ያለኢትዮ ቴሌኮም ዕውቅና ውጪ የሚሠራ የሳተላይት መቀበያ በአቶ ጃዋር መኖሪያ ቤት ተገኘ !
Posted: 19 Jul 2020, 05:32
Meles Bisrat
5m ·
ያለኢትዮ ቴሌኮም ዕውቅና ውጪ የሚሠራ የሳተላይት መቀበያ በአቶ ጃዋር መኖሪያ ቤት ተገኘ !
#Ethiopia : ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘውና በቅርቡ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) የተቀላቀለው የአቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ሲበረበር፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ዕውቅና ውጪ የሚሠራ የሳተላይት መቀበያ መሣሪያ መገኘቱን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ለፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡
መርማሪ ፖሊስ የአቶ ጃዋር ቤት በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ ሲበረበር የተለያዩ ሲዲዎች፣ ላፕቶፖች፣ ኮምፒዩተሮች፣ ፍላሾች፣ ኢንተርኔት ለየት ባለ ሁኔታ የሚጠቀሙበት ከኢትዮ ቴሌኮም ውጪ የሆነ የሳተላይት መሣሪያ ተገኝቷል ብሏል፡፡
መርማሪ ቡድኑ እንዳብራራው የድምፃዊው ግድያ ከተፈጸመ በኋላ አቶ ጃዋር ባስተላለፈው ትዕዛዝ በአዲስ አበባ የ14 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን፣ በኦሮሚያ ክልል የወደመውን ንብረት ግምት ገና በመሥራት ላይ ቢሆንም፣ የ167 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና በአጠቃላይ የ181 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃና የሰዎች ምስክርነት ቃል መቀበሉንም ገልጿል፡፡
ብሔርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ አመፅና ዕልቂት እንዲፈጠር ጥሪ መተላለፉንና በርካታ ንብረቶች እንዲወድሙ መደረጉን የገለጸው መርማሪ ቡድኑ፣ ይህንን ድርጊት የሚያረጋግጡለት የ34 ሰዎች የምስክርነት ቃል መቀበሉን፣ 14 የምርመራ ቡድኖች በማዋቀር ከፍተኛ ጉዳት ወደ ተፈጸመባቸው ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ፣ ምሥራቅ ሐረርጌና የተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ለምርመራ መላኩን ጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው!!!