Page 1 of 1

"ጃዋር ከርቀት አይቶ የመለየት ችግር ስላለበት ቤተሰቡን በቅርበት አግኝቶ ለማውራት ጠየቀ" ' ××በእስር ድንጋጤ የታወረው የአለማችን ልዩ ስው ××

Posted: 18 Jul 2020, 19:22
by MatiT
ጃዋርን ይፍቱ የሚል የተንኮል ምክር ሀገር አያሻግርም!
https://m.facebook.com/story.php?story_ ... 1736738995

ይድረስ፡ ለዶ/ር አብይ አህመድ -- ከዶ/ር መኮንን ብሩ

ሸህ ካሊድ ዑመር ለእርሶ (ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ) የላኩትን ግልፅ መልህክት ሰምቼ ይህን ልፅፍሎት ወደድኩ። ሸህ ካሊድ ዑመር ያስተላለፉት መልህክት የጠባብነትን ጥግ ከማሳየቱም በላይ ኢትዮጵያን መናቅ እና ግድ የለሽ መሆንን ያመላክታል።

ስንቶች ቆዳቸዉ በሕይወት እያሉ ተገፈዉ .....ስንቶች መላ ቤተሰባቸዉን በፅንፈኞች በግፍ ተነጥቀዉ ......ስንቶች ዕድሚያቸዉን ሙሉ የለፉበትን በአንድ ምሽት ለእሳት አስበልተዉ ምንም እንዳልተፈጠረ ይርሱት ብሎ ማለት ከሼሁ ሳይሆን እኔን ከመሰለም ዓለማዊ እንኳ የማይጠበቅ ነዉር ነዉ።

ዶ/ር አብይ ሆይ፡ ..... ጃዋርን ይፍቱ የሚል የተንኮል ምክር ወይም ጃዋርን መፍታት ኢትዮጵያን አያሻግርም ፤ ይልቁንም ያጠፋታል። እርሶ በሬ አርደዉ ወይ ኃይማኖተኛ ሰምተዉ ወንጀለኞችን ለመፍታት ከሞከሩ የሚጣሉት ከእኔና መሰል ሚሊዮኖች ጋር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም መቀመቅ መክተት ነዉ።

ዶ/ር አብይ ሆይ....የሕግ የበላይነት የወደፊት መረማመጃችን ብቸኛ መንገድ ነዉ። ሼሁ እየሞከሩት ያለዉ ምክር የኢትዮጵያ መጥፊያ ነዉ። ይቅርታ መፍትሄ አለመሆኑን ብዙ በሬ እንድናርድ ብዙም ንፁሐን በግፍ እንዲጨፈጨፉ አድርጓል። የምንጠብቀዉ በሕግ ስር ትክክለኛን ፍርድ ማግኘት ነዉ። ዶ/ር አብይ በፍፁም እንዳይሳሳቱ እመክራለሁ። ከተሳሳቱና ሼሁን ወይም ሌሎቹን ሰምተዉ ወደ ይቅርታ ሸብረክ ካሉ የእርሶም የፓርቲዎም ..... ምናልባትም ኢትዮጵያም መጨረሻ ይሆናል። ስለዚህ በፍፁም እንዳይሳሳቱ !!

የሀገሬ ልጆች ይህ መልህክቴ ጠቅላዩ ዘንድ እንዲደርስ ሼር በማድረግ ተባበሩኝ። አመሰግናለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!

ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው!!!