Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40247
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጉራጌ ሴራ

Post by Horus » 05 Jul 2020, 03:24

እኔ ቃላት መፍለጥ አልወድም ።

ሴራ የሌለው ሕዝብ ሰርዓትም ፣ አንድነትም፣ ነጻነትም፣ እድገትም ሊኖረው ፍጹም አይችልም። ሴራ የሌው ሕዝብ፣ ስነምግባር፣ ስነነገር፣ ስነስራት፣ ስነሞራል የለውም ። እንደዚህ ያለ ህዝብ ከከብት መንጋ ቀጥሎ ያለ ህዝብ ነው።

አንድ ህዝብ ቢያንስ በአንድ ፈጣሪ ማመን ግድ ይለዋል ። አንድ ሕዝብ አንድ በፈጣሪ አምሳል በተሰራ ግለሰብ ልዑልነትት ማመን ግድ ይለዋል ። አንድ ህዝብ በኢትዮያዊን ሁሉ ወንድማማችነት ማመን ግድ ይለዋል፣ የአንድ ፈጣሪ ልጆች ሰለሆኑ ፤ አንድ ሕዝብ በዚህ ዘመን በስራ ክቡርነት ማመን ግድ ይለዋል። አንድ ህዝብ በዘመናዊ የፈጣሪነት ካልቸር፣ የገስጋሽነት ካልቸር ማመን ግድ ይለዋል ።

ይህ ነው ጉራጌ ። ይህ ነው የጉራጌ ሴራ ኮስሞሎጂ !!!

ይህ ደሞ ሞዴል ካልቸር ነው። አንድ ነገር የሚሳካው ሞዴሉ ትክክል ስለሆነ፣ ዲዛይኑ ትክክል ስለሆነ ነው። አንድ ነገር የሚወድቀው ዲዛይኑ ሞዴሉ፣ ጽንሱ ስህተት እና ጭንጋፍ ስለሆነ ነው።

የኢትዮጵያ የዘር ሞዴል፣ የዘር ፓራዳይም፣ የዘር ቀመር ጭንጋፍ ቲኦሪ ነው ። ይህ ፋክት ነው !!!