Page 1 of 1

ሰበር መረጃ (ኢትዮ 360 - ሰኔ 24/2012) አቶ እስክንድ ነጋ በቁጥጥር ስር ዋለ።

Posted: 01 Jul 2020, 12:11
by OBANG
https://www.facebook.com/Ethio360mediaO ... =3&theater

(ኢትዮ 360 - ሰኔ 24/2012) አቶ እስክንድ ነጋ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ እስክንድ ነጋ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ለኢትዮ 360 እንደደረሰው መረጃ አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ ከሰአት በኋላ በቁጥትር ስር የዋለው ምንም አይነት የእስር ማዘዣ ባልያዙ የአዲስ አበባ ልዩ ሃይል አባላት ነው።

ከማለዳው ጀምሮ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ቢሮ በልዩ ሃይሉ ተከቦ መዋሉንም ነው መረጃዎች ያመለከቱት።

አቶ እስክንድር ነጋ በልዩ ሃይሉ እየተዋከበና እየተንገላታ ከቢሮው መወሰዱን እንጂ ተወስዶ የት እንደታሰረ ግን እስካሁን የታወቀ ነገር አለመኖሩን የመረጃ ምንጮቹ አስታውቀዋል።

እንደ መረጃዎቹ ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ የመጓጓዣ ታክሲሆች ታርጋ እየታየና እየተለየ መስታወታቸው ሲሰበርና በድንጋይ ሲደበደቡ ውለዋል ብለዋል።

የተወሰኑ ቤቶች ላይም ጉዳት መድረሱን ነው ጨምረው የገለጹት።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ዛሬ የፈረንሳይ ለጋሲዮን፣የቤላ፣የሽሮሜዳ፣የቄራና የሌሎች አካባቢዎች ወጣቶች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር።

የኢትዮ 360 ምንጮች በራሳቸው በወጣቶቹ ተነሳሽነት የተካሄደው ተቃውሞ እስክንድርን በቁጥጥር ስር እንዲውል ትዕዛዝ የሰጠው አካል በምክንያትነት ሊያስቀምጠው ይቻላል ሲሉ የቅድሚያ ግምታቸውን ሰተዋል።