አንደኛ ፣ አቢይ ማደረግ ያለበት አባ ዱላ ገመዳን ከደቡብ ሞግዚትነት አንስቶ ራሱ የደቡብ ህዝብ የራሱ የሚያምናቸው ሽማግሎች፣ ምሁራን ጋር መነጋገር አለበት ። የደቡብ ሕዝብ በብልጽኛ ፓርቲ ካድሬዎች እየተዘወረ አንድ እርምጃ ሊሄድ አይችልም ። ተቀዳሚ እርምጃው አቢይ የፒፒ ካድረዎችን ሰብስቦ ማስፈራራት ሳይሆን ከያንዳንዱ ዞን አዛውንት ጋር መገናኛ ዘዴ ይኑረው ። አባ ዱላን ከደቡብ ያንሳ ።
ሁለተኛ ፣ የክክልነት መብት ለሲዳማ፣ ለትግሬ፣ ላማራ፣ ለኦሮሞ ፣ላፋር ለአደረ ተገቢ ሆኖ ለጋሞ፣ ለሃዲያ፣ ጉራጌ ወላይታ ለከለከል እንደ ማይቻል አቢይ በመርህ ተቀብሎ በገሃድ ማሳወቅ አለበት ። አይ ክልልሎች ስለ ሚፈርሱ አሁን ሌላ ክልል ግዜ አልፎበታል የሚል ከሆነ አቢይ፣ ይህን የለውጥ አላማና ካርታ በገሃድ ለህዝቡ መንገር ያቢይ ሃላፊነት ነው። ደቡቦች አቢይን ስለሚደግፉት የደቡብን ህዝብ ሊቆጣ፣ ሊገስጽ ፍጹም አይችልም ። እንደዚህ ካለ ያልሰከነ ባህሪ መራቅ አለበት ።
ሶስተኛ ። ኢትዮጵያን እያመሰ ያለው የጎሳ ፖለቲካ ነው ። እሱም ማለት፤ የዘር ፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት፣ የዘር ሕገ መንግስት፣ የዘር ፌዴሬሽን፣ በዘረ ቀመር የተዋቀረ መንግት ነው። እነዚህ 4 የኢትዮጵያ ካንሰሮች ለማረም ሳይሞከር ላንዱ ክልልነት መብት ሰጥቶ ሌሎችን መንፈግ የማይሆን ነገር ነው።
በአንድ ቃል አቢይ ከጉልበትና ግፊት ራሱን ያቅብ ። አሁን አገሪቱ ሌሎች ትላልቅ ጉዳዮች ስላሉባት ይህን የደቡብ ጉዳይ ዛሬ ማንሳቱ ስህተት ነው። ለዎያኔ ፍትፈታ ሌላ መስክ መስጠት ስህተት ነው ።
ስለዚህ፤
አንድ፣ አባ ዱላን አንስቶ ሌሎች በደቡብ ሽማግሎች መተካት
ሁለት፣ የደቡብ ጉዳይ ወደፊት ማሳደር
ሶስት፣ እያንዳንዱ ዞን የራሱን ጉዳይ ለራሱ ዞን ህዝብ መስጠትና የዞኑ ጉዳይ ከጥቂት ፒፒ ካድሬዎች እጅ ማስወጣት
አራጥ እያንዳንዱ ዞን በራሱ ግዜና ሂደት እንዲጓልዝ ማደረግ
ወዘተ