ነገር ግን የኦሮሞ ብሄር ጥያቄ ሲወለድ ጀምሮ አውቃለሁ ። ሲወለድ ጀምሮ ግልጽ፣ የታወቀ፣ ወጥ የሆነ ራእይ፣ እስትራተጂና ግብ እንዳልነበረው ሲጀመር አቃለሁ ።
ከሜጫ ቱለማ መረዳጃ እስከ የሰፋሪ ቅኝ ግዛት ቲሪ ከጓደኞቼ አንጎል ምናብ ወጥቶ በ7 ገጽ ሲጻፍ አቃለሁ ። ያ የዛሬ 50 አመት አካባቢ ነበር ።
ከዚያም የኦሮሞ ጥያቄ ቅርጽ የለሽ፣ ዲፋይንድ ያልሆነ። ወሰን አልባ፣ እንደ ፈለጉት የሚለጠጥ፣ የሚከፋፈል፣ የሚንዛዛ አሰልቺ ሃስብ ሆኖ ዛሬ ደረሰ ።
ዛሬ ለመጀመሪያ ግዜ አንድ አዲስ እጅግ ወሳኝ የሆነ መፈክር ከአቢይም ከታዬ ደንደአም አፍ ሰምቻለሁ ።
እሱም "ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል" የሚለው ነው ።
ይህም ማለት የኦሮሞ ነጻ አውጪ የሚባል ነገር ፣ የሚባል ጥያቄ፣ የሚባል ፓርቲ፣ የሚባል ድርጅት ከዛሬ ጀምሮ የኦሮም ሕዝብ እንደ ማይሻ ማወጃ መፈክር ነው።
ይህ ትልቅ ትልቅ ውሳኔ ነው ። አሁን የኦሮሞ ጉዳይ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ፈቀቅ አለ ማለት ነው ።
እንዲያውም አቢይ ጨምሮ ያለው አሁን የኦሮሞ ጥያቄ "የብልጽና ጥያቄ" ነው ብሎአል ። ይህ አሚን የሚያሰኝ ነው ።
አሁን የኦሮሞ ወጣትም ሆነ ሕዝብ ግልጽ የሆነ አላማ ያዘ ማለት ነው ።
ይህ ደሞ ለመላ ኢትዮጵያ መልካም ነው። ኦሮሞ ወደ ስራ ሲመለስ ኢትዮጵያም ከማያቋርጥ ሁከት ታርፋለች፤ የኦሮሞ ማደግ ደሞ ለሁሉ እድገት ይበጃል ።
ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል የሚለው ትልቅ ውሳኔ ነው !!!
ኦነግን ወደ ታሪክ ክፍል ላኩት፣ በቃ !