃት የከተማ ስለላ መዋቅር sleeper cells በግልጽ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሳተፉ ታይተዋል። እናም ህወሃትን በልኳ የመከርከም ፖለቲካ ሉዐላዊነትን የማስከበር እንጂ የመጣስ አይደለም። ህወሃት ለጠባብ የፖለቲካ ጥቅሟ የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት አይደለም ህዝቤ የምትለውን የትግራይ ህዝብ ከመሸጥ የማትመለስ የስታሊኒስቶች ስብስብ መሆኗን መዘንጋት አያስፈልግም ።

ለማጠቃለል አቢይ አህመድ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ህብረት አይኑረው ምክር አይውሰድ የሚሉ ድምጾች ይሰማሉ ። ይሄ አይነቱ ምክር ወይ መሬት ላይ ያለ ሰው የሚያሰኝ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የዘነጋ የሳይበር አለም ትንታኔ ነው። ህወሃት ኢትዮጵያን ለማተራመስ ምስራቅ አፍሪካ ላይ ግጭቶች ለመጫር ስትሞክር አራት ኪሎ ቤተመንግስት ብቻ ተቀምጠህ አታጠፋውም። የሀገር ውስጥ ጉዳይ በሀገር ውስጥ መላ ይፈታ የምትለው ተቀናቃኝህ ተመሳሳይ መርሆ ሲይዝ ነው። እነ መለስ ዜናዊ ጋዳፊን ሲያገኙ ' አረብ ነን ' ፣ የሶርያና ሳዑዲ መንግስታትን ሲያገኙ እንዲያ ነን እያሉ በባዕዳን ድጋፍ ነው ደርግን ያዳከሙት። ያ ጠባይና መርሆ አሁንም አለ። አራት ኪሎ ለመመለስ ያ የማይቻል ከሆነ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም። እናም እንዲህ አይነት ክፉ ተገዳዳሪ ቤቱ ያለበት አቢይ አህመድ ነፋስ ግራና ቀኝ እየመታት ያለውን መንግስቱን ለማጽናት የትብብር አድማሱን ቢያሰፋ እንደ ተሳሳተ ስትራቴጂ ሊወሰድ አይገባም።