የዐብይ አህመድ እርምጃ የሚያስራቸው ሁሉ አጫሉን ገዳይ ናቸው ካለ ፣ እርሱንም በግድያው ተጠርጣሪ አብሮ ያደርገዋል - የደንቆሮ ሥራ ነው።
Posted: 03 Jul 2020, 13:06
የዐብይ አህመድ እርምጃ የሚያስራቸው ሁሉ አጫሉን ገዳይ ናቸው ካለ ፣ እርሱንም በግድያው ተጠርጣሪ አብሮ ያደርገዋል - የደንቆሮ ሥራ ነው። የዐብይ አህመድ ችግሩ እንዴ ጨጓራ ታጥቦ ሆዱ አይጠራም።የምድር እና የሰማይ ያህል የአቋም ልዩነት ያላቸውን ግለሰቦች እና ቡድኖች ሁላችሁም የአጫሉ ገዳይ ናችሁ ማለት ፌዝ ነው። ቢያንስ በቡድን ደረጃ ማን ገዳይ አንዴ ሆነ ሰው ያውቃል። ሾላ በዲፍኑ ንፁህ ነፍስ እና ግብር ከእርሱ በላይ ስለ ኢትዮጵያ የሚቆረቆሩትን ማሰር እና ማንገላታት እራሱን ፀረ-ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል። ለእነ ጁሃር እና የጥንት የፓለቲካ ፍቅረኞች ወያኔዎችን ለማስደሰት ንፁሃንን አብሮ ማሰር አንድም ዕብደት ሁለትም ፍርሃት እና በእራስ አለመተማመን ነው።በእንዴነዚህ ዓይነት ሰዎች ስለምትመራ ነው ኢትዮጵያ ጥሩ መስመር ላይ የማትገኜው። ቀደምት አንድ በበታችነት ስሜት የሚሰቃይ መለስ የሚባል የህሌና ድዊ አሁን ደግሞ እንዴ ዥዋዥዌ ጥሩ እና መጥፎ እየቀያየረ የሚመራ አካሄድ ገደል የሚያስገባ ነው። ዐብይ አህመድ ንፁሃን በአስቸኳይ መፍታት አለብህ።