Page 1 of 1

መልክት ለኢትዮዽያውያን

Posted: 14 Jul 2020, 20:09
by tlel
ያአባቶቻችን የኣያቶቻችን ንጉሶቻችን ጥፋታቸው እራሳቸውን ኢትዮዽያን እንደዛሬው የተበታተነውን ማህበረሰብ በዘመነ መሳፍንት ግዜ ሲገዳደልና ለብርነት ሲሽጣጡ ለቅኝ ግዛትነት ሲዘጋጁ፣ ኣይሆንም ብለው የሞቱ የታገሉ ናቸው። ይህም ስል ሁሉንም ነው ከሠሜን እሥከ ደቡብ ከምዕራብ ዕሥከ ምሥራቅ። ከደርግ ጀምሮ እስካሁን የውጭ ሃይልን ቅኝ ገዢነትን የሚደግፍ፣ በቂም በቀል የመጣ፣ ባዕድ ነገርን ይዞ የገባ ግሩፕ ነው ያለው። እነዚህ ናቸው እየገዙ ያሉት። ብልፅግና ገና ባይታይም የሚታየው ያው ከላይ እንደጠቀስኩት ግሩፖች የተያዙ ናቸው። ምንም መደናገር ኣያስፈልግም። የነሱ ኢትዮዽያ ከታሪኳ የተለየን ነው የሚፈልጉት። የሞቱላትን ኣያት የታገሉላትን ኣርበኛ ከነ ንጉሳትን ካድ ነው የሚሉህ። እውነት ከሆነ በተለያየ ነገር ኢትዮዽያን ከተውክ ስላልታገልክ እውነት ኣገሩን ኣሳልፈህ ከሰጠህ በመታለል፣ ለምን ልሙት ብሎ በሆዳምነት ኣገርህን ኣዳክመሃል ኣሳልፈህ ሰተሃል።

የእውነት ኢትዮዽያ የሚያስፈልጋት ታሪኳን ማንነቷን የማጥፋት ሳይሆን፣ ኣገርን በህዝቧ በሚያስፈልገው ሁኔታ መገንባት፣ መከላከል፣ ከመላው ኣለም ጋር ጥሩ ዲፕሎማሲ መፍጠር፣ እውነት የሆነ የሚጠቅም ትምህርት፣ በጎ የሆኑትን ነገሮች ብቻ ከውጭ መቅሠም። ለነዚህ ነው መሪ የሚያስፈልገው።

ባህልም ሆነ ሃይማኖትም ሆነ ቋንቋ ግላዊ መሆን ያለበትና ከመንግስት መራቅ ያለበት ነው። ግን ዛሬ ህዝብ ሣይሆን ከውጭ ሃይል ጋር ኣላማ ያላቸው ኣገሪቱ እንዳትረጋጋ ለ፭0 ኣመት ኢትዮዽያን እስከማጥፋት ድረሥ እየተጠቀሙበት ነው። ባሑኑ ጊዜ መደረግ ያለበት ኣገር በቀል የሆነና ልምድ ያላቸው ግን ሌላ ኣላማ የሌላቸውን ከውጭም ሆነ ከውስጥ ወክሎ ስልጣኔ በኖረው መልኩ ህዝብ ተውያይቶበት፣ ጤናማ የሆነ ክርክር ተድርጎበት በህግ በምርጫ በማህበር ውስጥ ያለውን የባህል የቋንቋ ወዘተ ችግሮችን መጨረሻ በምርጫ መፍታት ነው።