Page 1 of 1

ኢትዮጵያ የምትደራጀው በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው (አዋጅ ለዘር ደንቆሮ ሁሉ!)

Posted: 04 Jul 2020, 03:53
by Horus
እኔ ሆረስ እባላለሁ ፣ትንቢተኛም፣ ነቢይም ፣ ጠንቋይም አይደለሁም ። ስለ ፖለቲካ ሳይንስ ሳውጠነጥን እድሜዬን የፈጀሁ ሰው ነኝ ። ስለዚህ ስለኢትዮጵያ ጥልቅ ሳይኮሎጂና አበሻ ምንነት በደንብ አቃለሁ ።

ኢትዮጵያን ከኢትዮጵያዊነት ውጭ በምንም በማንም ሃሳብ ወይ ግፊት አትደራጅም። የኢትዮጵያን አንድና ብቸኛ ማደራጃ ጽንሰ ነገር፣ ቅርጸ ነገር ፣ ሞዴል ኢትዮጵያዊነት ነው ። ትግሬነት፣ አማራነት፣ ኦርሞነት፣ ምናምን እንኳንስ ኢትዮጵያን ቀርቶ ራሳቸው ጎሳዎቹን ሊያደራጅ ያልቻለ የከሸፈ፣ የደንቆሮ ሃሳብ የዘርና የጎሳ ሃሳብ ነው። አንድን ዘመናዊ ሰርአት በጎሳ ለማደራትጀትና በዚያም ተሳፍሮ ወደ ዘመናዊነት ለመሄድ የሚመኙ ደንቆሮች አስተማሪ ያሻቸዋል ።

ኢትዮጵያ በምን ሃሳብ ላይ ነው እንደ አንድ ስርዓት የምትደራጀው ሲባል ያለው አንድ ጽንስ ብቻ ነው ፤ እሱም ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ት !!!!

Re: ኢትዮጵያ የምትደራጀው በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው (አዋጅ ለዘር ደንቆሮ ሁሉ!)

Posted: 04 Jul 2020, 04:44
by clear12
Agreed 100% በዲያስፖራው በችሎታው ሰርቶ መኖር አቅቶት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኛ ፖለቲካ ፕሮግራምን በመቸርቸር የጡረታ ዘመኑ የገቢ ምንጭ አድርጎ ለመኖር ፕላን ያወጣ ሞኝም ሊያስብበት የሚገባ እውነት ነው

Re: ኢትዮጵያ የምትደራጀው በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው (አዋጅ ለዘር ደንቆሮ ሁሉ!)

Posted: 04 Jul 2020, 04:54
by Horus
clear12 wrote:
04 Jul 2020, 04:44
Agreed 100% በዲያስፖራው በችሎታው ሰርቶ መኖር አቅቶት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኛ ፖለቲካ ፕሮግራምን በመቸርቸር የጡረታ ዘመኑ የገቢ ምንጭ አድርጎ ለመኖር ፕላን ያወጣ ሞኝም ሊያስብበት የሚገባ እውነት ነው
ክሊይር 12

በሃሳብህ እስማማለሁ ! ግን የስምህ ትርጉም ምን ይሆን? ከፈለግህ ንገረን ?