Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Abere
Senior Member
Posts: 14874
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Abere » 18 Jul 2020, 14:48

እስክንድር ጥቃት የፈፀሙበትን ፓሊስ ተብዬ ቄሮዎች በህግ ከመጠየቁ በፊት በሰም ለይቶ ስለሚያውቃቸው ሥማቸውን ዘርዝሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቢያሳውቅ ህዝብ ጥላቶቹን ከወድሁ ማወቅ ይችላል። እስክንድ ሥማቸውን በምትችለው መንገድ ለህዝብ አሳውቅ - በእጃቸው ላይ የሌሎች ሰዎች ደም ይኖራል። በሬ ካራጁ ህዝብ እየዋለ ባለበት ሰዓት እነኝህን የመንግስት አሸባሪ ክንፍ ማሳወቅ የአንተ ሌላው የጀግንነት መታወቂያህ ነው። የዐይን እማኞችም ስማቸውን ከነ ፎቶግራፋቸው አጋልጡ - የተፈነ ብዙ ጥፋት ይኖርባቸዋል።



Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Revelations » 18 Jul 2020, 17:11

Please wait, video is loading...

Abere
Senior Member
Posts: 14874
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Abere » 18 Jul 2020, 18:36

Revelations wrote:
18 Jul 2020, 17:11
Please wait, video is loading...
የሃሰት ክስ መሆኑ ከዝርዝሩ ይዘት generic መሆን በቀላሉ ይታወቃል። "አዲስ አበባ ተጀምሮ አዲስ አበባያልቃል" የሚለው ብቻ ለወያኔም፣ለኦነግም ፣ለእስክንድርም የተጠቀሙበት free size የውንጀላ ስልት መሆኑ ግልፅ ነው። እስክንድር መቼም ይሁን መቼ ከሰላማዊ ትግል እና ድምፅ ውጭ ሌላ የጥፋት እና የክፋት አማራጭ ከአፉ ሲወጣ አይታወቅም። አያ ጅቦ ሳታማሀኝ ብላኝ ያለችውን ተረት ይመስላል። ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ ይሉ ዘንድ ዐብይ አህመድ መስቀል አደባባይ ሊገድሉኝ ነበር ያላቸውን ወይም ቤተ-መንግሥት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በድንገት የገቡት ወታደሮች በተመለከተ ምንም ሳያሰጉት እና ሳይቆጨው እስክንድርን ነበር መርዞ የያዘው። እስክንድር አዲስ አበባን ከቄሮ ጥፋት ስለታደገ። ዐብይ ልክ በመንግሥቱ ላይ እንዴ መጣበት ነበር የቆጠረው። እርሱ መሥራት የተሳነውን ወይም አውቆ የተወውን ሥራ ብቻ ለከተማዋ ስለ ሠራ ። ምክንያቱም የአዲስ አበባ ህዝብ ጠፍቶ ከባሌ እና አሩሲ ኦሮሞ መጥቶ እንድ ሰፍር ስልት ተነድፎ ስለነበር።

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by sun » 18 Jul 2020, 19:02

Abere wrote:
18 Jul 2020, 14:48
እስክንድር ጥቃት የፈፀሙበትን ፓሊስ ተብዬ ቄሮዎች በህግ ከመጠየቁ በፊት በሰም ለይቶ ስለሚያውቃቸው ሥማቸውን ዘርዝሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቢያሳውቅ ህዝብ ጥላቶቹን ከወድሁ ማወቅ ይችላል። እስክንድ ሥማቸውን በምትችለው መንገድ ለህዝብ አሳውቅ - በእጃቸው ላይ የሌሎች ሰዎች ደም ይኖራል። በሬ ካራጁ ህዝብ እየዋለ ባለበት ሰዓት እነኝህን የመንግስት አሸባሪ ክንፍ ማሳወቅ የአንተ ሌላው የጀግንነት መታወቂያህ ነው። የዐይን እማኞችም ስማቸውን ከነ ፎቶግራፋቸው አጋልጡ - የተፈነ ብዙ ጥፋት ይኖርባቸዋል።
I am not a politician but yet this pathological master liar and extremist professional provocateur calling himself Eski Ni'99a is one of the main if not the only sources of direct and indirect hate speech manufacturers helping and breading counter hate and counter actions. That guy has big dirty mouth meant to spit poisonous garbage and manufacture hate propaganda by characterizing Oromos (50 million) as foreigners and foreign invaders. So in that sense no wonder if his garbage spiting mouth happens to be massaged using olive oil and adjusted to speak normal and truthful, to say the least. :lol:

Yes, he might pull list of names straight out of his back hole in order to cause harms as a revenge action but then again, others can also put name lists and try to make him pea on his trousers. There can be no end in t!t for tat chess games and it leads only in the constant bleeding of Mamma Ethiopia while you are sitting in a foreign country and enjoying sufferance of ordinary Ethiopians wanting peace and security in order to pursue their normal ordinary peaceful regular daily activities!
:mrgreen:

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Za-Ilmaknun » 18 Jul 2020, 19:04

Eskindir is the thorn on the sides of the OPDO administration. The administration cant put the spirites of Addis Abebe in prison. It could however, try and eventually understand that it is only the truth that prevails.

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by sun » 18 Jul 2020, 19:22

Za-Ilmaknun wrote:
18 Jul 2020, 19:04
Eskindir is the thorn on the sides of the OPDO administration. The administration cant put the spirites of Addis Abebe in prison. It could however, try and eventually understand that it is only the truth that prevails.
On the contrary, this street corner street thug, E.Ni'99a, can't put any thorn in the spirit of Finfinne the beautiful and its Horaa Finfinne Hot Spring that have been healing leprosy and other skin diseases through out historical times to the present.

Also he is not a thorn on the sides of the OPDO administration since the OPDO have long ceased to exist as a result of self renewal and natural self transformation to reflect changing local and national environments. And you can't STOP the changes because change is the natural process of life to be understood as ongoing trend and truth to prevail.
8)


Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Revelations » 19 Jul 2020, 16:04

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Revelations » 19 Jul 2020, 17:30

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Revelations » 19 Jul 2020, 23:38

Please wait, video is loading...

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Revelations » 20 Jul 2020, 17:48

Please wait, video is loading...


Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: ድብደባ የፈጸሙብኝን ፖሊሶች መክሰስ እፈልጋለሁ - እስክንደር ነጋ

Post by Revelations » 21 Jul 2020, 21:06

https://www.ethiopianreporter.com/article/19369

ፖሊስ የአቶ እስክንድር ነጋን የከሳሽነት ቃል እንዲቀበል ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ

19 July 2020
ታምሩ ጽጌ


በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተፈቀደ

ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ከደረሰው የሰዎች ግድያና ንብረት ውድመት ምክንያት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በሚውሉበት ጊዜ፣ በፌዴራል ፖሊስ አባላት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡትን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን የከሳሽነት ቃል እንዲቀበል ለፖሊስ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራዳ ተረኛ ችሎት ትዕዛዙን የሰጠው ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ሲሆን፣ በዕለቱ አቶ እስክንድር በተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ነው፡፡ አቶ እስክንድር ቀደም ባለው ችሎት ድብደባ እንደደረሰባቸውና መክሰስ እንደሚፈልጉ ማመልከታቸውን አስታውሰው፣ ፍርድ ቤቱ የሰጠላቸው ትዕዛዝ መኖር አለመኖሩን ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ተመሥርቶ ክስ እንዲመሠርቱ ትዕዛዝ እንደሚሰጥላቸውና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲጎበኟቸው እንደሚፈቀድ እንደተነገራቸው ያስታወሱት አቶ እስክንድር፣ ኮሚሽነሩ በአካል መጥተው እንደጎበኟቸው አስረድተዋል፡፡

‹‹የደበደቡኝን አውቃቸዋለሁ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ናቸው፡፡ የሕግ ጥያቄም አንስቻለሁ፡፡ ነገር ግን እስካሁን ቃሌን የተቀበለኝ የለም፤›› በማለት ያስረዱት አቶ እስክንድር ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታቸውን ከሰማቸው በኋላ ፖሊስ የከሳሽነት ቃላቸውን እንዲቀበላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ እስክንድር ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር በሚውሉበት ጊዜ ድብደባ እንደ ደረሰባቸው ባመለከቱበት ጉዳይ ትዕዛዝ የሰጠው፣ ከድምፃዊ ሃጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከሰዎች ግድያና ከንብረት ውድመት ጋር በተያያዘ ላለፉት 14 ቀናት (እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን የሠራውን የምርመራ ውጤት ሪፖርት ለመስማት በተሰየመበት ወቅት ነው፡፡

መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው በተፈቀደለት ቀናት ‹‹አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሰዋለን፤›› በማለት በአዲስ አበባ በልደታ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በጉለሌና በቂርቆስ ክፍላተ ከተሞች በተሽከርካሪ በመዘዋወር፣ በስልክና በሥራቸው በአደራጇቸው ሰዎች በመታገዝ፣ እንዲሁም ወረቀት በመበተን ብሔርን መሠረት ያደረገ ግጭት እንዲነሳ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን ተናግሯል፡፡ በዚህም በመንግሥትና በግል ተቋማት ላይ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች መውደማቸውን፣ ከ20 በላይ የምስክሮችን ቃል በመቀበል ማረጋገጡን መርማሪው አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪው ብሔርን መሠረት ያደረገ ግጭት እንዲፈጠር ግለሰቦችን ማስታጠቃቸውን፣ ‹‹የሃይማኖት ተቋማት ሊቃጠሉ ነው›› በማለት ወረቀት መበተናቸውን፣ በዚህም ምክንያት ንብረት መውደሙንና የሰው ሕይወት ማለፉን በምስክሮች ማረጋገጡን መርማሪ ቡድኑ አስታውቆ፣ ሌሎች ሰፊ ምርመራዎችን ለማድረግ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቆች ባሰሙት ተቃውሞ፣ ‹‹መርማሪ ቡድኑ ምርመራውን በሰነድና በምስክሮች ካረጋገጠ ለምን 14 ተጨማሪ ቀናት ይጠይቃል?›› ብለዋል፡፡ ፖሊስ ምርመራውን በምስክር ካረጋገጠ ‹‹ሰፊ ምርመራ ለማድረግ›› በሚል ያቀረበው ተጨማሪ የቀናት ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው፣ የሕግ መሠረት እንደሌለው፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግም የሚያሳየው (የሚያዘው) የተጠረጠሩበት ወንጀል መፈጸሙን ማረጋገጥ ስለሆነና መርማሪዎቹም የገለጹ መረጋገጡን ስለሆነ፣ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት መጠየቅ ተገቢ አለመሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ግን በማንኛውም በኩል ምርመራውን እንደሚቀጥል ከገለጸ፣ ደንበኛቸው (አቶ እስክንድር) የዋስ መብታቸው ተጠብቆላቸው ቡድኑ ሥራውን መቀጠል እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

የስልክ ልውውጡ፣ የአስከሬን ምርመራ ውጤትና የፎረንሲክ ምርመራ የሚገኘው በመንግሥት ተቋም ከመሆኑ አንፃር ተጠርጣሪው ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብታቸውን ሊያስከለክል የሚችል ነገር ባለመኖሩ ሊከበርላቸው እንደሚገባ ጠበቆቹ ደጋግመው ጠይቀዋል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤቱ መርማሪ ቡድኑ ምርመራውን በምስክሮችና በሰነድ ማስረጃዎች ማረጋገጡን መግለጹ ምርመራውን አጠናቋል ማለት እንዳልሆነ ገልጾ፣ 13 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ ለሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


https://www.ethiopianreporter.com/article/19369

Post Reply