አብይ የራሱ ጠላት ነው፤ “ለሁለት አለቃ ማደር” ፤እውነትና ህጋዊነት ከማጠናከር ይልቅ የዘር ፖልቲካ ማጣቀስ ስለመረጠ።
Posted: 16 Jul 2020, 22:27
የዘር ፖለቲክስ የደደቦች ፖለቲካ ነው፡ ስሜት ይጭራል ከዚያ ተነስቶ ደግሞ ስሜቱን ትክክለኛ ነው ለማለት ታሪክአዊ እሮሮን እንደመሰረቱ አድርጎ ውሀ የማይዝ ምክንያት ይደረድራል፡ ፍትህ፤እኩልነት ፤ ዲሞክራሲ ፤ግልጽ የሆኑ ኮንሴፕቶች ናቸው ፤ ነገር ግን በጎሳ ፖለቲካ ሲጨማለቁ መልካቸው ቀይረው ፤ ፍትህን ለማገኝት ሳይሆን የጥላቻና የመግደያ መሳሪያ ይሆናሉ፡፡ አብይ አታዲያ ቆራጥነት የተነፈገው ሰው ስለሆነ ህግን ተመከቶ ፍትሀዊነትን ከማስፈን ወዲህና ወዲህ እየተሽመደመደ ጠላቶቹ እንዲንቁት ፤እሩስ ላይ እንዲያልሙ፤ ከአንዴም ሶስት ግዜ ህይወቱን ሊያጠፉ ሙከራ ሲያደርጉ ፤ ወጥቶ እራሱን ከማስገመት በሰተቀር ምንም ለሚጠሉት ተመጣጣኝ መልስ መስጠት ያልቻለ እራሱን አሁንም ኢላማ ውስጥ አስገብቶ የሚልፈስፈስ ፤ በቀላሉም ጠላቶቹ ሊያጠቁት የሚችሉ ቆራጥነት የጎደለው ሰው ነው፡ ፖለቲካውንና ህጉን በቅጡ ለይቶ ህጉ ህግን በተመለከተ ተጠናክሮ እንዳይቀጥል ፖለቲካ እየከተተ የሚያጨማልቀው እራሱ አብይ ነው፡ ይህ ግን እርሱን ብቻ ሳይሆን ሀገሪቷንም ብዙ ያሚያስከፍል ለጠላቶቹ መሳሪያ በማቀበል ላይ የተሰማራ በራሱና በሀገር ላይ የሚቀልድ ሰው ነው፡፡ ሶስት ግዜ ከሞት አመለጠ ማለት በዚህ መዝለፍለፉ ከቀጠለ ሁልግዜም ያመልጣ ማለት አይደለም፡ ይህንን ክፍተቱን ከወያኔዎችና ከጀዋር ደጋፊዎች በላይ የተረዳ የለም ስለዚህም በጣም ንቀውታል ፤ እራሱን የሚያስንቀው እንዲሁም የልብ ልብ የሚሰጣቸው ግን እራሱ ነው፡ የግድያ ጥሪው በነ ጸጋዬ አራርሳ፤ ኢስካኤል ጋቢሳ ፤ በወያኔ ሚዲያዎች በሞላ በግልጽ በድፍረት እየተላለፈ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ግን ብዙ የአብይ ደጋፊዎችም ህግን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል ባለማስከበሩ ተስፋ መቁረጥ ላይ ደርሰዋል ፤ ያ ደግሞ የበለጠ ስጋት ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡ ማንንም አማራንም ፤ ኦሮሞንም ፤ ማንንም ኢትዮጵያዊ ጋር ወገንነት ሳያሳይ ህግ የሚጥሱት ላይ ፤ ግን የማያወላዳ እርምጃ መውሰድ አለበት እድሚውንም ሆነ ሀገሪቷን ከዚህ ማጥ ውስጥ ማውጣት ከፈለገ; ኢትዮጵያ አትፈርስም እንደመፈክር ጥሩ ነው ፤ ነገር ግን አፍንጫው ስር ተደራጅተው አዲስ አበባ ላይ ድግስ ተደግሶለት የእርስ በእርስ ጦርነት ማንሳት በሚችሉበት ሁኔታ ደርሶ ኢትዮጵያ አትፈርስም አይፈቀድም በማለት ሊቀር የሚችል አይደለም ፡ ወያኔ በዘረፉት ገንዘብ ፤ በገነቡት ስርአት መዋቅር ውስጥ በሰገሰጓቸው የአሳቸው ሰዎች ፤ ከኦነግ እና ከነ ጀዋር ጋር የተቀናጀ ስራ እየሰሩ ነው; እስካሁ ከሰሯቸው ስህተቶች የየተማሩ መሳሪያቸውን እየሳሉ አጠገቡ ደርሰዋል ፤ የዋህን ዉሀ ወሰደው እንዲሉ ፤ በቃላት ድለላ ይህንን አልፋለሁ ብሉ አብይ ካሰበ እጅግ በጣም ተሳስቷል ፡፡ አብይ ጥሩ እይታ አለው ግን በማመንታትና በመዋዥቅ እጁ ላይ ያለውን እድል የያጣ ነው ፡፡ የህዝቡ ድጋፊም ከሁሉም በኩል እየተሸረሸበት ነው ፤ በሀገሪቱ ያሉትን የጸጥታ ተቋማት ተጽኖ የለውም ፤ በዚህ ላይ የሞራል ጥራት ያለው ቆጣ ያለ አቋም ወስዶ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን አያወግዝም ፤ ዘረኖቹ ነፍጠኛ ነው እያሉ ይዘምቱበታል ፤ ሌላው ህዝብ ደግም ሰላማቸውን ፤ ህይወታቸውን፤ ንብረታቸውን እንደ ኢትዮጵያው መከላከል ስላልቻለ ተስፋ ቆጥሮበታል ; በቶሎ ነቅቶ እራሱንና ሀገሪቱን ማዳን አለበት ፡፡ ሌላው ህግንና ፖለቲካ ማጣቀሱና መደባለቁ ትልቅ ፖለቲካ ኪሳራ እያመጣበት ነው፡፡ በህጫሉ የተቀነባበረ ግድያና ሴራ ለህዝቡ ግልጽ ሆኖ ሳለ ፤ የዘር ፖለቲከኞችን እኩል ነው የምንፈርዳችሁ ለማለት ብቻ በምንም መልኩ ከሀጫሉ ግድያና ሲራ ጋር ግንኝነት የሌላቸውን ጀዋርና እስከንድር እየተናበቡ መንግስት ለመገልበጥ ብሎ ሀዝብ ላይ ማላገጥ ለአብይና በእርሱ ስር የሚሯሯጡ ፖለቲከኞችን ብዙ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ፡፡ የሄንን የተበላ የወያኔ ግዜ ጫወታ ቢተውት ይሻላ፤ ግን ከወያኔ እንቁላል የተፈለፈሉ ጯጭቶች ቢመሳሰሉ ምንም አይደንቅም፡ አብይ ግን አራተኛ ተመሳሳይ እድል ይገጥመኛል ብሎ ባያሰላ ይመረጣል ፡ አንዴ ሞት እያየኝ ያልፋል ብሎ ነበር ነገር ግን በራሱ ማወላወልና ፤ ህግን እንደህግ ከመጠቀም ፋንታ የፖለቲካ አጀንዳ ካደረገው እራሱንም ሀገሪቷንም ትልቅ ችግር ውስጥ ይከታል ፡ ሌላው ኢትዮጵያዊ ግን ህግ በሀገሪቱ እስኪሰፍን ድረስ መደራጀት መደራጀት መደራጀት ብቻ ነው ያለበት፤