1. የአማራና የአፋር ልዩ ሀይል በቅንጅት ከየክልላቸው ሰላምና ጸጥታ ባሻገር ትህነግ ላይ ዓይናቸውን እንድያደርጉ፤
2. የጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ልዩ ሀይል ከየክልላቸው ሰላምና ጸጥታ ባሻገር በምዕራብ ኦሮሚያ ከኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጎን ሆነው ዓይናቸውን ኦነግ ሼኔ ላይ እንድያደርጉ፤
3. የደቡብ ክልል ልዩ ሀይል ከክልሉ ሰላምና ጸጥታ ባሻገር ከኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጋር በቅንጅት ደቡብ ኦሮሚያ (በተለይም ጉጂ) አከባቢ የሚንቀሳቀሰው ኦነግ ሼኔ ላይ ዓይኑን እንድያደርግ፤
4. የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ከክልሉ ሰላምና ጸጥታ ባሻገር ከኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጋር በቅንጅት የምሥራቅ ኦሮሚያ (ሀረርና ድረዳዋን ጨምሮ) ነውጠኞች ላይ ዓይኑን እንድያደርግ፤
5. የፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባና አከባቢዋ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሁሉንም ክልሎች የጸጥታ ሀይሎችን እንድያግዝ፤ ተወሰነ።