Page 1 of 1

አትነት ጉራጌ ፤ እጅግ ውብ ጥልቅ የኛሰብ ሜሎዲ የሚመጥን ቪዲዮ ስሩለት !!

Posted: 23 Jun 2020, 02:31
by Horus

አርቲስት ደሳለኝ መርሻ፣ የሚያናድደው የዘፈኑ ማጠር ነው። መልዕክቱ እጅግ ትክክል ግዜያዊ ፣ ዜማው ማር ወለላ !!

ጉራጌ ምርቃት ሲጀምር 'በሰማይ ዬውርድ፣ በምድር ዬውጣ' ይላል፤ ምርቃት ሲያበቃ 'ሙለን ኬር ዬሁን' ይላል! (ሁሉ ነገር ሙሉ ነው እውን ይሁን ማለት ነው)! ይህ የደሳለኝ ነጠላ የራሱ ቪዲዮ ከ16ቱ የጉራጌ ቤተ ሰቦች ጨምሩበትና ታሪካዊ ይሆናል !! ዘርደህም ዬክብር ፤ ዘርኛ ማለቅ ዬሁን!!


Re: አትነት ጉራጌ ፤ እጅግ ውብ ጥልቅ የኛሰብ ሜሎዲ የሚመጥን ቪዲዮ ስሩለት !!

Posted: 23 Jun 2020, 02:34
by Andertan
Why are most of your people a part of the arabist Muslim faith I thought Gurages were Christians not Warlord Worshippers

Re: አትነት ጉራጌ ፤ እጅግ ውብ ጥልቅ የኛሰብ ሜሎዲ የሚመጥን ቪዲዮ ስሩለት !!

Posted: 23 Jun 2020, 03:26
by Horus
እኔ ትምህርትና ክህሎቴ ሙዚቃ አይደለም፣ ግን ሙዚቃ በዝርዝር የሚያዳምምጥ ጆሮ አለኝ ። ተወልጄ ያደኩት በጉራጌ ባላገር ነው። ሁሉንም የባህል ሜሎዲዎች በልቤ አቃቸዋለሁ ። እኔ ክስታኔ ነኝ ፤ ግን አንድም የማልሰማው የጉራጌ ዜማ የለም ። ዛሬ ደሳለኝ የቀመመው ይህ የሁሉንም ሜሎዲ ያዋሃደ አስገራሚ የማይጠግብ ስራ ነው ። በደንብ ዳብሮ ከግሩም ቪዲዮ ጋር እንደ ሚታወጅ አልጠራጠርም ። ኬር ዬሁን !

Re: አትነት ጉራጌ ፤ እጅግ ውብ ጥልቅ የኛሰብ ሜሎዲ የሚመጥን ቪዲዮ ስሩለት !!

Posted: 23 Jun 2020, 03:35
by Horus
The all time classic Teshome Wolde !!!

Re: አትነት ጉራጌ ፤ እጅግ ውብ ጥልቅ የኛሰብ ሜሎዲ የሚመጥን ቪዲዮ ስሩለት !!

Posted: 23 Jun 2020, 03:58
by Horus
ይህን አቤቱታ ማቀርበው ለጸጋዬ ስሜና ፈለቀ ማሩ ነው ። ትክክለኛው የሰርግ የዎሬና ገረድ፣ የዎሬ ነሀ ጎሽ ዜማ ይህ ነው ። የወልኔ ባላገሮች ሚዘፍኑት ፣ ይህ ነበር በክስታኔ ሚዘፈነው ። እህቴ ስታገባ እናቴ ያወረደቸው በቀጥታ ይህ ዜማ ነበር ። በ7 አመቴ ማስታውሰው !!!

ባካችሁን መልሱት፣ ዘብርሙ !!1

Re: አትነት ጉራጌ ፤ እጅግ ውብ ጥልቅ የኛሰብ ሜሎዲ የሚመጥን ቪዲዮ ስሩለት !!

Posted: 23 Jun 2020, 04:05
by Andertan
HORORO


Re: አትነት ጉራጌ ፤ እጅግ ውብ ጥልቅ የኛሰብ ሜሎዲ የሚመጥን ቪዲዮ ስሩለት !!

Posted: 23 Jun 2020, 04:36
by Horus
እኔ ሳድግ የኔ አካባቢ ወጣቶች ከሚጫወቱዋቸው ምጅር መትከል፣ ቡሄ፣ አክራሚ፣ ኢምር፣ ገድራ፣ ደንጌሳት፣ መስቀል፣ ኩስ ወይም ዎጃራጆ፣ እንዞሪቴ፣ አንቃልት፣ ወዘተ እዚህ ምታዩት መስቀል አልፎ ረጅሙ የገና (አንቃት ጨዋታ ቶርናሜንት) ከመጀመሩ በፊት የሚካሄድ ከባድ የጎረምሶችህ ውድድር ጨዋታ ነው ። የጌሙ ቁም ነገር የሰውዬውን ራስ ሳይነኩ እሱን መዝላለ ነው። ስሙ ዝላይ ወይም ኩስ እንለዋለን።

ጸጋዬ ስሜን እናመሰግ ናለን !!!


Re: አትነት ጉራጌ ፤ እጅግ ውብ ጥልቅ የኛሰብ ሜሎዲ የሚመጥን ቪዲዮ ስሩለት !!

Posted: 23 Jun 2020, 05:05
by Horus
ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮ በትንሹ የገና አንቃት የጥንግ ቶርናሜንት ፣ እንዞሪቴ፣ የገና አባት፣ የገና እናት፣ (ዱላ ሚወረወርበት ቤት) ያሳያል ። ግን ሙሉ አይደለም። የጊራጌ ወጣቶች አንቃት (ሆኪ) ወይም ገና ወድድር ለብዙ ሳምንታት ነው ሚክሄደው ከህዳር ሚካኤል እስከ ገና በቀበሌና ቀበሌ ጎረምሳ መሃል ። የገና ቀን ከታቦት በኋላ ሁለት መንደሮች ይጋጠማሉ ። እጅግ ትልቅ በአል ነው።

የሴቶቹ ኢምር አምር ከደመራ ነው የሚጀምር። ይህ የኮከብ በአል ነው። ኢምር የኮከብ ብርሃን ነው። የልጃገርዶቹ ዘፈን ከብት ገብቶ ከ6 ፒኢም እስከ 8/ ፒኤም ድረስ በወዶች እየተጠበቁ ደመራ ስር የሚዘፍኑት ነው ። እዚህ ቪዲዮ ላይ ገና ጋር ገብቷል። ነገሩ ችግር የለውም ። ዛሬ ተለውጦ ነው እንጂ ድሮ ገና ማለት አዲስ አመት ቀን ነበር ።
ያም ሆነ ይህ የህዝቡ ባህል በሙሉ እየተጠና እንደ ድሮ ይመለሳል !!